አሜሪካን እያጠፉ ያሉት ታላላቅ ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው ተባለ "ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ" ራዕይ 11፡18

አሜሪካን እያጠፉ ያሉት ታላላቅ ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው ተባለ

የሰሞኑ ታላላቅ የባህር ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው እየተባለ ነው
“ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ”። ይህ ቃል የሚገኘው በዮሐንስ ራዕይ ምእራፍ 11 ቁጥር 18 ላይ ነው። ከቁጥር 15-19 ያለውን ማንበብ ሙሉ ሃሳቡን ይሰጣል። በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ሰባት ማህተሞች ይፈታሉ፣ ሰባት መለከቶች ይነፋሉ፣ ሰባት ጽዋዎችም በምድርና በሰማይ ላይ ይፈስሳሉ። ሰባተኛው ማህተም ሲፈታ እግዚአብሔር ለዚህ ዓለም ፍጻሜ ያዘጋጀው ምስጢር ይፈጸማል፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ይነግሳል። ያ ሲሆን ደግሞ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ወደ መንግስቱ ዓመጸኞችም ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘለዓለም ጨለማ ይሄዳሉ። ዛሬ ይህን መልእክት እንድጽፍ ያስገደደኝ ነገር፣ “ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” የሚለውን ቃል ዛሬ በምድር ላይ እየተካሄደ ካለው ነገር ጋር በጥሞና ሳስተውለው የሰው ልጆች ምን ያህል ጉልበትና እውቀት ቢኖራቸው ነው ምድርን እስከ ማጥፋት ድረስ የደረሱት የሚል ጥያቄ መሙላቱ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ ምድርን እያወከ ስለሆነ ሃብታሞቹም ሆኑ ድሆቹ አገሮች ብዙ ስምምነቶችን ሲያደርጉ ከርመዋል። የኪዮቶ ፕሮቶኮል፣ በቅርቡ ደግሞ የፓሪስ ስምምነት። በመገናኛ ብዙኃን፣ በትምህርት ቤት፣ በየዩኒቨርሲቲዎቹና በመዋእለ ህጻናትም እንኳን ሳይቀር እኛ የሰው ልጆች የምናደርገው ግድ የለሽ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ምድርን እያጠፋ ስለሆነ እንድንጠነቀቅ ነው። ስለዚህም ሁላችንም የምንችለውን በማድረግ ይችን እግዚአብሔር የሰጠንን ምድር ለመንከባከብ ጥረት እናደርጋለን ይህንንም መቀጠል ያስፈልገናል።
ነገር ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የአደባባይ ምስጢር እየሆነ የመጣ ነገር አለ። ባለፉት ከአንድ መቶ በሚበልጡ ዓመታት የሰው ልጅ፣ በተለይም ደግሞ ሃብታምና ኃያል የሆኑት እንደ አሜሪካና ሩሲያ ያሉ አገሮች የአየር ንብረት ምህንድስና ሳይንስን በከፍተኛ ፍጥነት በማሳደግ የምድርን አየር ንብረት በሚፈልጓቸው ቦታዎች ላይ ለመቀየር የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደ ገነቡና ይህንንም ሲፈትሹ እንደኖሩ እጅብ ብዙ ማስረጃዎች ወደ አደባባይ ወጥተዋል። እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ደመና እንዲፈጠር፣ የተፈጠረ ትንሽ ደመና እንዲሰባሰብ፣ እንዲበዛና ወደሚፈለገው አቅጣጫ እንዲሄድ ለመግራት፣ ትልልቅ ሞገዶች (storms and hurricanes) እንዲፈጠሩ፣ የተፈጠሩት እንዲዳከሙ ወይም እንዲጠናከሩና ወደተፈለገበት አካባቢ እንዲሄዱ፣ በአንድ ስፍራ ድርቅ በሌላው ቦታ ደግሞ ከፍተኛ ጎርፍ እንዲፈጠር በማድረግ ብዙ ህዝቦችን የሚጨርሱ እኩይ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ በግልጽ እየተዘገበ ነው። ይህን ስራ የሚሰሩት ደግሞ የአሜሪካ መንግስት ወታደራዊና ሲቪል መስሪያ ቤቶች፣ የጦር መሳሪያ አምራቾች፣ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ባለቤቶችና ተኮናታሪዎች እንደሆኑ ብዙ መረጃዎች ያመለክታሉ። እነዚህ ሰው ሰራሽ በአካባቢና በዓለም የአየር ንብረት ላይ ቀውስ የሚፈጥሩ ምርምሮች፣ ሙከራዎችና ስራዎች እንደሚፈጸሙ ደግሞ ሁለቱም የአሜሪካ ምክር ቤቶች በግልጽ ያውቃሉ፣ ሪፖርቶችም ይቀርቡላቸዋል። እንዲያውም ምክር ቤቶቹና ብዙ የመንግስት ቢሮዎችም ለዚሁ ስራ የሚያስፈልገውን በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር በጀት ይመድባሉ። የአየር ንብረትን ለመቀየር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች  አሉ ወይ ብሎ የሚጠራጠር ካለ ደግሞ የአሜሪካን መንግስት የአእምሮ ውጤት ባለቤትነት (patent) መመዝገቢያ ቢሮ እጅግ ብዙ ለሆኑ ለእነዚህ ቴክኖሎጂዎች በየጊዜው ያደረገውን ምዝገባ ማየት ይበቃል። ይህንን መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ድረ ገጽ እንድትጎበኙ በትህትና እጋብዛችኋለሁ። http://www.geoengineeringwatch.org/
ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ዜናና ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱት፣ ባለፈው በኦገስት ወር መጨረሻ ላይ በደቡባዊ አሜሪካ የቴክሳስ ግዛት ላይ፣ በተለይም በሂዩስተን ከተማ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰው ከፍተኛ ሞገድ (hurricane Harvey) ከላይ በተጠቀሱት ቴክኖሎጂዎች ተቀነባብሮአል ተብሎ በከፍተኛ ደረጃ ይጠረጠራል። በዚያ ሞገድ የተጎዱ ህዝቦች ገና በቂ እርዳታ እንኳን አግኝተው ሳያበቁ አሁን ደግሞ ሌላ hurricane Irma የሚባልና ከሁለት ሳምንት በፊት ከተከሰተው እጅግ የሚከፋ ሞገድ በመምጣቱ በደቡባዊውና በምስራቃዊው አሜሪካ የሚገኙ ብዙ ክፍለ ሃገሮች በተጠንቀቅ ላይ ሲቆሙ፣ ብዙ ሰዎችም የሚመጣውን ጥፋት ፍራቻ ከቤታቸው እየተሰደዱ ይገኛሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴት የአሜሪካ የራሷ መንግስት ወታደራዊና ሲቢል ድርጅቶች፣ የጦር መሳሪያ አምራቾችና ተኮናታሪዎች እንዴት በራሷ በአሜሪካ ግዛት ላይ ጥፋት የሚፈጥር ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለው ጥያቄ ለእኔም ሆነ ለብዙዎች ለማመን የሚያዳግት ነው። ቀረብ ብለው በአሜሪካ ውስጥ ዛሬ ያለውን ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ለሚያጠኑ፣ ይች ታላቅ አገር በዓለም ዙሪያ የሚቃወሟትን መንግስታት በመገለባበጥና አገሮችን በማፈራረስ የምታደርገውን ለሚከታተሉ ታዛቢዎችና በአየር ንብረት ምህንድስና ላይ ከፍተኛ እውቀት ላላቸው ለራሷ ለአሜሪካ ባለሙያዎች ግን ይህ እንግዳ ነገር ወይም የማይታመን አይደለም።  አሜሪካ ያላትን ከፍተኛ የሳይንስና ወታደራዊና እውቀትና ቲክኖሎጂ በመጠቀም አየሩን እደሚፈልጉት በመለዋወጥ የራሷን የአገሪቱን ህዝብ በሚጎዳ መንገድ ይሰራሉ ተብለው በሰፊው የሚታሙት “ጥልቅ መንግስት” (deep state) የሚባለው ከተመረጡ የመንግስት ባለሥልጣናት በስተጀርባ የሚሰራው መዋቅር መሆኑንም ብዙዎች ይዘግባሉ።

በአሜሪካ ብቻ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የአየር ንብረትን ሊቀይሩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች የአእምሮ ባለቤትነት ሰርቲፊኬት ቁጥሮች በአሜሪካ መንግስት የpatent ቢሮ ድረ ገጽ ላይ ማየት ይቻላል።  በየጊዜው አየር ንብረትን ለመቀየር በሰማይ ላይ ስለሚረጩት ኪሚካሎችም (chemtrail) እጅብ ብዙ ማስረጃዎች በአደባባይ ይገኛሉ። የአሜሪካ ምክር ቤቶች ባለፉት ሰባ (70) ዓመታት የአየር ንብረትን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ እንደተፈለገው ስለመለወጥ ስለሚያስችሉ ስራዎች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ፕሮጀክቶች ብዙ ውይይቶችን አካሂደዋል፣ ሪፖርቶች ቀርበውላቸዋል፣ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፣ ህጎችንም አውጥተዋል። ይህን ሁሉ አስመልክተው ነው ብዙ አዋቂዎች ምድራችን ወደ ከፋ ጥፋት ውስጥ ከመግባቷ በፊት እያስጠነቀቁ ያሉት።  ታዲያ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለሚያውቅ ይሆን በመጨረሻው ቀን እሱ ውብና ድንቅ አድርጎ የሰራትን ምድርንና በላይዋ ላይ ያለውን ህይወት በግድየለሽነት፣ በስግብግብነትና በክፋት የሚያጠፉትን ሁሉ የሚፈርድባቸው? ለዚህ ይሆን ሃዋርያው ዮሐንስም “ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” የሚለውን የሃያ  አራቱን ሽማግሌዎች ቃል የሰማው? ሲነገረን እንደኖረው የአየር ንብረት ቀውስ ሁሉ የእግዚአብሔር ስራ እንዳልሆነ በዚህ የተጠቀሱትን መረጃዎችና የተያያዘውን ዜና በማንበብ የተሻለ መረዳትን ማግኘት ይቻላል።  ዘመኑ እጅግ አስፈሪ ነው። እግዚአብሔር ግን የሚታመኑበትንና ተስፋ የሚያደርጉትን በዚህ ሁሉ ውስጥ ይጠብቃል። ለምድር ሁሉ፣ በተለይም በአየር ንብረት ቀውስ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ ሁሉ እንጸልይ። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...