ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 3 እውነት መሆኑን የሚያሳይ የቴክኖሎጂ ግኝት

ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 3 እውነት መሆኑን የሚያሳይ የቴክኖሎጂ ግኝት
http://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-4898576/Scientists-transfer-light-sound-waves-world-first.html
የእግዚአብሔርን ታላቅነት፣ ኃይል፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ ክብርና ግርማ ከሚያሳዩን ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው እርሱ ሁሉን ነገር መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉን ነገር የፈጠረው በአፉ ቃል መሆኑ ነው። ቃልን በመናገር ብቻ ያልነበረውን ነገር ወደ መኖር የሚያመጣ ከእርሱ ሌላ ማንም የለም። በዘፍጥረት 1፡2 ላይ እንደምናየው ጌታ አምላክ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ ምድር ባዶ እንደነበረችና፣ ጨለማም በጥልቁ ላይ እንደነበረ ተጽፎአል። ቁጥር 3 ላይ ስንደርስ ደግሞ ጌታ አምላክ ቃልን ብቻ በመናገር ብርሃንን እንደፈጠረ እናያለን። ይህ ብርሃን እኛ የሰው ልጆችና ፍጡራን ሁሉ ልናየውና ልንጠቀምበት የምንችለው ብርሃን ነው። ይህ ብርሃን የተፈጠረው በመጀመሪያው ቀን ሲሆን፣ የተፈጠረውም ከጌታ አምላክ አፍ በወጣው ቃል ኃይል ብቻ ነው። ጸሃይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ደግሞ የተፈጠሩት በአራተኛው ቀን ነው። ስለዚህ የጌታ የአምላካችን ቃል ነው ብርሃንን የፈጠረው።
ብርሃን እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም፣ እስከ ዛሬ ድረስ የሰው ልጅ የሰራው ቴክኖሎጂ ግን ብርሃንን ገርቶ በሚገባ ሥራ ላይ ማዋል ያልቻለበት ዋነኛ ምክንያት ብርሃን እጅግ ፈጣን መሆኑ ነው። ብርሃን በአንድ ሰከንድ ውስጥ ከ 299,792 ኪሎሜትር በላይ ይሄዳል። ማለትም በአንድ ሰከንድ ውስጥ ብርሃን ምድርን ከሰባት ጊዜ በላይ ይዞራታል ማለት ነው። ታዲያ የሰው ልጅ ዛሬ የሚጠቀምባቸው እጅግ ፈጣን የሚባሉ ኮምፒውተሮች እንኳን ይህን ፍጥነት መድረስ ስለማይችሉ ብርሃንን ለመረጃ መሰብሰቢያ፣ ማጠራቀሚያ፣ ለስሌትና ለማሰራጫ ሊጠቀሙበት አልቻሉም። የዛሬዎቹ ኮምፒውተሮች የተሰሩባቸው ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች እጅግ ብዙ ኃይል የሚፈጁ፣ ከፍተኛ ሙቀት የሚያወጡና በማግኔታዊና የኤሌክትሮን ሞገድም በቀላሉ ሊታወኩ የሚችሉ በመሆናቸው አስተማማኝነታቸው ብዙ ጥያቄ አለበት።
ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ዜና ላይ እንደምናነበው፣ በአውስትራሊያ የሚገኘው የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ብርሃንን ወደ ድምጽ ለመለወጥ የሚያስችል መሳሪያ ሰርተዋል። ይህ መሳሪያ ብርሃንን ወደ ድምጽ ለአጭር ጊዜ ለውጦ ለማዘግየት መቻሉ ተዘግቦአል። የድምጽ ፍጥነት በሰከንድ 331 ሜትር ነው። ይህ ደግሞ የብርሃንን ፍጥነት 1/1000 ኛ ያህል ስለሆነ፣ አዲሱ ግኝት በሚገባ በስራ ላይ ሲውል የሰው ልጅ የብርሃንን ፍጥነት በመጠቀም አስተማማኝ ያልሆኑትን የዛሬዎቹን የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች ፎቶን በሚባሉት ትንንሽ አካላት በሚሰሩ መሳሪያዎች ሊለውጣቸው ይችላል የሚል ትልቅ ተስፋን ፈጥሮአል።
የዛሬው መልእክቴ ትኩረት ኤሌክትሮኒክስ፣ ፎቶንስ ወይም አዲሱ የቴክኖሎጂ እርምጃ አይደለም። የሰው ልጅ በምርምሩ ብርሃንን ዝግ አድርጎ ወደ ድምጽ በመቀየር ብርሃን መረጃን እንዲሸከምና ስራን እንዲሰራ ማድረጉ ለሁለት ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ይመሰክራል። 1ኛ) እግዚአብሔር ቃልን በመናገር ብቻ ብርሃንንና ዓለምን በሙሉ መፍጠሩ (ድምጽን ወደ ብርሃን፣ ቁስ አካላትና ሌሎችም የኃይል መልኮች መለወጡ) እውን መሆኑን፣  2ኛ) መጽሐፍ ቅዱስ የማይሳሳትና እንከን የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን። የእግዚአብሔር ቃል፣ ድምጽ፣ ብርሃንን ስለ ፈጠረው ነው የሰው ልጅ ብርሃንን ወደ ድምጽ በመለወጥ ዝግ ሊያደርገው የቻለው። ስለዚህ በአንድ መልኩ የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያደረጉት የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ኋላ ገልብጠው መቅዳት ነው ማለት  ይቻላል።  በኃጢዓት መታለልና በዲያብሎስ ሽንገላ መንፈሱ የታወረው የሰው ዘር እንደሚገባ አላስተዋለውም እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ገና የሰው ዘር መርምሮ ያልደረሰባቸውንና ሊደርስባቸው የማይችሉ ታላላቅ ምስጢሮችን ያዘለ ነው።
በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ላይ “እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ” ተብሎ የተጻፈው ቃል እውነት ከሆነ ሌላውም የመጽሐፍ ቅዱስ  በሙሉ እውነት ነው ማለት ነው። እነዚያ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደግሞ እኛ የሰው ልጆች በበደላችንና በኃጢዓታችን ፈጽመን እንደ ጠፋንና በራሳችንም ጥረት ከዘለዓለም ሞት ልንድን እንደማንችል በግልጽ ይነግረናል። (ገላትያ 2፡16)  ነገር ግን እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ታላቅ ፍቅሩ የተነሳ፣ አንድ ልጁን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመላክ፣ እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቃይቶ በመሞቱና በመነሳቱ በደሙ የገዛልንን ጽድቅ አምነን እና ተቀብለን የዘለዓለምን ሕይወት እንድናገኝ የምስራቹ ወንጌል ይነግረናል። ይህ ያለንበት በዓመጽ የተሞላ ዓለም ደግሞ ከክፋት ወደ ክፋት እየባሰ በመሄዱና በዚህም መንገድ ለዘላለም መቀጠል ስለማይችል ጌታ አምላክ በዘመኑ መጨረሻ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ እንደሚመጣ፣ በሕያዋንና በሙታን ላይ እንደሚፈርድና የዘለዓለም መንግስቱን እንደሚመሰርት ብሉይም ሆኑ አዲስ ኪዳን ያስተምሩናል። በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 22 ቁጥር 12 እና 13 ላይ እንዲህ ተጽፎአል፡ “እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፣ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ፣ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ኦሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”  ልንሰራው የሚገባ ዋነኛው ስራ ሊያድነን የመጣውን የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል ማመን ነው። “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሰራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስም መልሶ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው። “ ዮሐንስ 6፡28-29 ስለዚህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውና እኛንም ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚወስደን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማመን ነውና፣ ይህን ታላቅ ሥራ ዛሬ ነገ ሳንል እንፈጽም። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፣ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ዮሐንስ 3፡18

ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ምድራችን በብዙ ጥፋት እየተመታች ነው፣ የታላቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ፍራንክሊን ግራሃም ዓለም ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መዘጋጀት አለበት አሉ።

የታላቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ዓለም ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መዘጋጀት አለበት አሉ።


እንኳን እግዚአብሔር ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። አዲስ ዓመት ሲመጣ ሁላችንም አዲስ ነገርን ተስፋ እናደርጋለን። በምእራቡ ዓለም ያሉ ሰዎች አዲስ ዓመታቸው ሲገባ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን በማለት ከራሳቸው ቃል ኪዳን ይገባሉ። ክርስቲያኖች የሆንን ሁሉ በአዲሱ ዓመት በበለጠ ወደ እግዚአብሔር ለመጠጋት፣ እርሱን በበለጠ ለማወቅና ለመታዘዝ ብንሻ ያንን መሻት እግዚአብሔር ይሰጠናል ብዬ አምናለሁ። “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት፣ ጽድቁንም ፈልጉ፣ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” ማቴዎስ 6፡33 ተብሎ ተጽፎአልና። በዚህ በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር ይህንን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር እንድንፈልግ እግዚአብሔር ይርዳን።
በግል ሕይወታችንም ሆነ በአካባቢያችን፣ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ሁሉ በአዲሱ ዓመት የምንሰማው ዜና በሙሉ መልካም ቢሆን ምንኛ ደስ ይል ነበር? ለጊዜው ግን እውነታው እንዲህ አይደለም። ዳግም በመምጣቱ ሁሉን ነገር አዲስ የሚያደርገው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር እስኪገለጽ ድረስ መልካምና ክፉ ዜና እየተደባለቀ መስማታችን የግድ ነው። በተለይም ደግሞ የጌታችን ዳግም ምጽዓት ቀን እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ዘመን ምድራችን በብዙ ትግልና ጣር ውስጥ መሆኗን ለማየት ሩቅ መሄድ አያስፈልገንም። በደቡብ ሱዳን ሲነጉድ የከረመው ጦርነት፣ በሶማሊያ ላለፉት 26 ዓመታት ሶማሊያን ያፈራረሳት የእርስ በርስ ጦርነት፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ብዙ ህዝብ የፈጀውና አገሪቱን ያወደመው የየመን ጦርነት፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአገራቸው ያፈናቀለው የሶሪያ ጦርነት፣ እኤአ ከ2003 የጀመረውና እስከ ዛሬ ድረስ አገሪቱን እያፈራረሰ ያለው የኢራቅ ጦርነት፣ ላለፉት 16 ዓመታት ሳያቆም በአፍጋኒስታን የሚካሄደው ጦርነት ወዘተ ጦርነትን በተመለከተ ልንጠቅሳቸው ከምንችላቸው ጥቂቶቹ ናቸው።  ይህ የሚያውከን ከሆነ ደግሞ ከዚህ የበለጠና ዓለም እስከ ዛሬ ድረስ ያላየችውን ጥፋት ሊያመጡ የሚችሉ መፋጠጦች በኤኮኖሚና በወታደራዊ ኃይላቸው ታላላቅ በሚባሉት አገሮች መካከልም በየጊዜው እየተካረሩ እየሄዱ ናቸው በማለት ብዙ ታዛቢዎች ያስጠነቅቃሉ። ታላቂቷ አገር አሜሪካ ከሩሲያ፣ ከቻይና፣ ከሰሜን ኮሪያና ከኢራን ጋር የገባችባቸው እሰጥ አገባዎች ወደ ሰላም የሚያመሩ አይመስሉም። ምድር ፍጹም ሰላም ያገኘችበት ጊዜ አልነበረም የሚሉ የታሪክ ባለሙያዎች እንኳን፣ ዛሬ ዓለማችን ያለችበት ውጥረት ግን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እጅግ ውስብስብና ከባድ መሆኑን አይክዱም።
ዘማሪው ወንድማችን ደረጃ ከበደ “ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ፣ የሚሆነው በምድር ዙሪያ፣ እየከፋ ሲሄድ ጊዜው መሸሸጊያ ኢየሱስ ነው” የሚለውን መዝሙር ከዘመረ ከአርባ ዓመት በላይ ሆኗል። የዚያ መዝሙር እውነተኛ መልእክት ግን ከዚያን ጊዜ ይልቅ ዛሬ እውን እየሆነ ነው ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም። ሆን ብለን አናይም፣ አንሰማም ካላልን፣ ወይም ደግሞ ብዙ ክፉ ዜናዎችን ከመስማታችን የተነሳ ልባችን ካልደነደነ በስተቀር በዓለም ሁሉ ዙሪያ ጎልቶ የሚታየውና የሚሰማው ዜና መልካም አይደለም። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘው ድረ ገጽ ላይ እንደምታነቡት ባለፉት ሁለት ሳምንታት እንኳን የተከሰቱትና ከባድ የህዝብ እልቂትና የንብረት ውድመት ያስከተሉትን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ብቻ እንኳን ስንመለከት ምድራችን ወደሚያስፈራ ሁኔታ ውስጥ እንደገባች እንረዳለን። የሚቀርበው የጥፋት ዜና ሁሉ ሆን ብሎ ከትንቢተ ኤርምያስ ምእራፍ 50 እና 51፣ ከትንቢተ ዳንኤል፣ ከትንቢተ ኢዩኤል ምእራፍ 2፣ ከማቴዎስ ምእራፍ 24፣ ማርቆስ 13፣ ሉቃስ 21 እና ከዮሐንስ ራዕይ መልእክቶች ላይ ተወስዶ የተጻፈ ይመስላል። በእርግጥ ዛሬ የምናያቸው ነገሮች ከጌታ ዳግም ምጽዓት በፊት በሚከሰተው የታላቁ የመከራ ዘመን ውስጥ ከሚፈጸሙት እጅግ አስፈሪ ነገሮች ጋር ሊወዳደር ባይችልም፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ግን በከፍተኛ አደጋና ችግር ውስጥ በየእለቱ እየገቡ ናቸው። ምናልባት እኛ ባለንባቸው ስፍራዎች ሰላም ከሆነ እግዚአብሔር ያን እድል የሰጠን ለሌሎቹ እንድንጸልይ መሆኑን አንዘንጋ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የምድር አካባቢዎች ከተከሰቱት ከፍተኛ ጥፋቶች መካከል የሚከተሉትን ብቻ መጥቀስ ይበቃል፡
*      California በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Oregon በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Washington በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png British Columbia በሚባለው የካናዳ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Alberta is on fire በሚባለው የካናዳ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Montana is on fire በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Nova Scotia በሚባለው የካናዳ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በግሪክ አገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በብራዚል ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በፖርቱጋል ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በአልጀሪያ ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በቱኒሲያ ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው

https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Greenland በሚባለው አገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በሩሲያ Sakha Republic በሚባለው ግዛት ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Siberia በሚባለው አገር ብዙ ቦታዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f22/1/16/26c8.png Texas እና Florida በሚባሉት የአሜሪካ ክፍለ ሃገሮች ብዙ ቦታዎች በሞገድና በውሃ መጥለቅለቅ ወድመዋል፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰድደዋል፣ መብራት ጠፍቶ በጨለማ ውስጥ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f22/1/16/26c8.png 
በህንድ፣ ኔፓል፣ ፓኪስታንና ባንድላዴሽ እጅግ ከፍተኛና አደገኛ በሆነ ዝናብና ጎርፍ መጥለቅለቅ ብዙ ህዝብ አልቋል፣ ንብረት ወድሟል
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f22/1/16/26c8.png 
ሴራ ሊዮን እና ኒጀር በሚባሉት የአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ ጎርፍና የመሬት መደርመስ ብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ፈጅተዋል።
*                  ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ስፓኝ፣ ስዊዘርላንድ፣ ሃንጋሪ፣ ፖላንድ፣ ሮማኒያ፣ ቦስኒያ፣ ክሮኤሺያ እና ሰርቢያ የሚባሉት የአውሮፓ አገሮች እጅግ ከፍተኛና ከዚህ በፊት ከሆኑት በሚልቅ ሙቀት በመጠቃታቸው ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ከሙቀቱም ከፍተኛነት የተነሳ አንዳንዶች ሙቀቱን “ሉሲፈር” ወይም “ዲያብሎስ” ብለው ሰይመውታል።
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f5f/1/16/1f31e.png 
በተለምዶ አየሩ ቀዝቃዛ ነው በሚባልበት በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት ከሳንፍራንሲስኮ እስከ ሰሜን የክፍለ ሃገሩ ክፍሎች ድረስ የካሊፎርኒያ ግዛት ታይቶ በማይታወቅ ሙቀት እየተቃጠለ ነው።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
በአለም ትልቁ የሆነው የአሜሪካው Yellowstone volcano ይፈነዳል የሚል ትልቅ ፍርሃት አለ። ከሰኔ ወር ጀምሮ በዚህ የእሳተ ገሞራ አካባቢ 2,300 የሚሆኑ ትንንሽ የምድር መንቀጥቀጦች ተከስተዋል።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
አይዳሆ በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር 5.3 የሚለካ የምድር መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
ጃፓን በምድር ውስጥ ጥልቅ በሆነ 6.1 በሚለካ የምድር መንቀጥቀጥ ተመትታለች።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
ከ 50 በላይ ሰዎችን የፈጀና 8.2 የሚለካ የምድር መንቀጥቀጥ በሜክሲኮ ተከስቷል።
ባለፉት 12 ዓመታት ያልሆነና ከፍተኛ የሆነ ከጸሃይ የተወረወረ ጨረር ምድርን በመምታቱ በብዙ የዓለም ስፍራዎች የሬድዮ ሞገድን አቋርጧል፣ አቃውሷል።ከፍተኛነቱ X10 C.M.E ነው የሚባለው ይህ ሞገድ በምድር መንቀጥቀጥና በአየር ንብረት ላይም ከፍተኛ ተጽእኖ ማድረጉ ተዘግቧል።
እነዚህ ዜናዎች መልካም ወይም የሚያበረታቱ አይደሉም። ነገር ግን ሕይወቱን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰጠ ክርትሲያን እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአጋጣሚ የሚሆኑና ተስፋ የሚያስቆርጡ አይደሉም። ጌታ ከመመለሱ በፊት በምድር ላይ የግድ ሊሆኑ አላቸው። እነዚህን ሁሉና ሌሎችንም በዚህ መልእክት ያልተጠቀሱ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ነው የታላቁ ወንጌላዊ የዶ/ር ቢሊ ግራሃም ልጅ የሆኑት ፍራንክሊን ግራሃም ዓለም ሁሉ ለክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ሊዘጋጅ ይገባዋል ያሉት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲገለጽና በጽድቅ ሲነግስ ምድር ሁሉ በሰላም ታድራለች። ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ያንን ቀን በናፍቆት ይጠብቃል። ተግተን በመጸለይና የምስራቹን ወንጌል ላልሰሙት በማድረስ መቅረዛችንን በዘይት ሞልተን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠብቀው። በሁለንተናችን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጽ ዝግጁ እንድንሆን ጌታ አምላክ ጸጋውን ሁሉ ያብዛልን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።


የሰው ልጅ በተወሰነች እውቀቱ የእግዚአብሔርን ስራ እያመሳቀለ ብዙዎችን እያጠፋ ነው።


ከሶስት ቀናት በፊት ሃብታሞቹና ታላላቆቹ የምድር መንግስታት የምድርን አየር በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ በመቀየር ድርቅን፣ ጎርፍን፣ ማእበልንና ሌሎችም ምድርን የሚያጠፉ የአየር ንብረት ቀውሶችን ማምጣታቸው ወደ አደባባይ ከወጣ ውሎ ማደሩን የሚያሳዩ መረጃዎችን አካፍዬ ነበር። ከዚህ መልእክት ጋር አያይዤ የላክሁት የ ዩ-ቲዩብ ማገናኛ፣ በ70ዎቹ አሜሪካ በቬትናም ባደረገችው ጦርነት የጦር ኃይሏ የአካባቢውን የአየር ንብረት በመቀየስ ከፍተኛ ዝናብ፣ ጎርፍና ጥፋትን ታመጣ እንደነበር የሚያስረዱ ዘገባዎችን ይዟል። ተጨማሪ መረጃን የሚፈልግ ሰው ደግሞ “Operation popeye” ብሎ በመፈለግ የአሜሪካ የጦር ኃይልና የጦር መሳሪያ አምራቾች እንዲሁም ተኮናታሪዎች የአየር ንብረትን ምህንድስናን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀማቸው የአደባባይ ምስጢር መሆኑን ማየት ይችላል። ይህን ማገናኛ በመጠቀም ቪዲዮውን ተመልከቱት፡ https://www.youtube.com/watch?v=Cpr5JVWjIW4

ምናልባት ለዚህ ይሆን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ላይ ዳግም ምጽዓቱ ሲቃረብ በምድር ላይ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ የምድር መናወጥና ጦርነት እንደሚበዛ የተናገረው?  የአየር ንብረት ቀውስ አጥፊ ጎርፍን፣ ድርቅን፣ ረሃብን፣ ወረርሽኝና ሌሎች ጥፋቶችንም ይፈጥራል። ከሁለት ሳምንት በፊት በሃሪኬን ሃርቪ የተጥለቀለቀችው የሂዩስተን ከተማና ሌሎችም የቴክሳስ ግዛቶች ለምሳሌ ከአየሩ ሙቀትና ተኝቶ ካለው ውሃ የተነሳ ዛሬ በከፍተኛ የቢንቢ ወረርሽኝ ተቸግረዋል። ይህ ደግሞ ብዙ በሽታዎችን ሊያስከትል ይችላል።

በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በመካከለኛው አሜሪካ በሚገኙ ደሴቶችና በደቡባዊና ደቡባዊ ምስራቅ አሜሪካ ከፍተኛ ጥፋትን እያመጣች ያለችው ሃሪኬን ኢርማ ከ 600 ሺህ በላይ ሰዎች ከፍሎሪዳ ግዛት እንዲሰደዱ ባደረገችበት በዚህ ወቅት፣ ይህች ታላቅ ሞገድም ሆነ ከእርስዋ በፊት ብዙ የቴክሳስን ግዛቶች ያጠፋው ሃሪኬን ሃርቪ፣ የአየር ንብረት ጦርነትን በሚያካሂዱ ክፍሎች የተቀነባበሩ እንደሆኑ ብዙዎች እየዘገቡ ነው። ዋሽንግተን ፖስት የሚባለው ጋዜጣ እንኳን ሳይቀር፣ ይህች ሞገድ፣ ሃሪኬን ኢርማ፣ “በGPS ትመራ ይመስል በካሪቢያኑ ባህር ብዙ ደሴቶችን ካጠፋች በኋላ አሁን ደግሞ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትል ቀጭን በሆነውን የፍሎሪዳ የመጥበሻ መያዣ መሰል መሬት ላይ ወደ አሜሪካ እየገባች መሆኗን ታዝቦ ዘግቦአል።

ሃሪኬን ኢርማ ከምታመጣው ጥፋት ሁሉ እጅግ እየተፈራ ያለው ደግሞ በዚያው በፍሎሪዳ ግዛት የሚገኙ ሁለት የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎችን በመምታት የኑክሊየር ጥፋት ትፈጥር ይሆን የሚለው ሥጋት ነው። ሌሎች ደግሞ ከዚህም አልፈው ይህች ሞገድ ከነዚህም አልፋ በአካባቢው ያሉ እስከ አስራ ሁለት የሚደርሱ የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎችንም ትጎዳ ይሆናል ይላሉ።  ሃሪኬን ኢርማ እያጣች ካለችው ጥፋት ሰው ገና ሸሽቶ ሳይጨርስ ሌሎች ሁለት ሞገዶችም ከበስተኋላዋ እያደጉ እንደሆነ ተዘግቧል። ሁኔታውን ቀረብ ብለው የሚያጠኑ ባለሙያዎች ደግሞ የሁለቱ ትልልቅ ሞገዶች ስም ራሱ የሚያስገርምና ምናልባት፣ በአጋጣሚ የተሰጠ ላይሆን ይችላል ይላሉ። ከሁለት ሳምንት በፊት ቴክሳስን ያጠፋው HARVEY የሚለው ስም መሰረቱ ከፈረንሳይ ሲሆኑ ትርጉሙ “ተዋጊ” ወይም “ለጦርነት ዝግጁ፣ ብቁ የሆነ” ማለት ነው። አሁን ጥፋት እየሰራች ያለችው ሞገድ IRMA ስም ደግሞ መሰረቱ ጀርመንኛ፣ ትርጉሙም “በሙሉ፣ ጠቅላላ፣ ዓለም አቀፍ” ማለት ነው። ከሃርቪም ይልቅ ከፍተኛ ጥፋት ልታስከትል ስለምትችል ይህችን ሞገድ ብዙ አዋቂዎችና የመንግስት ባለስልጣናትም ሳይቀር “የኑክሊየር ሞገድ” በማለት ሰይመዋታል። 

በዛሬው እለት በሜክሲኮና መካከለኛው አሜሪካ የተከሰተው 8.2 የተገመተው የምድር መንቀጥቀጥም ከባህሩ ሞገድ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ ፍርሃትን ፈጥሮአል። በሜክሲኮ የሚገኙ እጅብ ብዙ ሰዎች ደግሞ የምድር መንቀጥቀጡ በሚካሄድበት ባለፈው ሌሊት ከየት እንደመጣ የማይታወቅ መብረቅ የሚመስልና ከፍተኛ ብርሃን በተደጋጋሚ ሰማዩን ሲያበራው በማየታቸው እንደታወኩ ገልጸዋል። የምድር መንቀጥቀጥም ሆነ የባህር ማእበል በየጊዜው የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ናቸው ብለን ብናስብም፣ በማያጠራጥር ምክንያት የአሜሪካና ሌሎች ጥቂት የጦር ኃይሎችና ተኮናታሪዎቻቸው የምድርን አየር እንደፈለጋቸው ለማወክ መቻላቸው ምስጢሩ የገባቸውን ብዙ ሰዎች እንቅልፍ የሚነሳ ነገር ሆኖአል።

የሰው ያገኘውን እውቀትና ቴክኖሎጂ በመጠቀም በሌሎች ላይ ጥፋትን ለማምጣት፣ ደካሞችን በማስፈራራትና በጉልበት ለመግዛት ሲሞክር ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ጌታ አምላክ በኖህ ዘመን የነበረውን ዘመንም በውሃ ያጠፋው እንዲህ እንደ ዛሬው በምድር ላይ ዓመጽ ስለ በዛ ነበር። በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 17 እና 18 የተጠቀሰችው፣ በተለይም ደግሞ በምዕራፍ 18 ላይ የተገለጸችው፣ ምድርን ሁሉ እንደፈለጋት እየረጋገጠች ትገዛ የነበረችውና በኋላም ከጥልቁ የሚወጣው አውሬና ተከታዮቹ የሚያጠፉአት ታላቂቲ ባቢሎን የዛሬዋ አሜሪካ ትሆን?! 


በዚህ ሁሉ መካከል የሰው ነፍስ ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ግን በዙፋኑ አለ። በእርሱ የሚታመኑ ሁሉ በማይናወጠው ዓለት በክርስቶስ ላይ የተመሰረቱ ስለሆኑ በምድር ላይ እየነፈሰ ያለው የዓመጽና የጥፋት ማእበል አያጠፋቸውም። ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ጌታ አምላክ ግን በጎቹን ለመጠበቅ አይተኛም፣ አያንቀላፋም፣ አይደክምም አይታክትም። ሁሉንም በጊዜው በክርስቶስ ውብ አድርጎ እንደገና ይሰራዋል። የጌታ ሰላምና ጸጋ ይብዛላችሁ። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

አሜሪካን እያጠፉ ያሉት ታላላቅ ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው ተባለ "ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ" ራዕይ 11፡18

አሜሪካን እያጠፉ ያሉት ታላላቅ ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው ተባለ

የሰሞኑ ታላላቅ የባህር ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው እየተባለ ነው
“ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ”። ይህ ቃል የሚገኘው በዮሐንስ ራዕይ ምእራፍ 11 ቁጥር 18 ላይ ነው። ከቁጥር 15-19 ያለውን ማንበብ ሙሉ ሃሳቡን ይሰጣል። በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ሰባት ማህተሞች ይፈታሉ፣ ሰባት መለከቶች ይነፋሉ፣ ሰባት ጽዋዎችም በምድርና በሰማይ ላይ ይፈስሳሉ። ሰባተኛው ማህተም ሲፈታ እግዚአብሔር ለዚህ ዓለም ፍጻሜ ያዘጋጀው ምስጢር ይፈጸማል፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ይነግሳል። ያ ሲሆን ደግሞ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ወደ መንግስቱ ዓመጸኞችም ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘለዓለም ጨለማ ይሄዳሉ። ዛሬ ይህን መልእክት እንድጽፍ ያስገደደኝ ነገር፣ “ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” የሚለውን ቃል ዛሬ በምድር ላይ እየተካሄደ ካለው ነገር ጋር በጥሞና ሳስተውለው የሰው ልጆች ምን ያህል ጉልበትና እውቀት ቢኖራቸው ነው ምድርን እስከ ማጥፋት ድረስ የደረሱት የሚል ጥያቄ መሙላቱ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ ምድርን እያወከ ስለሆነ ሃብታሞቹም ሆኑ ድሆቹ አገሮች ብዙ ስምምነቶችን ሲያደርጉ ከርመዋል። የኪዮቶ ፕሮቶኮል፣ በቅርቡ ደግሞ የፓሪስ ስምምነት። በመገናኛ ብዙኃን፣ በትምህርት ቤት፣ በየዩኒቨርሲቲዎቹና በመዋእለ ህጻናትም እንኳን ሳይቀር እኛ የሰው ልጆች የምናደርገው ግድ የለሽ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ምድርን እያጠፋ ስለሆነ እንድንጠነቀቅ ነው። ስለዚህም ሁላችንም የምንችለውን በማድረግ ይችን እግዚአብሔር የሰጠንን ምድር ለመንከባከብ ጥረት እናደርጋለን ይህንንም መቀጠል ያስፈልገናል።
ነገር ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የአደባባይ ምስጢር እየሆነ የመጣ ነገር አለ። ባለፉት ከአንድ መቶ በሚበልጡ ዓመታት የሰው ልጅ፣ በተለይም ደግሞ ሃብታምና ኃያል የሆኑት እንደ አሜሪካና ሩሲያ ያሉ አገሮች የአየር ንብረት ምህንድስና ሳይንስን በከፍተኛ ፍጥነት በማሳደግ የምድርን አየር ንብረት በሚፈልጓቸው ቦታዎች ላይ ለመቀየር የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደ ገነቡና ይህንንም ሲፈትሹ እንደኖሩ እጅብ ብዙ ማስረጃዎች ወደ አደባባይ ወጥተዋል። እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ደመና እንዲፈጠር፣ የተፈጠረ ትንሽ ደመና እንዲሰባሰብ፣ እንዲበዛና ወደሚፈለገው አቅጣጫ እንዲሄድ ለመግራት፣ ትልልቅ ሞገዶች (storms and hurricanes) እንዲፈጠሩ፣ የተፈጠሩት እንዲዳከሙ ወይም እንዲጠናከሩና ወደተፈለገበት አካባቢ እንዲሄዱ፣ በአንድ ስፍራ ድርቅ በሌላው ቦታ ደግሞ ከፍተኛ ጎርፍ እንዲፈጠር በማድረግ ብዙ ህዝቦችን የሚጨርሱ እኩይ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ በግልጽ እየተዘገበ ነው። ይህን ስራ የሚሰሩት ደግሞ የአሜሪካ መንግስት ወታደራዊና ሲቪል መስሪያ ቤቶች፣ የጦር መሳሪያ አምራቾች፣ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ባለቤቶችና ተኮናታሪዎች እንደሆኑ ብዙ መረጃዎች ያመለክታሉ። እነዚህ ሰው ሰራሽ በአካባቢና በዓለም የአየር ንብረት ላይ ቀውስ የሚፈጥሩ ምርምሮች፣ ሙከራዎችና ስራዎች እንደሚፈጸሙ ደግሞ ሁለቱም የአሜሪካ ምክር ቤቶች በግልጽ ያውቃሉ፣ ሪፖርቶችም ይቀርቡላቸዋል። እንዲያውም ምክር ቤቶቹና ብዙ የመንግስት ቢሮዎችም ለዚሁ ስራ የሚያስፈልገውን በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር በጀት ይመድባሉ። የአየር ንብረትን ለመቀየር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች  አሉ ወይ ብሎ የሚጠራጠር ካለ ደግሞ የአሜሪካን መንግስት የአእምሮ ውጤት ባለቤትነት (patent) መመዝገቢያ ቢሮ እጅግ ብዙ ለሆኑ ለእነዚህ ቴክኖሎጂዎች በየጊዜው ያደረገውን ምዝገባ ማየት ይበቃል። ይህንን መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ድረ ገጽ እንድትጎበኙ በትህትና እጋብዛችኋለሁ። http://www.geoengineeringwatch.org/
ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ዜናና ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱት፣ ባለፈው በኦገስት ወር መጨረሻ ላይ በደቡባዊ አሜሪካ የቴክሳስ ግዛት ላይ፣ በተለይም በሂዩስተን ከተማ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰው ከፍተኛ ሞገድ (hurricane Harvey) ከላይ በተጠቀሱት ቴክኖሎጂዎች ተቀነባብሮአል ተብሎ በከፍተኛ ደረጃ ይጠረጠራል። በዚያ ሞገድ የተጎዱ ህዝቦች ገና በቂ እርዳታ እንኳን አግኝተው ሳያበቁ አሁን ደግሞ ሌላ hurricane Irma የሚባልና ከሁለት ሳምንት በፊት ከተከሰተው እጅግ የሚከፋ ሞገድ በመምጣቱ በደቡባዊውና በምስራቃዊው አሜሪካ የሚገኙ ብዙ ክፍለ ሃገሮች በተጠንቀቅ ላይ ሲቆሙ፣ ብዙ ሰዎችም የሚመጣውን ጥፋት ፍራቻ ከቤታቸው እየተሰደዱ ይገኛሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴት የአሜሪካ የራሷ መንግስት ወታደራዊና ሲቢል ድርጅቶች፣ የጦር መሳሪያ አምራቾችና ተኮናታሪዎች እንዴት በራሷ በአሜሪካ ግዛት ላይ ጥፋት የሚፈጥር ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለው ጥያቄ ለእኔም ሆነ ለብዙዎች ለማመን የሚያዳግት ነው። ቀረብ ብለው በአሜሪካ ውስጥ ዛሬ ያለውን ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ለሚያጠኑ፣ ይች ታላቅ አገር በዓለም ዙሪያ የሚቃወሟትን መንግስታት በመገለባበጥና አገሮችን በማፈራረስ የምታደርገውን ለሚከታተሉ ታዛቢዎችና በአየር ንብረት ምህንድስና ላይ ከፍተኛ እውቀት ላላቸው ለራሷ ለአሜሪካ ባለሙያዎች ግን ይህ እንግዳ ነገር ወይም የማይታመን አይደለም።  አሜሪካ ያላትን ከፍተኛ የሳይንስና ወታደራዊና እውቀትና ቲክኖሎጂ በመጠቀም አየሩን እደሚፈልጉት በመለዋወጥ የራሷን የአገሪቱን ህዝብ በሚጎዳ መንገድ ይሰራሉ ተብለው በሰፊው የሚታሙት “ጥልቅ መንግስት” (deep state) የሚባለው ከተመረጡ የመንግስት ባለሥልጣናት በስተጀርባ የሚሰራው መዋቅር መሆኑንም ብዙዎች ይዘግባሉ።

በአሜሪካ ብቻ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የአየር ንብረትን ሊቀይሩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች የአእምሮ ባለቤትነት ሰርቲፊኬት ቁጥሮች በአሜሪካ መንግስት የpatent ቢሮ ድረ ገጽ ላይ ማየት ይቻላል።  በየጊዜው አየር ንብረትን ለመቀየር በሰማይ ላይ ስለሚረጩት ኪሚካሎችም (chemtrail) እጅብ ብዙ ማስረጃዎች በአደባባይ ይገኛሉ። የአሜሪካ ምክር ቤቶች ባለፉት ሰባ (70) ዓመታት የአየር ንብረትን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ እንደተፈለገው ስለመለወጥ ስለሚያስችሉ ስራዎች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ፕሮጀክቶች ብዙ ውይይቶችን አካሂደዋል፣ ሪፖርቶች ቀርበውላቸዋል፣ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፣ ህጎችንም አውጥተዋል። ይህን ሁሉ አስመልክተው ነው ብዙ አዋቂዎች ምድራችን ወደ ከፋ ጥፋት ውስጥ ከመግባቷ በፊት እያስጠነቀቁ ያሉት።  ታዲያ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለሚያውቅ ይሆን በመጨረሻው ቀን እሱ ውብና ድንቅ አድርጎ የሰራትን ምድርንና በላይዋ ላይ ያለውን ህይወት በግድየለሽነት፣ በስግብግብነትና በክፋት የሚያጠፉትን ሁሉ የሚፈርድባቸው? ለዚህ ይሆን ሃዋርያው ዮሐንስም “ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” የሚለውን የሃያ  አራቱን ሽማግሌዎች ቃል የሰማው? ሲነገረን እንደኖረው የአየር ንብረት ቀውስ ሁሉ የእግዚአብሔር ስራ እንዳልሆነ በዚህ የተጠቀሱትን መረጃዎችና የተያያዘውን ዜና በማንበብ የተሻለ መረዳትን ማግኘት ይቻላል።  ዘመኑ እጅግ አስፈሪ ነው። እግዚአብሔር ግን የሚታመኑበትንና ተስፋ የሚያደርጉትን በዚህ ሁሉ ውስጥ ይጠብቃል። ለምድር ሁሉ፣ በተለይም በአየር ንብረት ቀውስ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ ሁሉ እንጸልይ። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፣ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡16

ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፣ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡16


በምእራቡ ዓለም የሚገኙ ብዙዎች ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ከሚያውቁት ይልቅ፣ ስለ ፊልሞች፣ ዘፋኞች፣ ተዋናዮችና ታዋቂ የሚባሉ ሰዎች የሚያውቁት ይበልጣል። የብዙዎች የክርስትና እምነትም የሚወሰነው በሳምንት አንድ ወይም ቢበዛ ሁለት ጊዜ በጸሎት ቤት ወይም በቴሌቪዝንና በሬድዮ በሚሰሙት ላይ ነው። የቴሌቪዥን፣ ሬድዮ፣ ሲኒማ ቤት፣ ኢንተርኔትና ኮምፒውተር መምጣት ብዙ መልካም አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም፣ ብዙ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ቁጭ ብሎ ከማንበብና የወንጌልን እውነት በቀጥታ ከመረዳት ይልቅ በነዚህ መገናኛ ብዙኃን የሚቀርቡትን ብቻ ቁጭ ብሎ በመመልከት መንፈሳዊ ህይወታቸውን የሚገነቡ ይመስላቸዋል። በትክክለኛ መንገድ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስተምሩ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ገንቢ አገልግሎት አላቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ ማንበብ የሚችል ክርስቲያን የሰማውን ሁሉ ከመቀበሉ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ እውነቱን መፈተንና መመርመር ያስፈልገዋል። አስተማሪና የቤተክርስቲያን መሪ የሆነውን ጢሞቲዎስን እንኳን ሐዋርያው ጳውሎስ “እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ”  ይለዋል። 1ኛ ጢሞቲ 4፡13  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የዘመኑን አዋቂ ነን ባዮች ሰዱቃውያንን “መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል ስለማታውቁ ትስታላችሁ” አላቸው። ማቴዎስ 22፡29-33
ከዚህ መልእክት ጋር ከተያያዘው ሪፖርት እንደምትመለከቱት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ነን የሚሉ ብዙ የአሜሪካ የውሸት አስተማሪዎችና የውሸት መጋቢዎች በግልጽ የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃወም ትምህርትን እንደ እውነት ለማስተማርና ተከታዮቻቸውም እንዲቀበሉት ለማድረግ ተስማምተው ውል ፈርመዋል። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ተብሎ በግልጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሳለ፣ ሰው ወንድና ሴት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብዙ ጾታዎችም ሊኖሩት  ይችላሉ፣ ሰው ሲፈልግ ወንድ ሲፈልግ ሴት፣ ሳይፈልግ ደግሞ ከሁለቱም የተለየ፣ ወይም ሁለቱንም ወይም ምንም ጾታ የለኝም ማለት ይችላል፣ ጋብቻ ደግሞ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ ሳይሆን ሰዎች እንደ ፈለጉት ሊያደርጉት የሚችሉ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም መቀበል አለባት የሚል ትምህርትን የሚያጸድቅ ቃል ኪዳንን ተፈራርመዋል። በዚሁ በፈረንጆቹ አመት የካናዳ መንግስትም አንድ ህጻን ሲወለድ  ወንድ ወይም ሴት ብቻ ሳይሆን ጾታው ያልተወሰነም ሊሆን ይችላል ብሎ፣ በትውልድ መረጃ እና በፓስፖርት ላይ እንኳን ወንድም ሴትም ያልሆነ የሚባል ሶስተኛ ጾታን ፈጥሮአል። ከላይ የተጠቀሱት ሃሰተኛ አስተማሪዎች ደግሞ ከዚህም አልፈው ተርፈው የነርሱን የመርገም ፍልስፍናና ትምህርት እንደ አዲስ የመንፈስ ቅዱስ መገለጽ በማቅረብ፣ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሩትን ክርስቲያን መሪዎችና አስተማሪዎች ራእይ የሌላቸውና ኋላ ቀሮች ናቸው በማለት በግልጽ እያሳጡ ይገኛሉ።
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍቅር የቀመሱና የእግዚአብሔርን ቃል ተረድተው ለጌታ በመታዘዝ ሕይወት የሚመላለሱ ክርስያኖች ሁሉ በዚህ ዜና ሊደነግጡ አይችሉም። ምክንያቱም ይህ የትንቢት ፍጻሜና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓቱ ስለተቃረበ የግድ ሊሆን የሚገባው ነገር ነው። ነገር ግን ማንም የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ። ዛሬ የሐሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ እንደ ድሮው በስውር ሳይሆን በግልጽ በምድር ላይ እየሰራ ነው። በ2ኛ ተሰሎንቄ ምዕራፍ 2 ላይ እንደ ተጻፈው መቼ ለይቶለት እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚቀመጥ ቀኑን ባናውቅም፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነን፣ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተን ነው እያሉ የእግዚአብሔርን ቃልና መሰረታዊ የተፈጥሮ ህግጋትን  የሚጻረሩ ነገሮችን ክርስቲያኖች እንዲቀበሉ የሚያስተምሩ እነዚህ የሃሰተኛው ክርስቶስ መንገድ ጠራጊዎች መሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም። ምክንያቱም ያ ዐመጸኛ የመገለጹ አንዱ ምልክት የእግዚአብሔርን ህግጋት ለመለወጥ መሞከሩ ነው። ትንቢተ ዳንኤል 7፡25።
እንንቃ ! መጽሐፍ ቅዱሳችንን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስር ሆነን እናንብብ እና እናጥና። ከእውነተኛ ክርስቲያኖችና የቤተ ክርስቲያን መሪዎቻችን ጋር ያለንን ህብረት እናጠንክር። የምንሰማውና የምናምነው ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር የሚስማማ መሆኑን እናረጋግጥ። እምነትና በክርስቶስ ደም የታጠበ በጎ ህሊና ካለን ከቃሉ ቃር የሚጻረረውን የሃሰትና የአጋንንት ትምህርት መለየት እንችላለን። ይህ ወቅት ግን የትእግስትና የጽናት ጊዜ ነው። በእውነተኛ ክርስቲያን ላይ ያለው ሰልፍና ጦርነት ዛሬ የሚመጣው ከሩቅ ሳይሆን በተያያዘው ሪፖርት ላ  እንደምታነቡት ክርስቲያንና መሪዎች ነን ከሚሉ ነው። እግዚአብሔር ግን ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል። ከእግዚአብሔር በክርስቶስ ዳግም የተወለደም ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ሆኖ ስለሚመሰክርለት የእግዚአብሔር መሆኑን ያውቃል። ከሁለት ሺህ ዓመታት ያህል በፊት ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ከተናገረ፣ እኛ ደግሞ የሚታየውን ሁሉ እያየንና እየሰማን በእርግጥም ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ መድረሱን እናውቃለን።
ልባችን አይታወክ። ሌሊቱ ሊነጋ ሲል ጨለማው ይከብዳል እንዲሉ፣ በምድር ላይ ዓመጻው ይክበድ እንጂ፣ የነገስታት ንጉስና የጌቶች ጌታ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድንገት ከተፍ ይላል። የዓለም መንግሥት ሥልጣንም ሁሉ የእርሱ ሊሆን ቀኑ ቅርብ ነው።  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በቅንነት በሚወዱና በሚያመልኩት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ሰላም ይሁን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።


ከእግዚአብሔር የተላከ ምልክት አይዋሽም

ከአስራ ሁለት ቀናት በፊት “ሰማያት እየተናገሩ ናቸው” በሚል ርዕስ ሥር በኦገስት 21 በአሜሪካና በካናዳ ላይ ስለሚከሰተው ታላቅ የጸሃይ ግርዶሽ የሚናገር ዜናን በማያያዝ መልእክት አስተላልፌ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስና ታሪክ እንደሚነግረን የጸሃይና የጨረቃ ግርዶሾች እግዚአብሔር አምላከ ለህዝቦችና ለመንግስታት ሊመጣ ስለሚችል ጥፋት ከሚናገርባቸው፣ ህዝቡን ወደ ንስሃ ከሚጠራባቸውና ማስጠንቀቂያ ከሚሰጥባቸው መንገዶች አንዱ ናቸው። ባለፈው መልእክቴ ውስጥ ከአሜሪካውያን ክርስቲያኖች ወገኖቻችን ጋር በመንፈስ አንድ በመሆን ምድሪቱም ከዓመጻዋ ንስሃ እንድትገባና ወደ እግዚአብሔር እንድትመለስ እንድንጸልይ አሳስቤ ነበር።
ባለፉት ብዙ ቀናት በዜና አውታሮች እንደሰማችሁትና ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው አንድ ዜና ላይ እንደምታነቡት፣ የጸሃይ ግርዶሹ ከዋለ ከአራት ቀናት በኋላ ጀምሮ ሃርቪ የተባለው ታላቅና ታሪካዊ ወጀብ ቴክሳስ ወደ ሚባለው የአሜሪካ ግዛት ገብቶ በአሜሪካ ታሪክ እስከ ዛሬ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ዶፍ  ለአምስት ቀናት ያህል በተከታታይ በማውረድ ከፍተኛ ጥፋት እየፈጠረ ይገኛል። http://endtimeheadlines.org/2017/08/harvey-costliest-natural-disaster-u-s-history-160-billion/
ብዙ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቤተሰቦች ተበታትነዋል ብዙዎች ቤታቸውን ትተው ተሰደዋል፣ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ደግሞ ከላይ፣ ከታች፣ ከፊትና ከኋላ በከፍተኛ ጎርፍና ውሃ ሙላት ተከበዋል። የሞተው፣ የቆሰለውና የት እንዳለ የማይታወቀው ሰው ቁጥር ገና በቅል አይታወቅም። ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ሪፖርት ላይ እንደምናነበው፣ ይህ ወጀብ የፈጠረው ታላቅ ውድመት ከዚህ በፊት በአሜሪካ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ተብሏል። በንብረትና በአገሪቱ ኤኮኖሚ ላይ ላይ ይህ ወጀብ ያደረሰው ውድመት በ2005 እና በ2012 ተፈጥረው የነበሩት ካትሪና እና ሳንዲ የተባሉት ሁለት ታላላቅ ወጀቦች በድምር ከፈጠሩት ውድመት እንደሚበልጥና የአሜሪካንንም የዓመት ኢኮኖሚ (GDP) በ ነጥብ ስምንት ከመቶ እንደሚጎዳው ተዘግቦአል።
ወጀብ፣ ማእበል፣ ድርቅ፣ የአየር ንብረት መዛባትና ሌሎችም የተፈጥሮ አደጋዎች በየጊዜው የሚከሰቱ ናቸው ቢሉንም፣ ሁሉም ነገር የሚሆነው በአጋጣሚ ብቻ ነው የሚለው ድምዳሜ ግን እግዚአብሔርን የሚያምኑ ሰዎች በቀላሉ የሚቀበሉት አይደለም። ከላይ የተጠቀሰውን ታላቅ ወጀብ ስናስብ እጅግ የሚያስገርመው ደግሞ ከዚያው ከቴክሳስ ግዛት ብዙም ሳይርቅ የሚገኘው የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ግዛት በበኩሉ እንደ እሳት በሚያቃጥል ሙቀትና በከፍተኛ ድርቅ እየተመታ መሆኑ ነው። ሊሰማ ለሚወድ ሁሉ ጥፋት ከመምጣቱ በፊት እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ደግሞና ደጋግሞ ይናገራል። በተለይም ደግሞ በከተማዎችና በአገር ላይ የሚመጣ ጥፋት እንዲሁ በአጋጣሚ የሚሆን አይደለም። ትንቢተ አሞጽ ምዕ 3 ቁ 6፣ መዝሙረ ዳዊት ምዕ 127 ቁ 1-2። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት እየተቃረበ በመጣ ቁጥርም ማእበሉና ወጀቡ ይበረታል፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ፣ ድርቅ፣ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ ጦርነትና ሁከት በምድር ሁሉ እየበዛ እንደሚሄድ በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 24፣ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21፣ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 13 እና በሌሎችም ስፍራዎች መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።  የኖህ ዘመንን ዝናብ በሚመስል ታሪካዊ ዝናብ ስፋቱ ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ የሆነ የበረሃማውን የቴክሳስን ግዛት በማጥለቅለቅና ከአሜሪካ ታላላቅ ከተሞች በአራተኛነት ደረጃ ላይ ያለችውን የሂውስተንን ከተማ ያንበረከከው ሃሪኬን ሃርቪ የፈጠረውን ጉዳት ስናስብ፣ ይህ አደጋ ከመፈጠሩ ከራት ቀናት በፊት የነበረውን የሰማያትን ማስጠንቀቂያ እናስታውስ። በዚያን ቀን ብዙ ሰዎች ግርዶሹን እንደ ማስጠንቀቂያ ከመውሰድ ይልቅ፣ ድግሶችን በማዘጋጀት አሸሸ ገዳሚ ይሉ እንደነበር በሰፊው ተዘግቧል። እኛም ለየራሳችን ከተማዎች፣ ለወገኖቻችን፣ ለያለንባቸው አገሮችም እንጸልይ። በስሙ የተጠራን ህዝቡ በፊቱ ወድቀን ንስሃ ብንገባና ከኃጢዓታችንም ሁሉ ብንመለስ እግዚአብሔር በደላቸንን ሁሉ  ይቅር እንደሚልና ያለንባቸውን ከተማዎች፣ መንደሮች፣ ማህበረሰቦችና አገሮች እንደሚፈውስ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። 2ኛ ዜና 7፡14 ሰማያትም፣ የምድር ኃይላትም እየተናገሩ ናቸው። የሚሰማ ጆሮንና የሚመለስ ልብን እግዚአብሔር ለሁላችንም ይስጠን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።


የሰው ዘር ዛሬ እንኳን ያልደረሰበት የሂሳብ እውቀት ከዛሬ 3700 ዓመታት በፊት በምድር እንደነበረ ማስረጃ ቀረበ

የሰው ዘር ዛሬ እንኳን ያልደረሰበት የሂሳብ እውቀት ከዛሬ 3700 ዓመታት በፊት በምድር ላይ እንደነበረ ማስረጃ ቀረበ
ከ 17ኛውና 18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በየትምህርት ቤቱና በየዩኒቨርሲቲው በሚሰጡት ትምህርቶች ውስጥ ቀስ በቀስ ስር በመስደድ የገቡት፣ በሳይንስና በእድገት ስም የአጋንንትን ትምህርት የሚያራምዱ እውቀቶች ዛሬ የሰው ልጅ ያለበት መንፈሳዊ፣ ሞራላዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ማህበረሰባው ምስቅልቅል ውስጥ ከትተውታል። ዘለዓለማዊ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምረውን የፍጥረትን ታሪክ ለመሻር የተነሱት እነዚህ ትምህርቶች የጥንቱ ሰው ኋላ ቀር፣ ያልተማረ፣ ውስብስብ የሆኑ ሳይንሳዊና የቴክኖሎጂ ነገሮች የማይገቡት እንደነበረ ሲያስተምሩ ምንም እፍረት አይሰማቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እውነት፣ እውነተኛውን የዓለም ታሪክና በየጊዜውም እያመለጡ የሚወጡትን የአርኪዎሎጂ ምርምር መረጃዎችን ቀረብ ብለን ከተከታተልን ግን፣ ዛሬ ብዙ ምሁራን እና የሰለጠንን ነን ብለው የሚያምኑ ሰዎች የሚናናፍሱት የዘገምታ ለውጥ (ወይም ኢቮሉሽን) የሚባለው በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠ የአጋንንት ትምህርት መሆኑን እንረዳለን።
የማይገለጥ የተሰወረ፣ የማይታወቅም የተከደነ የለም ተብሎ እንደተጻፈው እውነት ሁሉ በጊዜው በአደባባይ ይገለጻል። ከዚህ አጭር መልእክት ጋር ተያይዞ የሚገኘው ጽሁፍ እንደሚያሳየው፣ የተራቀቀ የሂሳብ እውቀት የመነጨው እስከ ዛሬ ድረስ ሲነገረን እንደኖረው ከግሪኮች፣ ከሮማውያን ወይም ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ፣ ከጃፓን ወይም ከቻይናም አይደለም። 3700 ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ከጥንቱ የባቢሎን ግዛት የተገኙ የሸክላ ሰሌዳዎች እንደሚያመለክቱት በዚያን ዘመን የነበሩ ሰዎች ውስብስብ የሆኑ የህንጻ ቅየሳና፣ የህዋ ምርምርን እንዲሁም ሌሎች ውስብስብ የሂሳብ ስሌቶችን በማድረግ የሚሰሩ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችላቸው እውቀት ነበራቸው የሚለው ሃሳብ በማስረጃ እየተደገፈ መጥቷል። ታዲያ ይህን ያህል የተራቀቀ እውቀት በዚያ ከጥፋት ውሃ በፊት በነበረው ዘመን ጀምሮ ከነበረ፣ እውቀቱ በምድር ሁሉ ያልተሰራጨውና አብዛኛው የምድር ህዝብ በኋላ ቀርነት ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ የቆየው ለምንድን ነው የሚል ጥያቄ መነሳቱ የግድ ነው።
የአርኪዎሎጂ ምርምሩን የሚያካሂዱት ምሁራን ራሳቸው እንደሚያመለክቱት ደግሞ እነዚያ የጥንት ሰዎች ይህን የመሰለ የተራቀቀ የሂሳብ እውቀትን ቤተ ጣዖቶቻቸውንና ቤተ መንግስቶቻቸውን ለመስራት ይጠቀሙበት ነበር። ማለትም በዚያም ዘመን ቢሆን ብዙ ህዝቦች እውነተኛውን አምላክ ክደው ባእድ አማልክትን ያመልኩ ነበር። እነዚያ ባእድ አማልክት የግብጾቹ አይሲስና ኦሳይሪስ፣ የባቢሎኖቹ ማርዱክ፣ በአል፣ ቤል፣ አስታሮት፣ የግሪኮችና የሮማውያኑ አፖሎ፣ ሄርኩለስ፣ ዙስ፣ ዳያና፣ አርጤምስ፣ ቪነስ ወዘተ እነማን ነበሩ? ጠለቅ ያለ ጥናትን ለማድረግና ለዚያም የሚያስፈልገውን መስዋእትነት ለማድረግ ዝግጁ ከሆንን፣ የጥንት ህዝቦችም ሆኑ ዛሬ በምድር ሁሉ ያሉ ባእድ አማልክት የሚያመልኩ ህዝቦች የሚሰግዱት ለድንጋይና ለእንጨት ወይም ለብረት ሃውልቶች ሳይሆን በነዚያ ሃውልቶች የተመሰሉትን በኖህ ዘመን በጥፋት ውሃ የጠፉትን ረዓይት መንፈሶች (አጋንንትን) መሆኑን ልንረዳ እንችላለን። ዛሬ በሃውልትና በተለያዩ ቁሳቁስ የሚመሰሉት አጋንንት በግሪክ፣ በሮም፣ በባቢሎን፣ በፋርስ በግብጽና ሌሎችም የጥንት ግዛቶች ሲመለኩ የነበሩት እነዚያ “በጥንቱ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን” ናቸው የሚለው ሃሳብ ዛሬ በብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ታሪካዊ መረጃዎች እየተደገፈ የመጣ ሃሳብ ነው። ይህን ዓይነት ምርምርና እውቀት ለክርስትና ህይወታችን ምን ያደርግልናል ብለን ከጠየቅን ደግሞ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚናገረው ነገር አለ ወይ ብለን መመርመሩ አስፈላጊ ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 6፣ 7 እና 8 ስለ ኖህ ዘመንና ስለ ጥፋት ውኃ የሚያስተምረንን ረጋ ብለንና በቅርብ ካጤንነው የእግዚአብሔር ልጆች (BNAI ELOHIM) የሚባሉ የሰውን ሴቶች ልጆች በወሰዱና ልጆች በወለዱላቸው ጊዜ ኔፊሊም የሚባሉ እንደተወለዱ እንመለከታለን። እነዚያ ኔፊሊም ደግሞ በዘመኑ የታወቁ ኃያላን ነበሩ። መሰረታዊው የእብራይስጡ ትርጉም ኃያላን የሚለውን ቃል “ሃጊቦሪም” ይለዋል። ይህ ቃል ደግሞ መታወቅን፣ ወኔንና ጀግናነትን ብቻ ሳይሆን እነዚያ ፍጥረታት በአካልም ከሰዎች የተለዩ ግዙፍና ጉልበተኞች እንደነበሩም ይጠቁማል። በጣም የሚያስገርመው ነገር ደግሞ፣ ልክ እነዚህ ኔፊሊም በምድር ላይ መብዛት ሲጀምሩ ነበር የሰው ልጆች ደግሞ መንገዳቸውን በምድር ላይ ያበላሹትና የእግዚአብሔርን ታላቅ ቁጣ ያነሳሱት። እውቀት በመብዛቱ ክፋትና ዓመጽ ለምን በዛ? የእውቀት መብዛት ለዓመጽ መነሳሳትና መሰራጨት አስተዋጽኦ አድርጎ ነበር ወይስ ሁለቱም በአጋጣሚ ነው የተከሰቱት? እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚሰጠው እውቀትና ጥበብ ሁሉ ሰውን ወደ ጽድቅ፣ ወደ ፍቅርና ወደ እውነት እንዲሁም ወደ ዘላለም ህይወት ብቻ የሚመራ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል። ስለዚህ የኖህን ዘመን ህዝብ ያጠፋው እውቀትና ስልጣኔ መሰል ስህተት ምንጩ እግዚአብሔር ሳይሆን በኤደን ገነት የመጀመሪያውን ውሸት ለሰው ልጅ ያስተማረው እባቡ ነው።
ከዚሁ ሃሳብ ጋር ተያይዞ ልብ ልንለው የሚገባ ነገርም አለ። ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሰው ልጅ በአስገራሚ ፍጥነት ከፍተኛ የሳይንስና የቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ ገብቶአል። ነገር ግን በዚሁ እጅግ ሰለጠንን በምንልበት ዘመን ደግሞ የሰው ዘር በከፍተኛ ሞራላዊ ውድቀት ውስጥ ተዘፍቆአል፣ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እጅግ ስር ሰድዶአል። ፈሪሃ እግዚአብሔር መሬት ላይ ተጥሎአል። ወንዶች በወንዶች፣ ሴቶች በሴቶች ጋር ነውር ማድረግ እንደ ቀላል በሚቆጠርበት በዚህ ዘመን፣ ሰው ወንድ ይሁን ወይም ሴት እንኳን ለመለየት እጅብ ብዙዎች ግራ ተጋብተው ይገኛሉ። ገና ተጫውተው ያልጨረሱ ህጻናት ትልልቅ ነን በሚሉ ሰዎች እየተደፈሩ ህይዋተቸው የምድር ሲኦል እየሆነ ነው። እንደ ኖህ ዘመን እውቀትና ስልጣኔ በዝቶአል በሚባልበት ዘመን የመንፈሳዊና ሞራላዊ ውድቀት በሰው ልጅ ላይ የበዛው በአጋጣሚ ይሆን?!  ብዙ ምርምሮችና መረጃዎች ይህ በአጋጣሚ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ምናልባት እነዚያ በኖህ ዘመንና ከዚያም በኋላ በምድር ላይ ነበሩ የተባሉት ኔፊሊም ዛሬም እንደገና በስውር በምድር ላይ እየሰሩ ይሆን?!! በማርች 2017 የወጣው የመለከት ድምጽ መጽሔት ቁጥር 5 (አምስት) በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያሉ ሃሳቦችንና መረጃዎችን ይሰጣል። መጽሔቱን ከሚከተለው የመለከት ድምጽ ብሎግ አድራሻ ላይ ማግኘት ይቻላል።  http://voice-of-trumpet-amharic.blogspot.ca ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።



ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...