የመለከት ድምጽ ቁጥር 6

የመጽሄቷን PDF ኮፒ ዳውንሎድ በማድረግ ማንበብ ይቻላል፤ ይህ መልእክት ለማይደርሳቸውም እንድታደርሱ በትህትና እጠይቃለሁ።
በዚህች እትም ውስጥ የሚከተሉት ትምህርቶችና ሃሳቦች እንዲሁም
ደግሞ ካለፈው የቀጠለው የዶ/ር ዘመድኩን ተሻለ የህይወት ምስክርነት ክፍል አራት ቀርበዋል።
1)      1)  በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተገለጠችው ታላቂቱ ጋለሞታ፣ የምስጢር ባቢሎን ማን ትሆን?
2    2)    መጽሐፍ ቅዱስ “ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ”፣“የዓመጽ ሰው”፣ “የጥፋት ልጅ” የሚለው ማንን ነው?
      3)    የሃሰተኛው ክርስቶስ ምልክት ወይም 666 የሚባለው ምን ሊሆን ይችላል? 
4    4)  በየእለቱ በታላቅ ፍጥነት እየበዛና እየተራቀቀ የሚሄደው ቴክኖሎጂ እና የመጨረሻው ዘመን የሚገናኙበት ምስጢር ይኖር ይሆን?
ለነዚህና ሌሎችም ተያያዥ ጥያቄዎች በአጭሩ መልስ ለመስጠት ተሞክሯል። ባለፉት ሁለት ሺ ዓመታት በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ተመራማሪዎችና ጸሐፊዎች የሰጧቸውን ግምገማዎች እና ትንተናዎች በመመርኮዝና በዘመናችን የተደረጉና እየተደረጉ ካሉ ጥናቶች ሰፋ ያለ ተቀባይነት ያላቸው ሃሳቦችና መረጃዎችም ቀርበዋል።
ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል። አይዘገይምም፤ ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፥ ወደኋላም ቢያፈገፍግ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እብራውያን 10፡37
ማራናታ !! አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!!

ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ

የሐሰተኛው ክርስቶስና የምስጢሯ ባቢሎን ማንነት የሚገለጽበት ጊዜ ደርሶ ይሆን?

ሐሰተኛው ክርስቶስና የምስጢሯ ባቢሎን


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ፍጻሜ፣ ስለ ዳግም ምጽዓቱ፣ ስለሚመጣው ፍርድና ስለ እግዚአብሔር መንግስት መገለጥ ለሐዋርያው ዮሐንስ የገለጻቸውን ብዙ ትንቢቶች በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ እናነባለን። ባለፉት ሁለት ሺ ዓመታት ብዙ የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ መሪዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ምሁራንን፣ የታሪክ አዋቂዎች እና ታዋቂ ክርስቲያን ሳይንቲስቶችም ሳይቀሩ እነዚህን ትንቢቶች ከማንኛውም መጽሐፍ በበለጠ ሲመረምሩ፣ ሲተነትኑ እና ለመረዳት ሲሞክሩ ኖረዋል። ከነዚህ ትንቢቶች ውስጥ የተፈጸሙ ብዙ ቢኖሩም አብዛኛዎቹ ግን ገና የሚፈጸሙ ናቸው። ከጌታ መምጣት አስቀድሞ ከሚሆኑት ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ አንዱ የሃሰተኛው ክርስቶስ መገለጽ ነው። በዮሐንስ ራዕይ ላይ እና በትንቢተ ዳንኤል ሰባት ራሶች እና አስር ቀንዶች ያሉት አውሬ ተብሎ የተጠቀሰው ሃሰተኛው መሲህ የሚገለጸው ደግሞ ታላቂቱ ባቢሎን እና የምስጢር ባቢሎን ተብላ ከምትጠራ ሴት ጋር ተያይዞ እንደሆነ በዮሐንስ ራዕይ ምእራፍ 17 እና 18 ላይ እንመለከታለን። በነዚህ ምእራፎች ላይ የተጠቀሰችውን ታላቂቱ ጋለሞታ ማንነት በመተንተን ባለፉት ብዙ መቶ ዓመታት የተጻፉና የትንቢት ትንተናዎች እንደሚያመለክቱት ታዲያ “የምስጢር ባቢሎን” ወይም “ጋለሞታ” የምትባለው በመጨረሻው ዘመን በምድር ላይ ተንሰራፍታና በአደባባይ ክርስትና መሰል ሀይማኖትንና ምድራዊ ፖለቲካን በመደባለቅ ሰማያዊውንና ምድራዊውን ነገር ሁሉ ከአውሬው ጋር በመተባበር ልትገዛ የምትነሳ ዓለም አቀፍ “የሃይማኖት” ድርጅት እንደምትሆን ሲያመለክቱ ከርመዋል። ከነዚህም ብዙዎቹ የዚህች ጋለሞታ ድርጅት ዋነኛው ማእከል በሮም የሚገኘው የካቶሊክ ቤ/ክ ዋና መስሪያ ቤትና ከሱም ጋር የተያያዙ ሌሎች ድርጅቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ እጅግ ብዙ ጸሃፊዎች በቅርቡም ሆነ ከረጅም ዘመናት በፊት በሰፊው ጽፈውበታል። የነዚህ ጸሃፊዎች ግምት ከእውነቱ ብዙም የራቀ እንዳልሆነ ደግሞ ከራስዋ ከቫቲካን የወጡ እንደ FATHER ማላኪ ማርቲን ያሉ የካቶሊክ ምሁራንና ከፍተኛ የሃይማኖት መሪዎች በሰፊው የጻፉበት ጉዳይ ነው። ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት እንኳን ከተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መዋቅር ጋር የጠበቀ የውስጥ ግንኙነት ያላቸው እንደ ሊዮ ሊዮን ዛጋሚ ያሉ ጸሃፊዎች የሮሟ ቫቲካን ሰዎች እንደሚገምቱት በቅንነት እግዚአብሔርን የሚያመልኩ የብዙ ካቶሊክ ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ራስ ከመሆንዋ ይልቅ በብዙ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካና ከዚያም ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያላት ድርጅት እንደሆነች አስረድተዋል። እዚህ ጋ መገንዘብ ያለብን አንድ እውነት አለ። ብዙዎቹ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ይህንን በሮም ያለችው ዋና ድርጅታቸው አለችበት የሚባለውን ነገር ሁሉ ያውቃሉ ወይም በዚያ ይስማማሉ ማለት አይደለም። ይህ ነገር የሚከነክናቸው አንዳንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምሁራንና መሪዎች ደግሞ በግልጽም ሆነ በስውር የቫቲካንን አሰራር በመቃወምና በማጋለጥ ምእመናኖቻቸውን እያስተማሩ ይገኛሉ። በቅርብ ጊዜ እንኳን በአሜሪካ የሚገኙ እንደዚህ ያሉ ካቶሊኮች፣ አሁን ቫቲካንን የሚመሩት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የበፊቱንና በህይወት እስካሁን ያሉትን ቤኔዲክት 16ኛውን በመጋፋት አሁን ከስልጣን በወረደው በአሜሪካው መንግስት ድጋፍ ጳጳስነቱን ይዘዋል የሚለው ጥርጣሬና የአሜሪካም መንግስት በዚህ ጉዳይ እጁን አስገብቶ ከሆነ እንዲጣራ አዲሱን የአሜሪካ መንግስት ፕረደንት በደብዳቤ ጠይቀዋል።

በዚህ ዜና ላይ እንደምናየው ደግሞ  ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ 27ቱ የአውሮፓ ህብረት መሪዎች እንዴት አድርገው ህብረታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ብቻ ሳይሆን፣ ከመንግስት በላይ መንግስት የሆነው የአውሮፓው ህብረት አያስፈልገንም የሚሉ በየአገሩ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም በማውገዝ፣ የሚከተሉት “ለአገሮቻችን ህዝቦች ብቻ እናስባለን” የሚለውን መመሪያቸውን አደገኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አንድ ጊዜ ክርስቲያን የሆኑትንም ሆነ ያልሆኑትን ስደተኞች እግር በማጠብ የክርስቶስን ምሳሌ የተከተሉ ሆነው ለመቅረብ የሚሞክሩት እኒህ ሊቀ ጳጳስ ሌላ ጊዜ ደግሞ አገሮች የትኛውን የፖለቲካ መስመር መከተል እንዳለባቸው ዲስኩር ያደርጋሉ። ባለፈው ዓመት የአሚሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በሚካሄድበት ጊዜ በሜክሲኮ በመገኘት፣ በአገሮች መካከል አጥር ለማጠር የሚፈልግ መሪ ክርስቲያን አይደለም ብለው በመናገር ዛሬ በአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ከተቀመጡት ዶናልድ ትረምፕ ጋር እሰጥ አገባ ገብተው እንደሆነ አይዘነጋም። እንዲሁም ደግሞ በእስራኤልና በፍልስጥኤማውያን መካከል ላለው ስር የሰደደ ጠብ መፍትሔ አመጣለሁ ብለው እስራኤልንና ፍልስጥኤማውያን የሚኖሩባቸውን የምእራብ ዮርዳኖስ ክልልና የቀረውን የእስራኤልን ግዛት ጎብኝተዋል፣ የሁለቱን ወገን መሪዎችም ቫቲካን ድረስ ጋብዘው ጸሎት አደረግን ብለዋል። በእውነትም በቫቲካን ባደረጉት ስብሰባ እሳቸው የክርስቲያን ተወካይ፣ የእስራኤሉ ፕሬዝደንት የአይሁድን እምነት ወክለውና የፍልስጥኤሙ አስተዳደር ፕሬዝደንት ደግሞ በአብዛኛው እስላም የሆነውን ህዝባቸውን ወክለው ለሰላም ጸልየው ከሆነ ጳጳሱ ትልቅ ስራን ሰርተዋል ማለት ነው። ብዙዎች ግን ጸሎቱ የመሸፈኛ ነው እንጂ ያካሄዱት የፖለቲካ ስብሰባ ነው ሲሉ ተችተዋል። ብዙ ታዛቢዎች የሃይማኖት አባቶች የተጣሉን ማስታረቃቸውና ህዝብን ለሰላም ማስተባበራቸው እጅግ መልካምና ተገቢ ተግባር መሆኑን እና ይህም ደግሞ በቫቲካን አለመጀመሩን ያመለክታሉ። ብዙ ጸሃፊዎችንና የትንቢት ምሁራንን የሚከነክነው ግን ይህች ቤተ ክርስቲያን ነኝ ብላ የምትጠራው ቫቲካን ለምን በአለም አቀፍ ደረጃና በየአገራቱም ፖለቲካ ውስጥ በመግባት ይህኛው ጥሩ ነው፣ ያኛው መሆን የለበትም በማለት የፖለቲካ ወገንተኝነት ውስጥ መዘፈቋን ነው። ከዚህም በላይ ብዙዎችን የሚያስገርመው ደግሞ መንግስትና ሃይማኖት ለየብቻው እንደሆነ እናምናለን የሚሉት የሰለጠኑት የአውሮፓ መንግስታት (እና ሌሎችም) ቫቲካን አለቃቸው እንደሆነች ያህል በመቀበል እኒህ ጳጳስና ከእርሳቸውም በፊት እንደ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛው ያሉ ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት  የሚናገሩአቸውን ነገሮችና የፖሊሲ መመሪያዎች የሚቀበሉ መምሰላቸው ነው። በመሰረቱ የቤተ ክርስቲያንን ስራ የክርስቶስን ወንጌል መስበክ፣ ምእመናንን ለእግዚአብሔር መንግስት ማዘጋጀትና በዚህ ምድር ህይወታቸው ደግሞ  ለየአገሮቻቸው መልካም ዜጎች እንዲሆኑ መርዳት ነው። ምእመናን በየግላቸው የራሳቸው የፖለቲካ፣ የፍልስፍናና ሌሎችም አስተያየቶች ሊኖሩአቸው ቢችሉም፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ነኝ የምትል ድርጅት ግን ከራሷ ምእመናንም አልፋ የብዙ አገሮች መሪዎችንና ህዝቦችን ይህ የፖለቲካ መንገድ ልክ ነው፣ ያኛው አደገኛ ነው በማለት ያለቦታዋ ስትዳክር መገኘቷ መንፈሳዊ አላማዋን የሳተች ያደርጋታል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ለዚህም ይመስላል ብዙ የትንቢት ምሁራንና የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ቫቲካን የምድር ጋለሞታዎች ሁሉ እናት፣ የምስጢር ባቢሎን የተባለችው ሴት ሳትሆን አትቀርም ወደሚል ድምዳሜ የደረሱት። የማይገለት የተከደነ፣ የማይታወቅም የተሰወረ የለምና ዛሬ ምስጢር የሚመስለው ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲመጣ ግልጽ ይሆናል። ባለፉት አስር በሚበልጡ ዓመታት ብዙ የዚህች ቤተ ክርስቲያን (ወይም ድርጅት) ቄሶችና የተለያዩ ባለስልጣናት በሰዶማዊነት፣ ህጻናትን በመድፈርና በሌሎችም አሳፋሪ ጉዳዮች ሲታሙና ሲወቀሱ መኖራቸው በዜና አውታራት ሁሉ ሲዘገብ የነበረ ነው። ታዲያ የገዛ ቤታቸውን እንኳን ገና በሚገባ ያላጸዱት እኒህ የቫቲካን መሪ መንፈሳዊና ሞራላዊ ስልጣኑን ከየት አግኝተው ይሆን የ27ቱን የአውሮፓ መሪዎች በዚህ ሂዱ፣ በዚያ አትሂዱ ለማለት የቃጡት? ባለፉት መልእክቶቼ እንዳልኩት ሁሉ፣ እንደዚህ ባለ ጊዜ የእውነተኛ ክርስቲያን ድርሻና ሃላፊነት እኒህ መሪና ሌሎችም የእምነትም ሆኑ የፖለቲካ መሪዎች የእውነትና የጥበብ ሁሉ ምሰሶ የሆነውን እግዚአብሔርን በመፍራትና ንስሃ በመግባት በክርስቶስ በእውነት እንዲያምኑና ዓለሙን ሁሉ ከሚያስተው ከዲያብሎስ መንፈስ እንዲጠበቁ መጸለይ ነው። እድሉን ስናገኝም እውነተኛውን የክርስቶስን ወንጌል ከመመስከር ወደኋላ ማለት የለብንም። ይህን ልናደርግ የሚያስችለንን ጸጋና የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እግዚአብሔር ያብዛልን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ሁል ጊዜ ትጉ። ሉቃስ 21፡36



በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሶቪየት ህብረትና ሌሎችም ሶሻሊስት የነበሩ የምስራቅ አውሮፓ አገሮች ሲፈራርሱና የምእራባውያኑን የኤኮኖሚና የፖለቲካ ስርዓት መከተል ሲጀምሩ፣ ቀዝቃዛው ጦርነት አበቃ፣ ከእንግዲህ በኋላ የዓለም መንግስታት በተሻለ መንገድ ይተባበራሉ፣ የመሳሪያ እሽቅድምድም አይኖርም ተብሎ ነበር። ከዚህም የተነሳ ሃብታሞቹ አገሮችና መንግስታት ብዙውን ጊዜአቸውን ፣ ገንዘብና ጉልበታቸውን ወደ ልማት ስለሚያውሉት ዓለም በፍጥነት እየሰለጠነች፣ እያደገችና እየበለጸገች ትሄዳለ፣ ምርትና ንግድ የበለጠ ይስፋፋል፣  ችግርና ድህነት ይቀንሳል፣ ለበሽታዎች መድኃኒት ይገኛል፣ ሰዎችና ህዝቦች የበለጠ ስለሚቀራረቡ ና ስለሚተዋወቁ በዓለም ላይ ሰላም እየሰፈነ ይሄዳል፣ አዳጊ አገሮች የበለጠና የተሻለ ድጋፍ ያገኛሉ ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር። ከነዚህ ተስፋዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ለናሙና ያህል እውነት ሆነው ቢገኙም፣ ያ ብዙ ህዝቦችና አገሮች ተስፋ ያደረጉበት የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም ብዙም ውሎ ሳያድር እጅግ ብዙ ህዝብን በፈጁ ጦርነቶች ተተካ። በቀድሞይቱ ዩኮዝላቪያ፣ በሩዋንዳ፣ በኮንኮ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅ፣ በሶሪያ ፣ በሊቢያ፣ በየመን የተለኮሱትና አሁንም እየነደዱ ያሉት ጦርነቶች ብቻ ሳይሆኑ፣ በዓለም ሁሉ እንደሰደድ እሳት የተስፋፋው ሽብርተኝነት እጅግ ብዙ መንግስታትን እንቅልፍ ከነሳ ውሎ አድሮአል። ይህ እውነታ ደግሞ በብዙ የዓለም አገሮች የሚኖረውን ሰላማዊ ህዝብ የእለት ከእለት ኑሮ በብዙ መንገድ ለውጦታል። በአፍጋኒስታንና  በኢራቅ የተደረጉት ታላላቅ ጦርነቶች የፈጠሩት እልቂት፣ የህዝቦች መፈናቀልና የሰላም መናጋት ገና መፍትሔ ሳያገኝ አዳዲስ ጦርነቶች በሶሪያ፣ በሊቢያ፣ በየመን ከተለኮሱ ዓመታት ተቆጠሩ። ሶቪየት ህብረት ከፈረሰች በኋላ ያለኔ ማን አለ ብላ ያሻችውን ሁሉ በዓለም ዙሪያ ለማድረግ የዘመተችው አሜሪካና፣ ቀስ ብላ በማንሰራራት “የለም እኔም አለሁ ከምትለው ሩሲያ እንዲሁም ቻይና መካከል የተፈጠረው ውጥረት ከፍተኛና ለዓለም ሰላም እጅግ አስጊ እንደሆነ ብዙ ታዛቢሶች ያስጠነቅቃሉ። ለጦርነት የሚደረጉ ዝግጅቶችና የመሳሪያ ቴክኖሎጂ እድገት እሽቅድምድም በሚያስገርም ፍጥነት በየእለቱ እየጨመረ መሆኑ ምንም አከራካሪ አይደለም። በአሜሪካና በሩሲያ፣ በቻይና፣ በኢራን፣ በሶሪያ እንዲሁም በሰሜን ኮሪያ መካከል ያሉት ከፍተኛ ውጥረቶች ብቻ እንኳን ምድራችንን ሊጠፋ ወደማይችል የጦርነት ሞገድ ውስጥ ሊከቷት እንደሚችሉ ብዙዎች እያስጠነቀቁ ነው።
በእንቅርት ላይ  ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ዓለም አቀፋዊና የግብረ ሰናይ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ከሚያወጧቸው ማስጠንቀቂያዎች አንዱና ዋነኛው የአደገኛ ህዋሳት (SUPER BUGS) መባዛትና ብዙ ህዝብን ሊፈጁ የሚችሉ የወረርሽኝ በሽታዎች ቁጥር መጨመር ነው። ባለፉት 15 ዓመታት  እንኳን SARS, MERS, EBOLA, Swine Flu, Bird Fl;u, Salmonella, ZIKA Virus ወዘተ የሚባሉ ተውሳኮችና በሽታዎች ብዙ ሺ ህዝቦችን ፈጅተዋል። አሁንና ወደፊት ይከሰታሉ ተብለው የሚነገሩ በሽታዎች ደግሞ ክትባት ወይም መድኃኒት እንኳን ሊገኝላቸው የማይችሉ እንደሚሆኑ ከሚናገሩት መካከል ባለብዙ ሃብቱ የMICROSOFT ባለቤት ቢል ጌትስ ይገኙበታል።  ድርቅና ረሃብ ብዙ አገሮችን እንደገና እየጎበኘ ባለበት በዚህ ዘመን፣ ጎርፍ፣ የመሬት መደርመስ፣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታና ሌሎችም የተፈጥሮ አደጋዎችም የራሳቸውን ጥፋት እየሰሩ ነው።
የዓለምን ሁኔታ በቅርቡ የሚከታተሉ አዋቂዎችና እንደ ሚካኤል ጎርባቾቭ ያሉ የቀድሞ መሪዎችም ሳይቀር ዓለማችን እጅግ አደገኛ ወደሆነ ሌላ የዓለም ጦርነት እየተቃረበች መሆኑን ሲያስጠነቅቁ ከርመዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ የተደረገው የመንግስት ሽግግር አገሪቱ ከሩሲያ፣ ከቻይና፣ ከኢራን፣ ሰሜን ኮሪያና ሌሎችም አገርች ጋር ያላትን ውጥረት ያረግበው ይሆናል ተብሎ የተገመተውም ቀቢጸ ተስፋ ከመሆን የዳነ አይመስልም። የአውሮፓ ህብረት በእንግሊዝ መውጣት ሲታወክ፣ ሌሎች ብዙ አገሮችም ይከተላሉ የሚለው ስጋት ትልቅ መናጋትን ፈጥሮአል። በእንግሊዝ ተጀምሮ ወደ አሜሪካ የተሻገረውና አሁን ደግሞ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በጣሊያንና በሌሎች አገሮችም ይከሰት ይሆናል ተብሎ የሚፈራው የፖለቲካ ለውጥ፣ ከመካከለኛው ምስራቅና መረጋጋት ከሚጎድላቸው ብዙ አገሮች ወደ ምእራቡ ዓለም የሚጎርፈው የስደተኛና የተሻለ ኑሮ ፈላጊ ህዝብ ብዛትም ከፍተኛ ውጥረትን ፈጥሮአል። ባለፈው ሳምንት እንደ ጻፍኩት የቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ ቦታ ላይ ስለደረሰን፣ የዘመኑ ባለሃብቶች እንዲሁም አዋቂዎች የሰው ልጅ ራሱ ኋላ ቀር ሆኖአልና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን በጭንቅላቱና በአካሉ ውስጥ በማስገባት ሰውን ራሱን እናሻሽለዋለን በማለት ሲያቅዱ የነበረው ሃሳባቸው ከምርምር ማእከሎችና ከምስጢርነት ወጥቶ በመገኛኛ ብዙኃን በግልጽ እየተናፈሰ ይገኛል።

ይህን ሁሉ ስንመለከትና፣ ከጥቂት ዓሰርት ዓመታት በፊት በምድር ላይ ከነበረው ተስፋ ሰጭ የሚመስል ሁኔታ ጋር ስናስተያየው መጽሐፍ ቅዱስ “ሰላምና ደህንነት ነው ሲሉ ምጥ እርጉዝን ሴት በድንገት እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፣ ከቶም አያመልጡም” ( 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡1-4) የሜለው የትንቢት ፍጻሜ ይመስላል። ያለጥርጥር ዓለም በታላቅ ፍጥነት እየከነፈችበት ያለው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እውነት የራቀና የሰውን ልጅ የወደፊት የሰላም ኑሮ እጅግ የሚያሰጋ ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አሁንም ቢሆን የመመለስ ተስፋ እንዳለ ይናገራል። እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰጠው ምህረትና የዘለዓለም ሕይወት ተስፋ በሩ ዛሬም አልተዘጋም። ለእያንዳንዱ ሰው በግሉም ሆነ ለዓለማችን በአጠቃላይ ያለው እውነተኛ ተስፋ መሰረቱ ይህ ብቻ ነው። ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ በዚህ እውነት ራሱን በመመዘን የወንገልን የምስራች ለሌሎች ሁሉ የማድረሻው ጊዜ ይህ ነው። የዓለማችን ዋነኛው ችግር ኃጢዓት፣ መፍትሔው ደግሞ ክርስቶስ ነው። የማታ የማታ ፍጥረት ሁሉ ይህን እውነት ያውቃል። ዛሬ ንስሃ በመግባት ለማይመለስ ሰው ሁሉ ግን ያ እውቀት ለፍርድ እንጂ ለመዳን አይሆንም። ስለዚህ ሁላችንም በምድር ላይ ሊመጣ ካለው ጥፋት ለማምለጥ እንድንችል በንስሃ እንመለስ፣ የተመለስንም ሌሎችን እንመልስ። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ ብርሃኑ አድማሱ።

አዕምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው፣ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና፣ ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው። የዮሐንስ ራዕይ 13፡18

አዕምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው፣ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና፣ ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው። የዮሐንስ ራዕይ 13፡18


 እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ሲፈጥረው በዚህች ምድር ላይ ዘሩ እንዲበዛና በእርስዋም ያሉትን ፍጥረታትን እንዲከባከብና እንዲያስተዳድር እንዲጠብቅም ነበር። የሰው ልጅ ያንን በረከት ለመውረስና የተሰጠውን ሥልጣን በሚገባ ለመጠቀም ደግሞ እርሱ ራሱ የሁሉም ነገር ምንጭ ከሆነው ከፈጣሪው ጋር እንዲኖረው የታደለበትን ልዩ ፀጋ በማክበር ለአምላኩ መገዛት፣ እርሱን ብቻ ማምለክና ከእርሱም ጋር ህብረት ማድረግ ያስፈልገው ነበር። ያ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ፍጹም ህብረት በኃጢዓት ምክንያት ሲበላሽ ግን የሰው ልጅ በወደቀው ኪሩብ በሉሲፈርና በጭፍሮቹ የተንኮል ወጥመድ ውስጥ ገባ። የሚያስፈልጉትንም ሆነ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት ሲል ከፈጣሪ በተሰጠው እውቀትና ጥበብ ብቻ ከመጠቀም ይልቅ፣ ከጨለማው ዓለም ገዥ የሚወረወሩለትን ቅራቅንቦዎች መለቃቀም ጀመረ። ስር ምሶ ቅጠል በጥሶ ሌላውን ለማጥፋት መርዝ ከመቀመም ጀምሮ፣ መናፍስትን በመጥራትና ከአጋንንት ጋር ቃል ኪዳን በመግባት በሌሎች ላይ መተትን እና ሟርትን ማድረግ የሰው ልጅ በራሱ የፈጠራቸው ሳይሆኑ በወደቁት መላእክት አማካይነት ዲያብሎስ የሰው ልጆችን ያስተማራቸው ብዙ ክፋቶች አካል ናቸው። እነዚህ ኋላ ቀርና የድሮ ነገሮች ናቸው ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን እነዚህ ነገሮች በምድር ሁሉ እንዴት ተንሰራፍተው እንዳሉ በቂ መረጃ የሌለው ወይም እያወቀ መቀበል የማይፈልግ ሰው ብቻ ነው።
የሰው ልጅ ኑሮውን ለማሻሻልና የተሻለ ህብረተሰብን ለመገንባት የተለያዩ ቴክኮኖሎጂዎችን መፍጠሩና በነዚህም በመረዳት የስራን ሸክም ማቃለሉ እና ፍሬያማነትን ማጠናከሩ መልካምን ሁላችንም ልንረባረብበት የሚገባ ነገር ነው። በዚህ በተያያዘው ዜና ላይ እንደምታዩት፣ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ልእቀት ላይ ደርሰናል በሚሉት አገሮች ባሉ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ መሪዎች የሚተነበየውና ትኩረት ተሰጥቶት ብዙ መዋእለ ንዋይ የሚፈስለት የቴክኖሎጂ እድገት አቅጣጫ የሚያተኩረው ግን ዛሬ ብዙ የዓለምን ህዝቦችን ወጥረው የያዙ የምግብና የንጹህ ውሃ እጥረት፣ የህክምና ችግር፣ ሽብርተኝነትና የሰላም መታጣት ወዘተ አይደሉም። በዚህ ዜና ላይ የተገለጸው ሃሳብ ዋና ምንጭና አራማጅ የሆኑት የጉግል ኮርፖሬሽን የቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ሬይ ከርዝዋይል የሚባሉት አሜሪካዊ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር የሚታወቁ ሰው ናቸው። ባለፉት አሰርት ዓመታት በጻፉአቸው ብዙ መጻህፍቶቻቸውና በየጊዜው በሚያደርጉአቸው ንግግሮች እኒህ ሰው ብዙ ቴክኖሎጂን የሚመለከቱ ትንበያዎችን አድርገው ከነሱም ውስጥ ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት እውን ሆነዋል። ነቢይ ሆነው ሳይሆን እየተሰራ ያለውን አዳዲስ ቴክኖሎጂ በአብዛኛው ስለሚያዉቁና እራሳቸውም ደግሞ በሚሰሩት ነገሮች ውስጥ ተሳታፊ ስለሆኑ ነው። በቴክኖሎጂ ልእቀት ከመታመናቸው የተነሳ እኒህ ሰው የሰውን ልጅ ክቡርነት ሰው ሰራሽ ከሆኑ ኮምፒውተሮችና መሰል ቴክኖሎጂዎች በላይ አድርገው ለማየት ተስኖአቸዋል የሚሉ ብዙ ናቸው።
በተያያዘው ዜና ላይ እንደምታነቡት፣ እኒህ ሰው ባለፉት አስር ዓመታትና ከዚያም በፊት በጻፉአቸው መጻህፍቶቻቸው ላይ እንደ ገለጹት፣ በተለያዩ የቴክኖሎጂ መስኮች የተደረጉ እድገቶች እጅግ የላቀ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው የተነሳ የሰው ልጅ የሰራቸው ኮምፒውተሮችና በኮምፒውተር የሚመሩ ቁሳቁሶች ከሰው ልጅ ችሎታና አቅም በላይ የሚሆኑበት ጊዜ ከ12 ዓመት እንደማያልፍ አመልክተዋል። በኮምፒውተር፣ በሮቦቲክስ፣ በናኖ ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሲንተቲክ ባዮሎጂ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የቴክኖሎጂ መስኮች የተደረሰበት የእድገት ደረጃ እጅግ ታላቅ ስለሆነና፣ የሰው ልጅ ደግሞ በተፈጥሮ ባለው ችሎታ ብቻ እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በሚገባ ተቆጣጥሮ ስራ ላይ ለማዋል ስለማይችል እሱ ራሱ በቴክኖሎጂ መሻሻል አለበት። ይህ አይቀሬ ነው እንዲያውም ከዛሬ እስከ ዛሬ አስራ ሁለት ዓመት ድረስ (በ2029 እንደ ኤውሮፓውያን አቆጣጠር) የሰው ልጅ ጭንቅላትና እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በመደባለቅ የቴክኖሎጂ አሃዱነትን (SINGULARITY) ይፈጥራሉ ብለዋል። ከኮምፒውተር ወደ ታብሌት፣ ከታብሌት ወደ ስማርት ስልኮች፣ ከስማርት ስልኮች ወደ ስማርት ሰዓቶች በታላቅ ፍጥነት ተሸጋግሮ የመጣው ቴክኖሎጂ ወደ ኪኒንነት ተለውጦ ሰዎች እንደ መድኃኒት የሚውጡአቸው የሆድ ውስጥ ካሜራዎችና ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ ሮቦቶች ከተሰሩ ውለው አድረዋል። ይህ ካስገረመን ዛሬ ደግሞ እንደ መድሃኒት በመርፌ ተወግተው ወደ ሰውነት የሚገቡ፣ ከዚያም በሰውነት ሁሉ ተሰራጭተው የተለያዩ ስራዎችን በሰው ሰውነት ውስጥ የሚሰሩ ናኖ ሮቦትስ ከተሰሩና መፈተሽ ከጀመሩም ዓመታት አልፈዋል። እንደ አንድ ማስረጃ የሚከተለውን ማገናኛ በመጠቀም ከ2 ዓመት በፊት በአንድ የእንግሊዝ ጋዜጣ የወጣ መረጃ ተመልከቱ።(http://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-3000904/Nanorobots-trial-begin-humans-Microscopic-DNA-devices-injected-leukaemia-patient-bid-destroy-abnormal-cells.html)
ታዋቂው አሜሪካው ፈልሳፊ ባለፉት ጥቂት ቀናት ያሉት ባጭሩ የሚለው፡ እኛ የሰው ልጆች ሰው ከሰራቸው ቴክኖሎጂዎች ይልቅ ቀርፋፋ፣ ብዙ ነገር የማይገባንና ይህችንም ምድር ያለአግባብ እያበላሸናት ስለሆነ፣ የተሻልን ፍጥረቶች እንድንሆን በመርፌ የሚወጉ፣ እንደ ኪኒን የሚዋጡ፣ ምናልባትም ደግሞ የሚጠጡ፣ የሚበሉና የሚሸተቱ ወይም ደግሞ በጨረር በቀጥታ ወደሰውነታችን ውስጥ የሚገቡ ጥቃቅን ኮምፒውተሮችና ሮቦቶች ይገጠሙልናል። በዚያን ጊዜ ጭንቅላታችንና ሰውነታችን ከቴክኖሎጂው እኩል ስለሚሆንና ራሱ ከኢንተርኔት ጋር ስለሚያያዝ ጆሮአችን ስልክ፣ አይናችን ቴሌቪዥን፣ አፋችን ድምጽ ማጉሊያ፣ ጭንቅላታችን ደግሞ ታላቅ ኮምፒውተር ይሆናል። ሬይ ከርዝዋይል እንደሚሉት ከሆነ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከሰውነታችን ጋር ሲዋሃዱ ሁላችን እንደ GOOGLE ሊቅ በመሆን ሁሉን ነገር እናውቃለን። በዓለም ሁሉ ካሉ ሰዎችና ቁሶች ጋር በቀጥታ በጭንቅላታችን ብቻ እንገናኛለን። ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ ወይም ለሌሎች ሰዎች ለመናገርና መልእክት ለማስተላለፍ ወይም ለመቀበል የትም መሄድ አያስፈልገንም። ሰውና ማሽን አንድ ይሆናል ከዚያም በኋላ ዓለም ገነት ትሆናለች ነው የኒህ ሰው ትንበያ ባጭሩ። የረሱት ነገር ግን የሰው ልጅ ስጋና ደም ወይም ጭንቅላትና ጡንቻ ብቻ ሳይሆን በልዑል እግዚአብሔር የተፈጠረ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው። ሰው የሚወደውና የሞተለት አምላክ አለው።
ቴክኖሎጂ እኛ የምንቆጣጠረው መሳሪያ እንጂ በውስጣችን ገብቶ እኛን የሚቆጣጠር ከሆነ ይህ የሰውም የእግዚአብሔርም ስራ ሳይሆን ሰይጣናዊ ነው። በቤታቸው ወይም በቢሮአቸው ተቀምጠው በሚያዩት ቴሌቪዝንና ስልክ ወይም በሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ግለሰቦችንna ሆነ መንግስታትን እየሰለሉ አናስቀምጥም ያሉት ኃያላን አገሮች በኢንተርኔት አማካይነት ወደ እያንዳንዱ ሰው ጭንቅላት ውስጥ መግባት ከቻሉማ ምን ያደርጉ ይሆን። አዋቂዎች ነን ያሉ ኑሮ ያልፍልሃል ብለው ውስጡን በቴክኖሎጂ ከተበተቡት በኋላ፣  ተንኮለኞች፣ ሽብርተኞችና ወንጀለኞች HACK በማድረግና ቫይረስ በመልቀቅ ድሃ ድሃውን ወይም እነሱ የሚጠሉትን ሁሉ እንደማይፈጁት ዋስትናው ምንድ ነው። ደግሞስ በቴክኖሎጂ ለመተብተብና የተሻለ ፍጥረት ለመሆን የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚከፍለው ማን ነው። መቼም ሚስተር ከርዝዋይል እና መሰሎቻቸው ለዓለም ህዝብ ሁሉ በነጻ ይህንን ቴክኖሎጂ ለመቸር የሚፈልጉ ወይም የሚችሉ  አይመስለኝም።  ስለዚህ ሃብታሙ በተራቀቁት ቴክኖሎጂዎች ሲታደስ፣ ድሃ ድሃው ደግሞ በተራረፈውና ምናልባትም ደከምና ረከስ ባሉት ቴክኖሎጂዎች ሊታደስ ነው ማለት ነው?  

መጽሐፍ ቅዱስ 666 የሚባል ነገር ይመጣል ይላል ሲባል የሰማን ሁሉ አሁን ልንነቃ ይገባል። ሃሰተኛው ክርስቶስ የምድር ህዝብ ሁሉ እንዲሰግዱለት የሚያደርግበት ቴክኖሎጂ በደጅ ነው። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው። የሰው ልጅ በምድር ሁሉ ላይ ሊመጣ ታላቅ ስህተትና ጥፋት ሊያመልጥ የሚችለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው። በቀኝ እጅ ወይም በግንባር ለሰው ሁሉ ይሰጣል ሲባል ያነበብነውና የሰማነው የሚፈጸምበት ጊዜ እንደደረሰ እንመለከታለን። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ብሎ ወንጌል እንደተናገረ፣ የንስሃ ቀን ዛሬ ነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የመዳን ቀን ዛሬ ነው።  ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ ብርሃኑ አድማሱ። 

የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ፤ 2ኛ ጢሞቲዎስ 2፤19

የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ፤ 2ኛ ጢሞቲዎስ 2፤19

Engineers search the mass grave at the former mother and baby home in Tuam, County Galway.
ባለሙያዎች በመሬት ውስጥ የተቀበረውን በሚያይ ራዳር በመታገዝ Tuam, County Galway በሚባለው ና በአየርላንድ በሚገኝ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስር ይተዳደር የነበረ ያላገቡ እናቶች እና የህጻናት መኖሪያ ስፍራ ያለአገባብ ሞተውና አስከሬናቸው በአንድ ስፍራ በድብቅ የተቀበረ 800 የሚሆኑ ህጻናት አጽሞችን ሲመረምሩ

የወንጌል የምስራች እጅግ አስደናቂ እና ክቡር ዜና፣ ከዚህ በፊት ያልመጣ ከዚህም በኋላ ሌላ ምትክ የሌለው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢዓታችን እና በበደላችን የጠፋነውን እኛን የሰውን ልጆች ሊዋጅ የመጣው እግዚአብሔር ወልድ ነው። ይህ ከራሱ ከልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ ከሰማይ የመጣው ዜና ደግመን ደጋግመን ብንሰማው፣ ብንዘምረው፣ ብንሰብከው ብንጽፈው የማይሰለች እውነት ነው። ይህን ታላቅ ዜና እንድናበስርና በወንጌሉ መዳን በሚገኘው አዲስ ሕይወት በመኖር የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ጽድቅና መልካምነት እንድናሳይ የተጠራን ደግሞ ራሳችንን ክርስቲያን ብለን የምንጠራ ሁሉ ነን። በእውነት ምስጢሩ ከገባን፣ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ተብሎ መጠራትን የሚተካከል ታላቅ ክብር፣ ሹመትና ኃላፊነት በዚህ ምድር ላይ የለም። ይህ ሥልጣን፣ ክብርና ኃላፊነት ግን በምድር ላይ እስከ ዛሬ ከነበሩ፣ ዛሬም ካሉና ነገም ሊመጡ ከሚችሉ ሹመቶችና፣ ክብሮችና ኃላፊነቶች ሁሉ የተለየ ነው። ምክንያቱም የዚህ ሥልጣን፣ ክብርና ሹመት ዋና ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን እንጂ ሰዎች እንዲያገለግሉት አይደለም። ስለዚህ፣ ባሪያ ከጌታው፣ ደቀ መዝሙርም ከመምህሩ አይበልጥምና የክርስቶስ ተከታይ ነኝ የሚል ማንኛውም ሰው እንደተሰጠው ጸጋ፣ ሹመትና ኃላፊነት መጠን በነገር ሁሉ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ ሊከተል የግድ ነው። የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ የሚል ሰው ደግሞ አገልግሎቱ በእግዚአብሔርና በሰዎች፣ እንዲሁም በሰማይ መላእክትና በጨለማው ዓለም ገዥዎችም ፊት ጭምር ስለሆነ ክቡር በሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ላይ ነቀፌታን እንዳያመጣ በብዙ የእግዚአብሔር ፍርሃት መኖር ይገባዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው ሰዎች ሁሉ ኃጢዓትን ሰርተዋል፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፣ ስለዚህም በኢየሱስ ክርስቶስ በተደረገው ቤዛነት በኩል ብቻ ከዘለዓለም ሞት ይድናሉ። ሮሜ 3፤23 ይህ መዳን የሚገኘው ደግሞ ሰው ኃጢአተኝነቱን ተገንዝቦ ንስሐ ሲገባና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት የከፈለውን የደህንነት ዋጋ በማመን የእግዚአብሔርን ጸጋ ሲቀበል ነው። አንድ ሰው ሰው ጌታን በማመንና በመቀበል የሚገኘውን ዳግም ልደት ከተለማመደ በኋላ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል በመመገብ፣ ለቃሉ በመታዘዝና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእግዚአብሔር ጸጋ በማደግ ዕለት ከዕለት፣ ደረጃ በደረጃ ክርስቶስን እንዲመስል ወደሚያስችለው ሕይወት ለመድረስ መትጋት ያስፈልጋል። ለዚህም እድገት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ማእከል የአማኞች ህብረት ወይም “ቤተ ክርስቲያን” ነው። አንድ ክርስቲያን እንደ አንድ ኩራዝ፣ ሻማ፣ ጧፍ፣ ፋኖስ፣ ማሾ፣ ወይም አምፖል የእግዚአብሔርን ብርሃን በኃጢዓት ጨለማ ውስጥ ላለው ዓለም ያበራል። ቤተ ክርስቲያንና የአማኞች ህብረት ደግሞ ብዙ ኩራዞች፣ ሻማዎች ወይም ፋኖሶች በተናጥል ከሚያበሩት በላይ ሊያበሩ ይችላሉ። ብርሃን ሊያበራ የማይችል ሻማ፣ ፋኖስ ወይም ኩራዝ ዋጋ ስለማይኖረው ምናልባት ለጌጥ ወይም ለአሻንጉሊትነት ካልሆነ በስተቀር ፈላጊ አይኖረውም። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረውና ያስጠነቀቃቸውም ይህንኑ ነው። ጨው ጨውነት ከሌለው በስተቀር ድንጋይ ነው ተብሎ ወደ ውጭ ይጣላል በእግርም ይረገጣል። በተራራ ላይ የተሰራች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም፣ መብራትንም ስናበራ ለሰዎች ሁሉ በሚታይና በሚያሳይ ቦታ ላይ እናስቀምጠዋለን እንጂ ከእንቅብ በታች አናኖረውም። ማቴዎስ 5፡13-16
በዓለም መንግስታትም ሆነ በግል ድርጅቶች ሰራተኛ የሚሆኑ ሰዎች ሁሉ ለመንግስታቸውና ለድርጅታቸው ዓላማ፣ መልካም ስምና ተግባር ገንቢ አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ቢያንስ ቢያንስ ግን አፍራሽ አስተዋጽኦ ማድረግ የለባቸውም። በነዚህ መንግስታትና ድርጅቶች እንደ ባለሥልጣን የሚሾሙ ደግሞ በተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት መጠን የድርጅቱን ወይም የመንግስቱን ዓላማ ማራመድ እንዲሁም ደግሞ አፍራሽ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች እንዳይፈጠሩ ጥንቃቄ በማድረግ ሌሎች ሰራተኞችን እና ባልደረቦቻቸውን የመምራት ግዴታ አለባቸው። ይህ የዓለም ሥርዓት ከሞላ ጎደልም ቢሆን ስለሚሰራ ነው በሰላም ወጥተን የምንገባው፣ ልጆች ወልደን የምናሳድገውና የምንኖረው። እነዚያ ባለስልጣናትና ሰራተኞች መልካም አድርገው ቢገኙ ይሾማሉ፣ ክፉ ካደረጉ ግን ውሎ አድሮም ቢሆን ይቀጣሉ፣ ሥልጣናቸውን ያጣሉ ወዘተ። የዚህ መልካም ሥርዓትና እውቀት ሁሉ ምንጭ ደግሞ እግዚአብሔር እንደሆነና ሥልጣንም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንማራለን። ሮሜ 13፡1 ታዲያ የዚህ የሚያልፈው ዓለም መንግስታትና ድርጅቶች እንዲህ በመልካም አስተዳደር መሄድ ካስፈለጋቸው፣ የዓለም ብርሃን ናችሁ የተባሉ ክርስቲያኖች አካል የሆኑባት ቤተ ክርስቲያንማ እንዴት በላቀ መንገድ ልትኖር ይገባት !?
ሁሉ ድርጅት፣ ሁሉ ባለስልጣን ወይም ሁሉ መንግስት አንድ እንዳልሆነ እናውቃለን። መሆን ባይኖርበትም አብያተ ክርስቲያን ሁሉም የእግዚአብሔርን ቃል በአንድ መንገድ እንደማይረዱ ወይም ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ሁሉ መስራችና ባለቤት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በአንድ ዓይነት መንገድ እንደማያንጸባርቁ ከታሪክም በዘመናችን ከምናየውም እንረዳለን። እያንዳንዱ በገዛ ፈቃዱ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚያምን ሰውም ሆነ ቤተ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚጠራ ድርጅት ሁሉ በአካሄዱ፣ በአስተዳደሩና በህብረተሰብ መካከል በሚያሳየው ባህርዩ ለክርስቶስ ወንጌል ምስክር ወይም እንቅፋት ሊሆን ይችላል። በክርስቶስ ያመነ ማንም ሰው፣ ከማይጠፋው ከእግዚአብሔር ቃል ዘር ተወልዶአልና ኃጢዓትን በፈቃዱና በተለምዶ ማስተናገድ አይችልም።  እግዚአብሔር ብርሃን ነውና ክርስቶስን የሚያምን በጨለማ ለመመላለስ አይችልም።

በዚህ ባያያዝኩት ዜና ላይ እንደምንመለከተው፣ ይህ ያለንበት ዘመን እጅግ አሳዛኝ፣ ዘግናኝ እና አሳፋሪ የሆኑ ዜናዎችን ከመስማት ልንሸሽ የምንችልበት ዘመን አይደለም። እያንዳንዳችን ክርስቲያኖች፣ ምንም ቦታ የለኝም የምንለውም ሆንን በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያለን ሁሉ በእኛ ላይ የሚጠራው የክርስቶስ ስም ከእኛም ሆነ የእኛ ከምንላቸው ነገሮችና ሰዎች በላይ መሆኑ ሁል ጊዜ በፊታችን ተቀርጾ ሊቀመጥ ይገባዋል። የክርስቶስ ተከታይ ነኝ የሚል ሰው እግዚአብሔርን ማመኑ፣ መከተሉና ማገልገሉ በምንም ዓይነት መንገድ ለዚህ ምድር ጊዜያዊ ኑሮ ማትረፊያ ወይም መጠቀሚያ ከመሰለው እጅግ ተሳስቶአል።1ኛ ጢሞቲዎስ 6፡5-10። እንኳን  አገልጋይና የቤተ ክርስቲያን መሪ ይቅርና እያንዳንዱ ተራ ክርስቲያንም ቢሆን በክርስቶስ ያለውን ነጻነትና መልካም ስም ለክፋት መሸፈኛ ማድረግ የለበትም። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡16። ወገኖች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ሩቅ አይደለም። እሱ ሲመጣ ደግሞ ለእያንዳንዱ እንደ ስራው ዋጋውን ይሰጣል። ልንገነዘብና ልንፈራ የሚያስፈልገን ግን አንድ ቁም ነገር አለ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መላእክቱ ጋር በክብር ሲገለጽ፣ የክርስቲያን ስም በላያችን ላይ ለጥፈን በውስጣችን፣ በዙሪያችንና በኃላፊነት ቦታችን አውቀን፣ ፈልገን የሸሸግነው ነውር እንዳይገኝብን እንጠንቀቅ። እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላም። የክርስቲያን ስም ወይም የሹመት ማእረግ መያዛችን የኃላፊነታችን ቀንበርና ምልክት እንጂ የፈለግነውን ሁሉ እያደረግን እና እንዳሻን እየተመላለስን ምንም አልሆንም ብለን የምንኩራራበት ምሽግ አይደለም። ኃጢዓት እግራችንን ጠልፎ ሊጥል ሁል ጊዜ በዙሪያችን፣ በሃሳባችን፣ በምንሰማው፣ በምናየው፣ በምናነበው ነገር ሁሉ ውስጥ ያደባል። ነገር ግን ጌታ ለቃየል እንደነገረው፣ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ልንቃወመውና በእግራችን ስር ልንረግጠው ስልጣን አለን።  “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመጽ ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበትና የተደላደለ የእግዚአብሔር መሰረት ቆሞአል።” 2ኛ ጢሞቲ 2፤19። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ ብርሃኑ አድማሱ

አንድ የዓለም መንግስት ይመስረት የሚለው ሃሳብ እየጨመረ ያለው ለምን ይሆን? ታዋቂው ፕሮፌሰር ስቲቨን ሆውኪንግም ይህ ያስፈልጋል አሉ

http://www.thetimes.co.uk/article/hawking-on-humanity-and-corbyn-jk88zx0w2?#_=_

አንድ የዓለም መንግስት ይመስረት የሚለው ሃሳብ እየጨመረ ያለው ለምን ይሆን?

ባደረባቸው ከፍተኛ የነርቭ ህመም ምክንያት የወንበር ቁራኛ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቨን ሆውኪንግ በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉት ታላላቅ የTheoretical Physics ምሁራንና ተመራማሪዎች በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው። ኢሎን መስክ የሚባሉት የደቡብ አፍሪካ ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊ ቢሊዮነርና SPACE-X የሚባሉትን ወደህዋ የሚመጥቁ ሮኬቶችን የሚሰራው ድርጅት እና TESLA በሚባለው ስም የሚታወቁትን የተራቀቁ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ሰሪ ድርጅት ባለቤት ደግሞ እንዲሁ በቴክኖሎጂው መስክ ትልቅ ዝናን ያተረፉ ሰው ናቸውው። ታዲያ በዚህ በተያያዘው ዜና ላይ እንደምታነቡት እነዚህ ሁለት ታላላቅ ሰዎች የሰው ልጅ ራሱ የሰራው እና በከፍተኛ ፍጥነት በዓለም ላይ እየተሰራጨ ያለውና ARTIFICIAL INTELLIGENCE በመባል የሚታወቀው ቴክኖሎጂ የሰውን ዘርና ሌላውንም ፍጥረት ደህንነት ስለሚያሰጋ መንግስታት በመተባበር ይህ ቴክኖሎጂ ከቁጥጥር ስር እንዳይወጣ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ሲያሳስቡ ከርመዋል። በዚህ ዜና ላይ እንደምናየው ትንሽ የሚያስገርመው ግን፣ ፕሮፌሰር ሆውኪንግ አሁን ያሉት የዓለም መንግስታት መተባበር ብቻ በቂ መሆኑ ስላሳሰባቸው አንድ የዓለም መንግስት መቋቋም ያስፈልገዋል ማለታቸው ነው። ያ አንድ የዓለም መንግስት ደግሞ አምባ ገነን ሊሆን እንደሚችል ግር የማይላቸው ፕሮፌሰር፣ ያ ሊሆን ቢችልም የሰው ልጅ ያንንም ችግር ቢሆን መወጣት ስለሚችል እንደሳቸው ሃሳብ አንድ የዓለም መንግስት መቋቋሙ የግድ አስፈላጊ ነው። ታሪክን ጠጋ ብለን ከመረመርን አንድ የዓለም መንግስት ይቋቋምልን የሚለው ሃሳብ በኒህ ፕሮፌሰር የተጀመረ ወይም በ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጣ አዲስ ሃሳብ ሳይሆን፣ የሰው ዘር ገና በፈረስ በሚጎተት ጋሪ ይሄድ በነበረበት ዘመንም የነበረ ነው። ለነገሩም እግዚአብሔር ምድርን ሲፈጥር ምድር ሁሉ በአንድ ቋንቋ ነበረች። የአንድነቷም መሰረት እግዚአብሔር በሰው ልጅ መካከል መመላለሱ ነበር። ሉሲፈር ወይም ዲያብሎስ በሚባለው የወደቀ ኪሩብ ማታለል ምክንያት የሰው ልጅ ከአምላኩ ጋር ያለው ግንኙነት ሲበላሽ ግን ሰው እግዚአብሔርን በመግፋት የራሱን መንግስት ለማቋቋም ሲከጅል ሳይወድ በግዱ በዲያብሎስና በሱ ስር በሚተዳደሩ የወደቁ የሰማይ ፍጥረታት ስር መገዛት የግድ ሆነ። ይህ የሆነው ደግሞ በባቢሎን እንደነበር ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ሲያስረዳን፣ ኦሪት ዘዳግም ምእራፍ 32 ቁጥር 7 እስከ 9፣ መጽሐፈ ኢዮብ ምእራፍ 1 እና 2 እንዲሁም ደግሞ መዝሙረ ዳዊት 96፤5 እና ምእራፍ 82 ደግሞ ምድር ዛሬ ወዳለችበት አሳዛኝ ደረጃ እንደደረሰች ዋና ዋና ሃሳቦችን ይሰጡናል።
ይህ የኃጢዓት፣ የጥላቻ፣ የራስ ወዳድነትና የዓመጽ ዘመን ሲያበቃ ጌታ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ በሰላምና በደስታ የሚኖሩበት ምድርና ሰማይም ሁሉ በስሩ የሚተዳደሩበት የእግዚአብሔር መንግስት እንደሚመሰረት ከብዙ ሺ ዘመናት በፊት በተጻፈው በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጾአል። የዚያ መንግስት ንጉስ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከዚያ ከእግዚአብሔር መንግስት መገለጥ ትንሽ ቀደም ብሎ ግን ምድር ሁሉ የሚሰግድለት አንድ ታላቅና ኃይለኛ መሪ እንደሚነሳ፣ የዓለምን ህዝብና መንግስታት ሁሉ በሚያስገርም መንገድና ሰይጣናዊ ጥበብ በማታለልና በመሸንገል፣ እምቢ ያሉትንም በመፍጀት አንድ የዓለም መንግስትን ለአጭር ጊዜ እንደሚመሰርት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ያን መሪ መጽሐፍ ቅዱስ ሃሰተኛው ክርስቶስ፣ የዓመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ፣ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ፣ ሰባት ቀንዶችና አስራ ራሶች ያሉት አውሬ ወዘተ በማለት ይጠራዋል። ይህን በተመለከተ ግልጽ ትምህርቶችን ከሚሰጡት ክፍሎች ውስጥ ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 2፣ ምዕራፍ 7፣ ምዕራፍ 9 እና 11 ፣ የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 24፣ የሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 21 እና የማርቆስ ወንጌል ምእራፍ 13 እና የዮሐንስ ራዕይ ምእራፍ 13፣ እና 17 አንዳንዶቹ ናቸው። ያ ዓመጸኛ መሪም በስልጣኑ ሲደላደል እኔ እግዚአብሔር ነኝና ስገዱልኝ ከማለት አልፎ የማይሰግዱለትን ሁሉ እንደሚያስገድልም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምታል።
በመጨረሻው ዘመን የሚመጣው በሃሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ በመመራት በየዘመናቱ ብዙ ኃያላን ነን ያሉ በጦር ኃይል፣ በማባበል፣ በፍልስፍና እና በኃይማኖት አንዳንዴም ከነዚህ ሁለቱን ወይም ሶስቱን ወይም ሁሉንም በማጣመር ዓለምን በሙሉ በስራቸው አድርገው እንደ አንድ መንግስት ሊገዙ እንደተነሱ የቅርብና የሩቅ ታሪክ በዝርዝር የዘገበው ጉዳይ ነው። የባቢሎኑ ናቡከደነጾር፣ የግሪኩ እስክንድር፣ የፈረንሳዩ ናፖሊዮን፣ የእንግሊዝ ነገስታት፣ እና የጀርመኑ ሂትለር ዋና ዋናዎቹ ምሳሌዎች ናቸው። ፕሮፌሰር ሆውኪንግ የተመኙት አንድ የዓለም መንግስት መምጣቱ የግድ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ተናግሮአልና። ነገር ግን ያ መንግስት ዓለም እስከ ዛሬ ድረስ ያላወቀችው አታላይ፣ ፈጽሞ ኢሰብዓዊ እንደሚሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። እስካሁን ድረስ በምድር ላይ የነበሩ ክፉ መንግስታት ፈጽሞ የማይወዳደሩት እብሪትና ጭካኔ የተሞላው መንግስት እንደሚሆንና በሱም ዘመን ብዙ የምድር ህዝብ እንደሚያልቅ መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠነቅቃል። ወደ ስልጣን የሚወጣው ግን የምድርን ችግር ሁሉ እንደሚፈታና ምድርን ገነት እንደሚያደርጋት በቴክኖሎጂና በገንዘብ እንዲሁም በሰይጣናዊ ተአምራት በመደገፍ የዓለምን መንግስታትና ህዝቦች በማታለል ነው። ታዲያ ፕሮፌሰር ሆውኪንግ ያ መንግስት አምባ ገነን ሊሆን ይችላል ብለው ሲናገሩ ምን እየተመኙልን እንደሆነ ያውቁ ይሆን? ወይስ እሳቸው የምድርን ህዝብ ወይም የራሳቸው አገር የእንግሊዝን እንኳን በመወከል ይህን ሃሳብ እንዲሰነዝሩ የአገራቸው ህዝብ ድምጽ ሰጥቷቸው ይሆን።

ወገኖች፣ መጽሐፍ ቅዱስ እኛን ክርስቲያኖችን ለአገር መሪዎችና ለባለስልጣናት እንድንጸልይ የሚያስተምረን ዋነኛው ምክንያት እነዚያ መሪዎች ራሳቸው ከክፉ ነገር እንዲጠበቁ፣ እንዲሁም ደግሞ እነሱም እንደኛው ሰብዓዊ ፍጡር ናቸውና በግልም ሆነ በጋራ ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሚመጣ ክፉና አጥፊ መንፈሳዊ፣ ስነልቡናዊ፣ ፖለቲካዊና ሌሎችም ምድራዊ ግፊቶችን በመቋቋም፣ የሚመሩትን እና የሚያገለግሉትን ህዝብ እንደሰብዓዊ ፍጡር በርህራኄ ማስተዳደር እንዲችሉ ነው። የቅዱሳን ጸሎች ታላቅ ነገርን እንደምታደርግ መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ያስተምረናል። ባለፈው መልእክቶቼ እንደ ጻፍሁት፣ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ባለፉት አምስት ዓመታት የዓመጽ መንፈስ በምድር ሁል ላይ እያንዣበበ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የተጻፈው ሁሉ ሊፈጸም የግድ ነው። እኛ ግን የመጸለይና እድሉን ስናገኝም ለሰዎች ሁሉ፣ ለመሪዎችም ጭምር፣ ዘለዓለማዊውን የእግዚአብሔርን እውነት፣ እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያለውንና ራሱን በመስቀል ላይ በመስጠት የገለጸውን ፍቅሩን እንዲሁም ደግሞ የወንጌሉን ግብዣ ለሚቀበሉ የሰው ልጆች ሁሉ ያለውን አስደናቂ እቅድና ዘለዓለማዊ ተስፋ የመናገር ግዴታ አለብን። የሰውን ልጅ ከሚመጣው ጥፋት ሁሉ የሚያድነው ፕሮፌሰር ሆውኪንግ እና ሌሎቹ የሚመኙት ሰው የሚመሰርተው አንድ የዓለም መንግስት ሳይሆን፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ምኞታቸው ለመልካም ቢሆንም የሚመኙት ነገር ምን እንደ ሆነ ግን በትክክል የተገነዘቡ አይመስልም። ስለዚህ ጸሎታችን ለእርሳቸውና ለመሰሎቻቸውም መሆን ያስፈልገዋል። እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ዶ/ር በፈቃዱ ብርሃኑ አድማሱ።

ሃሰተኛው ክርስቶስ ምድርን ሁሉ ወደሚገዛበት ቴክኖሎጂ ደርሰን ይሆን?

https://www.rt.com/news/379757-your-whole-life-is-hacked/

ሃሰተኛው ክርስቶስ ምድርን ሁሉ ወደሚገዛበት ቴክኖሎጂ ደርሰን ይሆን?

ከላይ ማገናኛው የተሰጠውን ዜና በመጀመሪያ አንብቡት።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ተገልጾ ዘለዓለማዊውን የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ የሚመሰርትበት ጊዜ እጅግ እየተቃረበ መምጣቱን ለማስተዋል፣ በቅዱሳን ነቢያት፣ በሐዋርያትና በጌታም በራሱ የተነገሩትን ትንቢቶች ማጥናት ብቻ ሳይሆን፣ በምድር ላይ በተግባር እየተከናወኑ ያሉትንን ነገሮች በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ቀረብ ብሎ መከታተል ያስፈልጋል። ባለፉት አምስት ዓመታት ብዙ ነገሮች ወደ ፍጻሜያቸው እየቸኮሉ መሆናቸውን ብዙ የትንቢት ምሁራንና መንፈሳዊውን ዓለም በቅርብ የሚከታተሉ ተመራራሚዎች ያስረዳሉ።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመገለጹ በፊት ግን እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ እንደገና በኢየሩሳሌም በሚሰራው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚቀመጥ የዐመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ በተለምዶም ሐሰተኛው ክርስቶስ የሚባለው እንደሚገለጽ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ታዲያ ይህ የምድር መንግስታትና ህዝቦች በሙሉ የሚሰግዱለት ዓመጸኛ ወይም ሐሳዊው መሲህ፣ በሚገለጽበት ጊዜ እንዴት አድርጎ ነው የምድር ህዝቦች ሁሉ እንዲሰግዱለት የሚያደርገው የሚለውን ጥያቄ በማንሳት፣ ኮምፒውተር የሚባለው ቴክኖሎጂ እስከተደረሰበት እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ብዙዎች  የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ቀልድ ነው እያሉ ያንኳስሱት ነበር። ዛሬ ግን ሰዎች አመኑም አላመኑም ያለጥርጥር እዚያ ዘመን ላይ ደርሰናል። በእጆቻችን የምንይዛቸው፣ የምንኮራባቸውና በመራቀቃቸው የምንወዳደርባቸው ስልኮች (smart phones) ፣ ታብሌቶች፣ በእጅ ላይ የሚታሰሩ (smart watches)፣ እንዲሁም በመኪናዎች፣ በቴሌቪዥን እና የሙዚቃ ማጫወቻዎች፣ በትራፊክ መብራቶች፣ በካሜራዎችና በሌሎችም ብዙ የእለት ከእለት መጠቀሚያ ቁሳቁሶች ውስጥ ያለው ቴክኖሎጂ ሁሉ ያገለግለናል ብለው የገዙትን ሰዎች ወይም ማህበረሰብ ከማገልገል ባለፈ፣ የማንፈልጋቸውንና ሊጎዱን የሚችሉ ነገሮችን እንደሚሰሩ ከተጠረጠረ ውሎ አድሮአል። ይህ ያያዝኩት ዜና በግልጽ እንደሚያስረዳው፣ እነዚህ በገዛ ገንዘባችን የምንዛቸው ቴክኖሎጂዎች፣ ከዓለም አቀፉ መረብ (ኢንተርኔት) ጋር መያያዛቸው ደግሞ በዚህ ዜና ላይ እንደተገለጸው ያሉ ድርጅቶች ሰው በማያስበው መንገድ በየእለቱ የሚወጣ የሚገባበትን፣ የሚሰራውን፣ የሚገዛ የሚሸጠውን፣ የሚያወራውንና ውሎ የሚያድርበትን ሳይቀር በመቃኘት ሪፖርት ስለሚያደርጉ፣ የየእለት ኑሮአችንን እንኳን በነጻነትና በግል ለማካሄድ የማይቻልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

መንግስታት የአገርን ጸጥታና ሰላም እንዲሁም ህግን ለማስከበር የተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን መጠቀም ህጋዊ ስልጣን እንዳላቸው የታወቀ ነው። ነገር ግን በዓለም ላይ ካሉት መንግስታት አንዱ ብቻ የሆነው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ለምን ይሆን እያንዳንዱን የምድር ሰው ለመሰለል የሚያስችለውን ቴክኖሎጂዎች ፈጥሮና የተፈጠሩትንም ቴክኖሎጂዎች በመጣስ የግለሰቦችን፣ የቤተሰቦችን እና የሌሎች መንግስታትንም ድንበር የሚዘል መረጃ መሰብሰብ ያስፈለገው? ወንጀልን እና ሽብርን ለመግታት ብዙዎቹ ሰላማዊ አገሮችና መንግስታት ከሌሎች መንግስታት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ይተባበራሉ። ያም ባይሆን ደግሞ አሜሪካን የሚያህል ታላቅ አገርና መንግስት መረጃዎችን የሚያገኝበት እጅግ ብዙ መንገዶች እያሉ፣ ለምን ይሆን እያንዳንዱን የእጅ ስልክ፣ የቤት ኢንተርኔት፣ ድረ ገጽ፣ የመኪና አቅጣጫ መፈለጊያ መሳሪያ እና ሌሎችንም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ቁሳቁሶችን መድፈር ያስፈለጋቸው? እነዚህ ድርጅቶች፣ የነሱን ስራ የሚደግፉትና የሚተባበሩአቸው ሁሉ አውቀውትም ሆነው ሳያውቁት፣ ፈልገውም ሆነ ሳይፈልጉት መጽሐፍ ቅዱስ ከክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በፊት ተገልጾ የምድር ሕዝብ ሁሉ በግድ እንዲሰግዱለት ያደርጋል ለተባለው ሐሳዊው መሲህ ዓለምን እንዲቆጣጠር የሚያስችለውን መረብ እየዘረጉለት ነው እያሉ የሚያስጠነቅቁ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና ታዛቢዎች ብዙ ናቸው። ዛሬ የተደረሰበት ቴክኖሎጂና እየተመረቱ ያሉት የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች የተያያዙበት የመረብ አሰራር በእርግጥም በዮሐንስ ራዕይ ምእራፍ 13 ላይ የተጠቀሰው አውሬ አንሰግድልህም የሚሉትን ህዝቦች በሙሉ መግዛትና መሸጥ እንዳይችሉ ለማድረግ የሚያስችሉት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ብዙ የባለጸጎቹ አገሮች መንግስታት ዛሬ ጥሬ ገንዘብን ከገበያ ላይ ቀስ በቀስ እያስወገዱ ዜጎች ለመግዛትና ለመሸጥ ቢወዱም ባይወዱም ኤሌክትሮኒክ ካርዶችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ የእጅ ስልኮችን እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ ደረጃ በደረጃ እያስገደዱ ነው። smart cards የሚባሉት በኑሮ ዘርፎች ሁሉ እንደ አሸን በፈሉባቸው ሰለጠኑ በሚባሉት አገሮች ሰው መኪና ለመንዳት፣ ምግብና ሌሎች ሸቀጦችን ለመግዛት፣ ገንዘብ ባንክ ለማስገባትም ሆነ ለማውጣት፣ ህክምና ለማግኘት፣ በአውሮፕላንና በሌሎችም መጓጓዣዎች ለመጠቀም ሳይወድ በግድ የግል መረጃዎቹን የያዙ ኤሌክትሮኒክ ካርዶችን ወይም የእጅ ስልኮችን መጠቀም የግድ ነው። 

ቴክኖሎጂ በመሰረቱ መልካም ነው። ችግሩ ግን የሰው ልጅ ቴክኖሎጂን ሁሉ ለመልካም አይጠቀምበትም። ከክፉ ሰዎችም ሁሉ በስተጀርባ እስከ ዛሬ በስውር ሲሰራ የነበረው የሃሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ ነው። ያ ክፉ መንፈስ ደግሞ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ የሚገለጽበት ዘመን እጅግ የቀረበ ይመስላል። የብዙ ሰዎች ልብ ከእግዚአብሔር ፍቅር ይልቅ ቴክኖሎጂን እና ዓለምን እየወደደ በመጣበት በዚህ ዘመን ለሃሰተኛው ክርስቶስ መገለፅ አስፈላጊ የሆኑት ቴክኖሎጂዎችም የተዘጋጁ ይመስላል። ራዕይ 13 እንዲህ ይላል፤ “ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፣ ለዘንዶውም ሰገዱለት፣ ለአውሬስ ስልጣንን ሰጥቶታልና ለአውሬውም፤ አውሬውን ማን ይመስለዋል፣ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት። >>> የአውሬው ስም ወይም የስሙ ቁጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው፤ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።” ራዕይ 13 ከ 4 እስከ 18። ጌታም እንዲህ አለ፣ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ማቴ 24፤4 በጌታ መገለጥ ቀን እንዳናፍር ነቅተን ልብሳችንን እንጠብቅ። ጌታ ይባርካችሁና ይጠብቃችሁ። 
ዶ/ር በፈቃዱ ብርሃኑ አድማሱ።

የመለከት ድምፅ መጽሔት ቁጥር 5 ዛሬ ወጥቶአል

የመለከት ድምፅ መጽሔት ቁጥር 5 ዛሬ ወጥቶአል። በዚህ እትም ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረው በመጨረሻው ቀን በተለይም የሃሰተኛውን ክርስቶስን መምጣት ተመልክቶ ብዙዎችን ወደ ስህተት ሊያስገቡ የሚችሉ ሃሳቦችን፣ ፍልስፍናዎችን እና የተሳሳቱ ሃይማኖታዊ እምነቶችን ዋነኛ መሰረቶች በተመለከተ አጠር ያለ ጽሁፍ ቀርቦአል። በተጨማሪም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽፋን እየተዘጋጀ ስላለው ስለኔፊሊምና የሃሰተኛው ክርስቶስ መምጣት ስውር ዝግጅቶች፣ በነዚህ ወራት እጅግ እየበዛ ስለመጣው አለም አቀፋዊ ጦርነቶች ዝግጅትና የጦርነት ወሬ፣ በዱባይ ስለተካሄደው አምስተኛው የዓለም መንግስት ጉባኤ ዘገባ፣ አጠር አጠር ያሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንተናዎች ቀርበዋል። በመጨረሻም በመከራና በፈተና የምናልፍ ክርስቲያኖች ሁሉ እውነተኛና ዘላቂ መጽናናትን የምናገኘው እንዴትና ከየት ነው በሚለው ጥያቄ ላይ አጠር ያለ ትምህርት ቀርቧል። በPDF የተዘጋጀውን የመጽሄቱ ኤሌክትሮኒክ ቅጂ ከላይ ተሰጠው ማግኘት ይቻላል። በጊዜ እጥረት በየወሩ ይቀርብ የነበረው ምስክርነት ቁጥር 4 በዚህ እትም አልደረሰም። በሚቀጥለው ቁጥር 6 ላይ እንደሚቀርብ የምናስታውቀው ከይቅርታ ጋር ነው። ጥያቄና አስተያየታችሁን ብትልኩልን ደስ ይለናል። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ ብርሃኑ አድማሱ

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...