ከትልልቆቹ የመድሃኒት አምራቾች ድርጅቶች አንዱ የሆነው የፋይዘር የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት Gardasil የሚባለው ሴቶች ልጆችን ከማህጸን ካንሰር ይጠብቃል የሚባለው ክትባት አደገኛና ገዳይ ነው ሲሉ አጋለጡ።

ከትልልቆቹ የመድሃኒት አምራቾች ድርጅቶች አንዱ የሆነው የፋይዘር የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት Gardasil የሚባለው ሴቶች ልጆችን ከማህጸን ካንሰር ይጠብቃል የሚባለው ክትባት አደገኛና ገዳይ ነው ሲሉ አጋለጡ።
ስለ መጨረሻው ዘመን የሚናገሩ እንደ ማቴዎስ 24 ሉቃስ 21 እና ማርቆስ 13 ያሉ ትንቢት አዘል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ባሉት ጊዜያት በምድር ላይ አለመረጋጋትና ጦርነት፣ ረሃብና ብዙ ህዝብን የሚፈጁ በሽታዎች (ቸነፈር) እንደሚበዛ ይናገራሉ። ከእነዚህ መካከል የዛሬው አጭር መልእክት የሚያተኩረውቸነፈርበሚለው ላይ ነው። ባለፉት ብዙ አሰርት ዓመታት ክትባት ብዙ በሽታዎችን በመቀነስ የብዙ ሰዎችን ሕይወት ማዳኑ በሰፊው የሚዘገብ ነው። ይህ በአብዛኛው እውነት ቢሆንም ግን፣ ከክትባት ጋር ተያይዘው ስለሚመጡና ብዙ ሰዎችን ለህይወት ዘመናቸው ህመምተኛና አካለ ጎደሎ አድርገው ስለሚያስቀሩ ወይም የብዙዎችን ህይወት ስለሚያጠፉ ንጥረ ነገሮች ግን በሰፊው አለመዘገቡ የሚያስደንቅና የሚያሳዝን ነገር እንደሆነ ብዙ የህክምና እና የመድኃኒት ቅመማ ባለሙያዎች እንዲሁም ለህዝብ ጤና ተከራካሪ ድርጅቶች ይናገራሉ። ለምሳሌ ያህል በሰሜን አሜሪካና በምእራቡ ዓለም በሰፊው በስራ ላይ በዋሉና ተነባብረው በአንድ ጊዜ በሚሰጡ እንደ MMR እና እንፍሉዌንዛ ባሉ ክትባቶች ውስጥ በሰፊው በስራ ላይ ሲውል የቆየው ታይመሮሳል (Thimerosal) የሚባለው ከሜርኩሪ የሚሰራ ንጥረ ነገር ኦቲዝም የሚባለው የእጅግ ብዙ ወጣቶችን ሕይወት የቀጨውና ያበላሸው ህመም ምንጭ መሆኑ እርግጠኛ ነው የሚሉ ብዙ የህክምና እና የህዝብ ጤና ተከራካሪ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ቁጥር እየበዛ መጥቷል። ይህ Thimerosal እና የኦቲዝም መስፋፋት እጅግ ያሳዘናቸው 1960ዎቹ የተገደሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ዘመድ የሆኑት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ጁኒየር ጉዳዩ ያሳዘናቸውንና ያበሳጫቸውን እጅግ ብዙ ባለሙያዎች በማስተባበር እነዚህ ሰውን የሚጎዱ በክትባት ውስጥ የሚጨመሩ ንጥረ ነገሮች ከገበያ ላይ እንዲወገዱ ዘመቻ ሲያደርጉ ቆይተዋል። እኒሁ ታዋቂ ሰው ከሌሎች ዶክተሮችና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በጻፉት “Thimerosal, Let the Science Speak” በሚለው መጽሐፍ ላይ በThimerosal እና በኦቲዝም መካከል ያለው ቁርኝት ሳይንሳዊ መሆኑ የሚያሳዩ ብዙ ጥናቶችን ለአብነት ያቀርባሉ።

እነዚህን ክትባቶች የሚሰሩት በቢሊዮን ዶላር በመሸጥ የሚበለጽጉት የመድሃኒት ቀማሚ ድርጅቶች በመንግስትም ሆነ በግል የጤና ድርጅቶች ገንዘባቸውን በመጠቀም፣ በህክምና ባለሙያዎች፣ በትምህርትና በምርምር ተቋማት እንዲሁም በመገናኛ ብዙኃን ላይ በሚያደርጉት ተጽእኖ ምክንያት ክትባቶቻቸው በህዝብ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት እንደሚታፈን ከነዚያው ከክትባት ሰሪ ድርጅቶቹ ውስጥ ምስጢሩን የሚያጋልጡ ባለሙያዎች ጥቂት አይደሉም። በዚህ ምክንያት አንዳንድ ክትባቶች፣ በተለይም ደግሞ በክትባቶቹ ውስጥ ያሉ ጎጂ ንጥረ ነገሮች በብዙ ህጻናት፣ ጎልማሶችና አዋቂዎች ህይወት ላይ የሚያደርሱት ሞትና ጉዳት እንደ ውሸትና በሳይንስ ያልተረጋገጠ አወዛጋቢ ነገር ሆኖ በመገናኛ ብዙኃን ይቀርባል። በአሜሪካን አገር ብቻ እንደ አሸን የፈላው የኦቲዝም በሽታ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ልጆችን ህይወት የጎዳ በመሆኑና፣ ችግሩም እየተባባሰ በመሄዱ ባለፉት ብዙ ዓመታት የአሜሪካው ፌደራል መንግስት የተወካዮች ምክር ቤት እንኳን ሳይቀር በጉዳዩ ላይ ብዙ ውይይቶችን ማድረጉ የታወቀ ነው። ኦቲዝም የሚባለውና በአብዛኛው ወንዶች ልጆችን በከፍተኛ ቁጥር የሚያጠቃው ህመም ዋነኛ ምንጩ ከላይ የተጠቀሰው ከሚርኩሪ የሚቀመመውና በአንድ ላይ የሚሰጡ የተለያዩ በሽታ ክትባቶች ጊዜያቸው እንዳያልፍ የሚጨመረው ታይመሮሳል የሚባለው ንጥረ ነገር መሆኑ በብዙ ባለሙያዎችና ጉዳቱ በደረሰባቸው ልጆች ቤተሰቦችም የሚታመን ሆኗል። ምሳሌን ለመጥቀስ ያህል በካናዳ ስራ ላይ ከዋለና በብዙ ልጆች ላይ የሜኒንጃይተስ በሽታ ካስከተለ በኋላ በህዝብ ጩኽት ከገበያ ላይ የተወገደው MMR ክትባት ስሙ ወደ  Pluserix ተቀይሮ በ1980ዎቹና 90ዎቹ በእንግሊዝ አገር ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በዚያም ብዙ ልጆችን ስለጎዳ ታግዷል። ነገር ግን ክትባቱ በፍጹም ከገበያ ላይ በመነሳት ፈንታ እንደገና ስሙ ተቀይሮ እንደ ብራዚል ባሉ አዳጊ አገሮች በስራ ላይ መዋሉ በሰፊው ተዘግቧል። ለአብነት ያህል በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ አንዳንድ የባለሙያና የዜና ድርጅቶች ድረ ገጾች በዚህ ተመልክተዋል፡https://vaccinechoicecanada.com

http://www.nvic.org


ክትባቶች ሁሉ መጥፎ ናቸው ለማለት ወይም ክትባትን ሁሉ መውሰድ በሽታን ያስከትላል ለማለት አይቻልም። ነገር ግን በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየበዙ ከሄዱት እንደ ኦቲዝም፣ የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት መጨመር፣ የተለያዩ አለርጂዎችና የአእምሮ በሽታዎች እንዲሁም በሰውነት ውስጥ እብጠትን እና የማያቋርጥ ህመምን የሚያመጣው አውቶ ኢሚዩን የሚባለው ህመም ወረርሽኝ ብዙ ምንጮች መካከል አንዳንድ አደገኛ ክትባቶችም እንዳሉበት ለመጠቆምና የሚችል ሰው ሁሉ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሻ ለማሳሰብ ነው። በዚህ ላይ ሊጨመር የሚገባቸው ሁለት ትልልቅ ቁም ነገሮች አሉ። 1) ብዙ ክትባቶች እንደ ሌሎች መድኃኒቶች በብዙ ሙከራ ውስጥ አያልፉም። ስለዚህም ክትባቶቹን አምራች የሆኑት ታላላቅ የምእራቡ ዓለም (በተለይም የአሜኪካ) መድሃኒት አምራች ድርጅቶች በክትባት በሞቱና በተጎዱ ሰዎች ቤተሰቦች ሊደርስባቸው በሚችል ክስና የገንዘብ ቅጣት እንዳይከስሩ የአሜሪካው ምክር ቤት ብዙ ህጎችን አውጥቷል። የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ወደርሱ አቤት በተባሉ ክሶች ላይ ተመርኩዞ የእነዚሁኑ ክትባት አምራች ድርጅቶች ጥቅም ብቻ የሚጠብዙ ውሳኔዎችን አስተላልፎአል። ታሪክ የሚጻፈው በአሸናፊዎች፣ ክስም የሚሰምረው ገንዘብና ጉልበት ላላቸው ነው የሚለው አባባል ብዙ እውነትነት እንዳለው በክትባት ምክንያት የተጎዱ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኦቲዝም፣ የተለያዩ የአካልና የአእምሮ ህመሞች፣ የአለርጂና የእውቶ ኢሚዩን ህመም ሰለባዎች እየተረዱ ነው።  ከሁሉም በላይ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ዶክተሮችን ጨምሮ ብዙ የህክምና ባለሙያዎችም ቢሆን አንዳንድ ክትባቶች በእርግጥ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን አለማወቃቸው ነው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከክትባቶቹ ጋር ተያይዘው የሚላኩት ወረቀቶች ራሳቸው በግልጽ ክትባቱ ጉዳትና ሞትም ጭምር ሊያደርስ እንደሚችል ቢገልጽም አንዳንድ ሃኪሞች በማወቅም ባለማወቅም ይህን ማስጠንቀቂያ በማጣጣል “ይሄ እንደ አጋጣሚ ካልሆነ በቀር አይሆንም” ስለሚሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ልጆቻቸውን፣ የልጆቻቸውን ጤናና ደህን  አጥተው በመከራ ይኖራሉ።

እውቀትና ቴክኖሎጂ እያደገ በሄደበት በዚህ ዘመን ለብዙ ህመሞችና በሽታዎች ክትባትና መድሃኒት መገኘቱ የሚያስደስተውን ያህል፣ በታላላቆች የመድሃኒት አምራች ድርጅቶችና በተባባሪዎቻቸው ስግብግብነት ምክንያት አንዳንድ ክትባቶች እጅግ ብዙ ጉዳቶችን ማድረሳቸው፣ ይህም ደግሞ ከህዝብ መሰወሩ ቢያሳዝነንም ሊያስደንቀን አይገባም። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነውና። ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ዘመን እንደሚመጣ እወቅ ብሎ ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ያስጠነቀቀን። 2ኛ ጢሞ ምዕ 3። እንደምንገምተው ረሃብና ቸነፈር ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ አይደለም። እልቂትና ጦርነት ወይም ሁከት በአጋጣሚ አይከሰትም። ስለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ለመሪዎች፣ ለመኳንንትና ለባለስልጣናት ሁሉ በያለንበት እንድንጸልይ የሚያስተምረን። የክፋት፣ የጭካኔና የእልቂት ደራሲ የሆነው ዲያብሎስ የሚፈረድበት ጊዜ እንደደረሰ ስለሚያውቅ በስግብግብነትና በራስ ወዳድነት የተሞሉ የግል ድርጅቶችም ሆነ የመንግስት ባለ ስልጣኖችን በመጠቀም የሰውን ዘር የሚያጠፋበትን ስራ እንዳይሰራ መጸለይ በክርስቶስ ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ሁሉ ግዴታ ነው። እንንቃ፣ ለአገራችን፣ ለህዝባችን፣ ለምንኖርባቸው አገሮች መንግስታትና ባለ ስልጣናት ሁሉ ከልብ እንጸልይ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ ይመጣል። ያለንበት ዘመን አስጊና አስፈሪ ቢሆንም “እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጌዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” ማቴ 28፡20 ያለው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም ከሚያምኑት፣ ተስፋ ከሚያደርጉትና ከሚታዘዙት ሁሉ ጋር ነው። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኃያላኑና ባለጸጎቹ አገሮች ወይም ድርጅቶች የምድርን አየር ንብረት እንዳሻቸው ለመለወጥ መቻላቸው ይፋ እየሆነ ነው።

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኃያላኑና ባለጸጎቹ አገሮች ወይም ድርጅቶች የምድርን አየር ንብረት እንዳሻቸው ለመለወጥ መቻላቸው ይፋ እየሆነ ነው። http://www.newsweek.com/artificially-cool-earth-volcano-eruptions-extremely-dangerous-711203
ከብዙ ሳምንታት በፊት በላክሁት መልእክት ሃብታሞቹ አገሮች ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሚፈልጉት ቦታና ጊዜ ደመና እንዲፈጠር፣ ዝናብ እንዲዘንብ ወይም እንዳይዘንብ፣ ነጎድጓድና መብረቅ እንዲሁም በምእራቡ ዓለም ሃሪኬን (Hurricane) በእስያ ደግሞ ታይፉን (Typhoon) የሚባሉ ከፍተኛ ጥፋት የሚያደርሱ የአየር ማእበሎችን መፍጠር እንደሚችሉ ተጠቁሞ ነበር። ለብዙ አሰርት ዓመታት የዚህ ቴክኖሎጂ መኖርና በቬትናምና ሌሎችም ቦታዎች ላይ አሜሪካ ይህን ቴክኖሎጂ ለጦርነት ማዋሏ ሲካድ ከቆየ በኋላ ጉዳዩ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በአሜሪካ ምክር ቤትም ሳይቀር ውይይት የሚካሄድበት ሆኗል። ይህን ማገናኛ (link) በመጠቀም የአሜሪካው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ያደረገውን ስብሰባ የተመለከተ ዜናን ማግኘት ይቻላል፡http://www.homelandsecuritynewswire.com/us-congress-holds-hearings-geoengineering
ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ዜና እንደምታነቡት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የሚለቅቀውን አቧራ ዓይነት ሰው ሰራሽ ግርዶሽ በምድር ከባቢ አየር ላይ በመፍጠር የምድርን ከባቢ አየር የሚያሞቀውን የጸሃይ ብርሃን በመቀነስ በሰሜን ዋልታ አካባቢ በተፈለገው ጊዜ ቀዝቃዛ አየር በመፍጠር አሜሪካን በየጊዜው የሚጎዷትን ታላላቅ የአየር ማእበሎች (hurricanes) ለመቀነስ እንደሚቻል ቴክኖሎጂውን በቅርብ የሚያውቁ ባለሙያዎች ስለ ጉዳዩ ያላቸውን ፍራቻ በአደባባይ መዘገብ ጀምረዋል። በእንግሊዝ የሚገኘው የኤግዘተር ዩኒቨርሲቲ ዋነኛ ተመራማሪ የሆኑት አንቶኒ ጆንስ የተባሉት ባለሙያ Nature Communications በሚባለው መጽሔት ላይ እንዳሰፈሩት ይህ ቴክኖሎጂ በሰሜናዊው የምድር ግማሽ ስራ ላይ ሲውል በአሜሪካና በካሪቢያን አገሮች አካባቢ የሚከሰቱትንና ብዙ ጥፋት የሚያደርሱትን የአየር ማእበሎች ሲቀንስ፣ በሌላ ወገን ደግሞ በአፍሪካ የሳሄል አካባቢ ከፍተኛ ድርቅን ያስከትላል። ቴክኖሎጂው በደቡባዊው ክፍለ ዓለም በስራ ላይ ቢውል ደግሞ አሜሪካንና የካሪቢያን አገሮችን በየጊዜው የሚጎዱትን የአየር ማእበሎች እንደሚያባብስም ተደርሶበታል ይላል ይኸው ከላይ የተጠቀሰው ሪፖርት። በመቀጠልም ሪፖርቱ ገንዘቡና ቴክኖሎጂው ያላቸው አገሮች ወይም ድርጅቶች ይህን ቴክኖሎጂ  በፈለጉት ጊዜና ቦታ ስራ ላይ እንዳያውሉት የሚከለክላቸው ነገር ስለሌለ በአፍሪካና ሌሎችም አካባቢዎች ትልቅ ጥፋትን ሊያስከትል እንደሚችል ፍርሃቱን ገልጿል።

ቴክኖሎጂ በአግባቡ ስራ ላይ ሲውል  ለሰው ዘር ሁሉ ገንቢ የሆነ የእድገት አስተዋጽኦ ማድረግ መቻሉ የማያሻማ ቢሆንም፣ ኃያላኑና ባለጸጎቹ አገሮች ብቻ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ እንደ ሰው ሰራሽ የአየር ንብረት መቀያየሪያ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ግን በኤኮኖሚና በቴክኖሎጂ ገና እያደጉ ባሉት እንደ አፍሪካ ያሉ የዓለም ክፍሎች ብዙ ህዝብን ሊጨርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ሊፈጥሩ መቻላቸው ያልተረጋገጠየሴራ ወሬ ወይም “conspiracy theory” ነው ከመባል አልፎ በአደባባይ መነገር መጀመሩ መጽሐፍ ቅዱስ ከብዙ ሺ ዓመታት በፊት በመጨረሻው ዘመን በምድር ላይ ይከሰታሉ በማለት ያስቀመጠልን ማስጠንቀቂያዎች ምን ያህል እውነት እንደሆኑ ያስረዳል። ለምሳሌ ያህል በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 24 ቁጥር 7 ላይ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፣ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፣ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው ይላል።”  በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ በግልጽና በዝርዝር እንደተቀመጠው በሰባቱ ዓመት ታላቁ የመከራ ዘመን ጌታ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ንስሐ ለመመለስ ታላላቅ መቅሰፍቶች በምድር ላይ እንዲፈጸሙ ይፈቅዳል። ነገር ግን ዛሬ በአደባባይ በግልጽ እየተዘገቡ ያሉትን ዜናዎች ልብ ብለን ካዳመጥን የሰው ልጅ ራሱ ደግሞ በሰራው ቴክኖሎጂ በራስ ወዳድነት፣ በማን አለብኝነትና በግድ የለሽነት የተፈጥሮን ሚዛን በማቃወስ ረሃብን፣ ቸነፈርን እና የምድር መናወጥንም በሰፊው ሊፈጥር መቻሉን እናስተውላለን።


የሰማይና የምድር እንዲሁም የሰው ዘር ሁሉ ፈጣሪና ባለቤት እግዚአብሔር ነው። የሰው ልጅ የተሰጠችውን ይህችን ምድርና ከባቢ አየርዋን በመስማማትና በመተሳሰብ መጠቀም ሲገባው፣ በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸውና በኃይላቸው በመመካት ህዝብን የሚፈጅ፣ የሚያስርብና ለጥፋት የሚዳርግ ራስ ወዳድና እኩይ ተግባሮችን በተፈጥሮ ላይ የሚፈጽሙ ሁሉ በእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ለስራቸው መልስ ይሰጡበታል። ለዚህ ነው በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 11 ቁጥር 18 ላይ “ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” ተብሎ የተጻፈው። እያንዳንዳችን መረዳቱና እድሉ ያለን ክርስቲያኖች ለሐገር መሪዎች በመጸለይ እና ስንችል ደግሞ በዚህ መልእክት ላይ እንደ ተገለጠው ያሉ የእግዚአብሔርን ሥራ የሚፈታተኑና በህዝብ ላይ እልቂት ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን መግለጥ፣ መቃወምና በጊዜው እርምት እንዲደረግ ማሳሰብ ግዴታችን ነው። ዓይናችንን ከፍተን የሚካሄደውን እንመልከት፣ ያለነው በዘመኑ መጨረሻ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል፣ እስከዚያ ግን የክፉውን ስራ ሁሉ በመቃወምና የክርስቶስን የወንጌሉን ብርሃን በማብራት እንጽና። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ከአስራ አምስት ሺህ የሚበልጡ የዓለማችን ሳይንቲስቶች የሰው ዘርና ምድራችን ወደ መጥፊያቸው እጅግ ተቃርበዋል በማለት አስጠነቀቁ ተባለ

“በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱ ድምጽ የተነሳ እያመነቱ ይጨነቃሉ፣ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሳ ይደክማሉ፣ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሱ።” ሉቃስ 21፡25-28
በተያያዘው ሪፖርት ላይ እንደምታነቡትና በትናንትናው መልእክቴም እንደ ገለጽሁት፣ ዓለማችን በብዙ ምጦች ተይዛለች የሚለው ግምገማ ከትንቢት ተከታታዮች፣ አስፈሪ ዜና ማቅረብና የሴራ ወሬን ማናፈስ ይወዳሉ ከሚባሉ ምንጮች የመጣ ሳይሆን በምድራችን ላይ ታዋቂ ናቸው የሚባሉ ከ15 ሺ በላይ ሳይንቲስቶችም የሚስማሙበት ነው። በምድር ዙሪያ ያለው የ ኦዞን ልባስ እጅግ በመሳሳቱ ምድራችን ለአደገኛ ጨረርና ጥፋት ተጋልጣለች ሲሉ የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያቸውን ከዛሬ 25 ዓመት በፊት ለሰው ዘር ሁሉ የጻፉት የእነዚህ ሳይንቲስቶች ህብረት ዛሬ ግን  ምድራችን ከመቼውም የበለጠ እጅግ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ወድቃለች፣ የሰው ዘር፣ እንስሳትና በአጠቃላይም በምድራችን ላይ ያለ ህይወት በሙሉ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጦአል ይላሉ። ከ184 አገሮች የተውጣጡት እነዚህ 15384 ሳይንቲስቶች ለሰው ዘር ሁሉ የጻፉት ደብዳቤ ምድርን በጥፋት አፋፍ ላይ ጥለዋታል ከሚላቸው ነገሮች መካከል ባለፉት 25 ዓመታት የሰው ዘር ብዛት በ35 ከመቶ ማደጉ፣ ሰዎች የሚጠቀሙበት ንጹህ ውሃ መጠን 26 በመቶ መቀነሱ፣ በብክለትና በኦክስጂን እጥረት ምክንያት ህይወት ሊኖርባቸው የማይችለው የውቅያኖስና የባህር አካሎች መጠን በ75 ከመቶ ማደጉ፣ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ደን በመመንጠሩና በሌሎችም ሰው ሰራሽ ጥፋቶች የምድር አየር ንብረት ሙቀት እያሻቀበ መሄዱና፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ የአእዋፍ፣ አሳዎች እንዲሁም ሌሎች እንስሳት ቁጥር በ29 ከመቶ መቀነሱ ነው። የእነዚህን ሁኔታዎች አስከፊነት ለመረዳት በፉኩሺማ ጃፓን በ2014 ዓም የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀትና ሱናሚ ተከትሎ የተፈጠረው የኑክሊየር ኃይል ማመንጫ አደጋ ባለፉት ስድስት ዓመታት ተኩል ወደ ፓሲፊክ ውቅያኖስና ወደ ምድር ከባቢ አየር እየለቀቀው ያለ ከፍተኛ የኑክሊየር ጨረር የፈጠረውን አደጋ ልብ ማለት ያስፈልጋል። አደጋውን ለማቆም ይህን ወይም ያንን እያደረግን ነው የሚለው ዜና በተከታታይ ቢሰማም፣ በጉዳዩ ጥልቅ እውቀትና መረጃ ያላቸው ሰዎች ግን ጥፋቱ እንደ ቀጠለና ሊቆምም እንደማይችል ከመናገር ወደ ኋላ አላሉም። ከነዚህ ባለሙያዎች አንዳንዶቹ እንደሚያቀርቡት የፉኩሺማው የኑክሊየር ኃይል ማመንጫ ፍንዳታ በዓለማችን ላይ እየለቀቀው ያለው ገዳይ ጨረር በ1945 ዓም በሂሮሺማ ጃፓን ላይ አሜሪካ የጣለችው የአቶሚክ ቦምብ ከለቀቀው ጨረር በ15000 (አስራ አምስት ሺህ) እጥፍ የከፋ ነው ይላሉ። ይህ ጨረር በቀጥታ የሚገባው ወደ ውቅያኖስችና ባህሮች እንዲሁም (አነስ ባለ መጠን) ወደ ከባቢ አየር በመሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የባህር እንስሳት ላለፉት ስድስ ተኩል ዓመታት እያለቁ ናቸው። እነዚህ ሳይንቲስቶች ያልጠቀሷቸው፣ ነገር ግን የሰውን ዘርና ምድራችንን ጥፋት በር ላይ ያደረሱአት ሌሎችም እጅግ ብዙ ነገሮች አሉ። የተፈጸመው ጥፋት ሳይበቃን ዛሬ ደግሞ ባለጸጎቹ አገሮች ምድርን ብዙ መቶ ጊዜ ደጋግሞ ሊያጠፋ የሚችል አዳዲስ መሳሪያ በመስራት እየተሽቀዳደሙ ናቸው። የዚህ ሁሉ ክፋትና ፍጥረትን እያጠፋ ያለው ዋነኛው መርዝ ግን ኃጢዓትና እርሱም ያመጣው በእግዚአብሔር ላይ ዓመጽ፣ ራስ ወዳድነት፣ ገንዘብ ወዳድነት፣ ጥላቻ፣ ከገደብ ያለፈ ምቾት ናቸው። የምድር አዋቂዎች፣ ኃይለኞችና መሪዎች አሁንም ቢሆን ያንዣበበውን አደጋ ለመለስ የሚያስችል እውቀቱም፣ ችሎታውም የላቸውም። ብዙም ቀን ውሎ ሳያድር ይህን የሳይንቲስቶችን ማስጠቀቂያና ሌሎችም አስፈሪ ዜናዎችን ተከትሎ፣ “የገጠመንን ችግር ሁሉ በራሳችን ለመፍታት ስለማንችል፣ ከሌላ ዓለም የመጡ ሌሎች ልዩ ፍጥረታት (ETs, Aliens, Martians ወዘተ) እንዲረዱን እርዳታ ጠይቀን፣ እነርሱም ስለ ተስማሙ ውል ገብተናል። መሪያችንም እገሌ ይባላል” የሚል ዜና ቢመጣ ልንደነቅ አይገባም። ምክንያቱም ይህ ሁሉ እንደሚሆንና፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመመለሱ በፊት ምድርን ሁሉ የሚገዛ ሃሳዊ መሲህ (ሃሰተኛው ክርስቶስ) እንደሚገለጽ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። “በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፣ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዓመጸኛ ይገለጻል። ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኛ ድንቆችም በመጻም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሰራር ነው።” 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡8-10 የዚህ መልእክት ዓላማዎች ሶስት ናቸው፤ 1ኛ) ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል የዘለዓለምን ህይወት ተስፋ ያላገኙ ሁሉ በወንጌሉ የምስራች እንዲያምኑ ለመጋበዝ 2) በክርስቶስ የሚያምኑ ወገኖች ሁሉ በዓለማችን ላይ እየተካሄዱ ያሉትን ትልልቅ ነገሮች በመቃኘትና በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መነጽር በመመርመር ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ራሳቸውንና ሌሎችንም እንዲያዘጋጁ ለማነቃቃት 3) ምንም እንኳን የምናየውና የምንሰማው ሁሉ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢመስልም፣ ክርስቲያኖች ሁሉ ፍጥረትን ሁሉ በእጁ የያዘው እግዚአብሔር ዛሬም በዙፋኑ ላይ እንዳለና ለሰው ዘርም ሆነ ለፍጥረት ሁሉ እኛ ከምናስበው የበለጠ ተስፋና እቅድ እንዳለው በማወቅ ያለ ፍርሃትና ያለ ስጋት መኖር እንደምንችል ለማሳሰብ ነው። ዓለሙን ሁሉ እጅግ ስለወደደ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም በመላክና ስለኛ ኃጢዓት በመስቀል ላይ እንዲሞት በማድረግ ለእኛ ያለውን ፍቅር ገልጾአል። ያ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በዘመኑ መጨረሻ ዳግም ተመልሶ ይመጣል። ይህ ሁሉ የምናየውና የምንሰማው የእርሱ ዳግም ምጽዓት የምጥ ጣር መጀመሪያ ይመስላል። ጌታ ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ያልተቀበልን ሁሉ እርሱን አምነን የመዳን ቀን ዛሬ ነው። በእርሱ ለምናምንም ደግሞ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መዘጃጋው ሰዓት አሁን ነው። እንደ አምስቱ ሰነፎች ቆነጃጅት በሩ እንዳይዘጋብን ቶሎ እንንቃ፣ መቅረዛችንን በዘይት እንሙላና ሙሽራውን ለመቀበል እንዘጋጅ።
“በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱ ድምጽ የተነሳ እያመነቱ ይጨነቃሉ፣ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሳ ይደክማሉ፣ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሱ።” ሉቃስ 21፡25-28

ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ

በዓለማችን ላይ ይህ ሁሉ የምድር መናወጥ፣ አለመረጋጋት፣ መከራና ትርምስ ሲከሰት የዘለዓለም ሕይወት ኢንሹራንስ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ችላ ብለነው ይሆን?

በዓለማችን ላይ ይህ ሁሉ የምድር መናወጥ፣ አለመረጋጋት፣ መከራና ትርምስ ሲከሰት የዘለዓለም ሕይወት ኢንሹራንስ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ችላ ብለነው ይሆን?  https://www.rt.com/news/409633-iran-iraq-earthquake-updates/

ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 86 የሚሆኑ የምድር መናወጦች በተለያዩ የዓለም ማዕዘናት ተመዝግበዋል። ከነዚህ ውስጥ ይህ ጽሁፍ እስከተጻፈበት ሰዓት ድረስ 100 በላይ ሰዎችን የገደለውና በንብረት ላይ ትልቅ አደጋን ያስከተለው በምስራቃዊው የኢራቅ ክፍልና በኢራን ድንበር አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። ይህ የፈረንጆቹ ዓመት ከተጀመረ ጀምሮ ብቻ 110 በላይ የሚሆኑ ዋና ዋና መንቀጥቀጦች እንደተከሰቱ  የምድር መንቀጥቀጥን የሚያጠናውና የሚከታተለው የአሜሪካው መንግስት ቢሮ (USGS) መረጃዎች ያሳያሉ። በምድራችን ላይ ባሉት ትልልቅ ውቅያኖሶች፣ ባህሮችና ሀይቆች ውስጥ ያሉ በብዙ የሚቆጠሩ ትልልቅና ትንንሽ ፍጥረታት በየእለቱ እያለቁ መሆናቸውም በተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይዘገባል። ለምሳሌ ያህል http://www.end-times-prophecy.org የተሰኘውን ድረ ገጽ መጎብኘት ዝርዝር መረጃዎችን ይሰጣል። ታላላቅ የሚባሉና በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ እንደ ከዋክብት የሚታዩ የሆሊውድ ተዋናዮች፣ ዲሬክተሮች፣ ዘፋኞችና፣ በፊልም ኢንዱስትሪው ዋና ዋና የሚባሉ ብዙ ሰዎች በታዋቂ አዋቂ ተዋናዮችና ነፍስ ባላወቁ ልጆችም ላይ ሳይቀር የገንዘብ ስልጣናቸውን በመጠቀም ሲያደርሱ የኖሩት ወሲባዊ ጥቃት ባለፉት ሁለት ወራት በከፍተኛ ቁጥር እየተጋለጠ መጥቶአል። ከላይ ለሚያዩት መልካም የሚመስለውና በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች የሚያዩአቸውን ፊልሞች፣ ቲያትሮችና የቴሌቪዝን መዝናኛዎችን የሚያመርተው ይህ ኢንዱስትሪ ጉድ በምእራባውያኑ መገናኛ ብዙኃን መዘገብ እንደሚገባው ሳይዘገብ እስከ ዛሬ ታፍኖ ቢቆይም፣ እጅግ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ ኮረዶችና ጎልማሶች በአሰሪዎቻቸውና ባለጸጎች የኢንዱስትሪው ዋናዎች የደረሰባቸውን መዋረድና በደል በአደባባይ እያወጡ ነው። የተሻለ እድል፣ ስራ፣ ገንዘብ፣ ዝናና ታዋቂነትን ታገኛላችሁ በሚል ማታለያ ከየቤተሰቦቻቸው ተታልለው ወደ የፊልሙ ኢንዱስትሪ ዋና ዋና መናኸሪያ ከተማዎች ከሄዱ በኋላ የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ጠፍተው የቀሩም እጅግ ብዙ እንደሆነ ብዙ የነጻው መገናኛ ብዙኃንና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ያመለክታሉ።  የዲሞክራሲ፣ የሰላምና የብልጽግና ዋና ምሳሌ ነኝ በምትለ አሜሪካ እየተፈጸሙ ያሉት የሽብር ጥቃቶች፣ አለመረጋጋትና አምልኮ ስፍራዎችን እንኳን ሳይቀር ሰላማዊ ህዝብ የፈጁ ግድያዎች ብዙ አሜሪካውያንን እና ምእራባውያንን "ዓለም ወዴት እየሄደች ነው" በሚል ጥያቄና ፍርሃት ውስጥ ከቷል።
በነዳጅ ሃብቷ እጅግ ሃብታም የሆነችውና በንጉስ የምትመራው ሳውዲ አረቢያ የአረብ ጸደይ ተብሎ መንግስታትን ካፈራረሰው ቀውስ ብታመልጥም ዛሬ ደግሞ በተራዋ በልዑላኑ ቤተሰብ መካከል በተፈጠረ ውዝግብ ቀውስ ውስጥ እየገባች መሆኑ ደግሞ ከሰሞኑ ትልልቅ ዜናዎች አንዱ ነው። ይህ ቀውስ ደግሞ አገሪቱ ከኢራን ጋር ካላት ፉክክርና በየመን ስታካሂ  ከቆየችው ጦርነት እንዲሁን በሊባኖስ፣ በኢራቅና በሶሪያ ከታየው የኢራን ተጽእኖ መስፋፋት ጋር የተያያዘ በመሆኑ አካባቢውን በሙሉ ወደ ጦርነት እሳት ሊያስገባ ይችላል በማለት ብዙ አዋቂዎች ያስጠነቅቃሉ። በአሜሪካና በሩሲያ መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መሄዱም ብዙዎችን እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ ከሆነ ውሎ አድሮአል። የአሜሪካና የአጋሮቿ የምእራብ አውሮፓ አገሮች ጦር ለሩሲያ አዋሳኝ በሆኑ የምስራቅ አውሮፓ አገሮች መስፈር፣ ሰሜን ኮሪያ የኑክሊየር ቦምብና ግዛቶቼን ሊመቱ የሚችሉ ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች የማምረት እርምጃዋን ካላቆመች በጦርነት አፈራርሳታለሁ በማለት አሜሪካ መዛቷ እና ከፍተኛ ብዛት ያለውን ጦሯን ወደ አካባቢው ማሰማራቷ፣ የቻይናን የኤኮሚና ወታደራዊ ግስጋሴ ለመግታት በማለት አሜሪካ በደቡባዊው የቻይና ባህር አካባቢ ከቻይና ጋር የገባችው እሰጥ አገባ፣ ሶሪያንና ሊባኖስን እረዳለሁ በሚል ሰበብ ኢራን በድንበሮቼ አካባቢ ያላትን ተጽእኖ ስለጨመረች በሶሪያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት እስራኤል መዛቷ 3ኛው የዓለም ጦርነት እንዲነሳ ሊያደርጉ የሚችሉትን ሁኔታዎች እያባባሰ መምጣቱ ብዙዎች አዋቂዎችንና መሪዎችን እጅግ ያሳሰበ ነገር ነው። ከምድር ላይ ጠፍተው ከነበሩ ብዙ ህዝብ ከሚፈጁ ወረርሽኝ በሽታዎች መካከል አንዱ የሆነው ጥቁሩ መቅሰፍት (black plague) በማደጋስካር ብዙ ሰዎችን እየገደለ ነው፣ በፍጥነት በመሰራጨትም በዓለም ላይ ብዙ ህዝብን ሊገድል ይችላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቆአል። ይህም ሁሉ ሳይበቃ ታዋዊ የሆኑት የፊዚክስ ፕሮፌሰር ስቲቨን ሆውኪንግ እና የእንግሊዙ ልዑል ዊሊያም የዓለም ህዝብ ቁጥር እጅግ ስለበዛ የምድርን የህይወትና የአየር ንብረት ሚዛን ያናጋል በፍጥረታትም ላይ ቀውስ ይፈጥራል እንዳሉ ተዘግቧል። ፕሮፌሰር ሆውኪንግ ከዚህም በማለፍ የሰው ዘር ከልክ በላይ በሆነ መንገድ የምድርን የኃይል ምንጮች በመጠቀም በሚቀጥሉት 600 ዓመታት ምድርን በእሳት ያቃጥላታል ሲሉ ፍርሃታቸውን ገልጸዋል። ለዚህም መድሃኒቱ የሰው ዘር ምድርን የምትመስል ሌላ ዓለም በህዋ ውስጥ ፈልጎ ወደዚያ መሄድ መጀመር ነው ሲሉ መፍትሄ ያሉትን ሰንዝረዋል።  በእስራኤል የሚገኙ ታዋቂ ራባይ (መምህር) ደግሞ የመሲሁ ማንነት በርቡ ለአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች በህልም ይገለጻል ሲሉ ተናግረዋል። እርሳቸው የሚሉ መሲህ ደግሞ ክርስቲያኖች የምንከተለው ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም።
አሁን ያለው የዓለም ሥርዓት መጨረሻ ሲቃረብ በምድር ላይ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ የምድር መናወጥ፣ ጦርነትና የጦርነት ወሬ፣ ህዝብ በህዝብ መንግስት ደግሞ በመንግስት ላይ መነሳት እንደሚበዛ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ሌሎችንም ብዙ ምልክቶች እንደሚከሰቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሃዋርያትና ነቢያት አመልክተዋል። ምናልባት ይህ በዘመናችን የምናየው ነገር ሁሉ በወንጌል የተገለጸው የመጨረሻው ዘመን የምጥ ጣር መጀመሪያ ይሆን?  ከሆነስ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘለዓለም ቤት እንዳለን አረጋግጠን ይሆን። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሰው ልጅ የዚህ ዓለም ህይወት በጊዜው ያበቃል። ሰው በክርስቶስ ቢያምንም ባያምንም ከሞት ባሻገር የዘለዓለም ህይወት አለ። በክርስቶስ የሚያምን ያን ዘለዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ይኖራል። ክርስቶስ የሌለው ደግሞ ወደ ዘለዓለም ጨለማ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ይሄዳል። እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው ስለወደደ የኃጢዓታችንን እዳ በልጁ የመስቀል ሞት ከፍሎ ሁላችንንም ወደ መንግስቱ ጋብዞናል። የመዳን ቀን ዛሬ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛችን ለማድረግ ዛሬ ነገ አንበል። በክርስቶስ የምናምን ደግሞ እርምጃችን ከእርሱ ጋር እናስተካክል። በዓለማችን ላይ የሚካሄደውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚያየው ማየት እንድንችልና ልባችንን ወደ እርሱ እንድናቀና የአብርሃም፣ የይስሃቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።


ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...