የኖህ፣ የሰዶምና የገሞራ ዘመን
ያለንበት ዘመን የጥንቱን የኖህን ዘመን እንደሚመስል፣ ሰልጥኗል፣ በልጽጓል በሚባለው ዓለም የሚሰራው ኃጢዓት፣ ዓመጽና በህብረተሰብ መካከል የሚታየው ጭካኔ ከሰዶምና ገሞራ ዘመን የማያንስ ነው። ታላላቆቹ የዜና አውታሮች የሚያሳዩን ዜና ይህ ሰለጠነ፣ በቴክኖሎጂ ረቀቀ ስለሚባለው ዓለም የፊልምና የሙዚቃ ኮከቦች፣ ስለ ልዑላንና ታዋቂ ሰዎች ብልጽግናና ስኬት፣ ስለ አገር መሪዎች ክፉ ስራና ሌሎችም ውሃ የማያነሱና እንደ ነፋስ የሚያልፉ ወሬዎች ነው። ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ ግን መከራቸውን ለመግለጽ አቅም የሌላቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወንዶችና ሴቶች ልጆችና ትንንሽ ህጻናት ክፉና አጋንንታዊ የዝሙት መንፈስ በተጸናወታቸው ሰዎች ይደፈራሉ፣ እንደ አሻንጉሊት የእርቃንነት ፎቶአቸው እየተነሳ ይሸጣል፣ ብዙዎችም በአሳዛኝና አሰቃቂ ሁኔታ ይገደላሉ። ከዚህ መልእክት ጋር የተያያዘው ዜና የሚናገረው ስለ ድሃና ያልሰለጠኑ አገሮች ሳይሆን፣ በምድር ላይ በሃብቷና በስልጣኔው እንዲሁም በቴክኖሎጂ ከሁሉም የላቀች ነች በምትባለውና የሌሎች አገሮችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ በምትተቸውና በምትነቅፈው በአሜሪካ ነው። በትክክል ስራ ላይ ቢውል ለሰው ልጅ እድገትና የኑሮ መሻሻል ይበጃል የሚባልለት ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በተለይም ደግሞ ከ1980ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋው የመረጃ ማጠናቀሪያና፣ ማከማቻና ማንሸራሸሪያ ቴክኖሎጂ (ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ) ለብዙ ወንጀሎች፣ ጭካኔዎችና የሰው ልጅ ክፉ ምኞቶች ማስፋፊያና መሸፋፈኛ መሆኑ የማያጠራጥር ሆኗል። ድንበር የለሽ የወሲብ ስሜትን የሚቀሰቅሱና ብዙ ታላላቅ ሰዎችን፣ መሪዎችን፣ ክርስቲያኖችንና አገልጋዮችንም ጭምር ያዋረዱ አሳፋሪ ፊልሞችና ቪዲዮዎች በአብዛኛው የሚመነጩት ከአሜሪካ መሆኑ ስውር አይደለም። ዛሬ በዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ (ኢንተርኔት) በሰፊው የተንሰራፋውና ፖርኖግራፊ በመባል የሚጠራውን ጋጠ ወጥ የፍትወተ ስጋ ስራዎችን የሚያስፋፋው ኢንዱስትሪ ለባለቤቶቹ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ትርፍን ያስገኛል። በሌላው ወገን ግን ይህ ቸነፈር ስፍር ቁጥር የሌለውን ትዳር ያፈርሳል፣ ቤተሰብን ይበትናል፣ የወጣቶችንና ጨቅላ ህጻናትን ህይወት ይቀጫል፣ ትልልቅ ሰዎችንም ሳይቀር ያዋርዳል። ከሁሉም በላይ የሚያስከፋው ግን በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ህጻናት መደፈር፣ መንገላታትና በአሰቃቂ ሁኔታ መሞት ነው። የተያያዘው የአሜሪካው የፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ የሚያሳየው በሶስት ወራት አሰሳ ብቻ ከ2300 በላይ የሆኑና በህጻናት ላይ በሚደርሰው ወሲባዊ ጥቃት የሚጠረጠሩ ሰዎች መያዝ የችግሩ ጫፍ ብቻ እንደሆነና ሁኔታው ከዚህም የከፋ እንደሆነ ብዙዎች ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች ይናገራሉ። የመዝናኛው፣ የዘፈኑና የፊልም ኢንዱስትሪው በዚህ ጉዳይ የተጨማለቀ መሆኑ መሆኑ ስውር አይደለም። ስለዚህ እኛም ሆን ልጆቻችን የምናየውንና የምንሰማውን እንምረጥ። የልጆች ማጫወቻ የሚመስሉ ብዙ ቪዲዮዎች፣ ፊልሞች፣ የቴሌቪዝን ቅንጅሮችና የኮምፒውተር ፕሮግራሞች (አፕስ) እንዲሁም መጽሔቶችና መጻህፍት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ልጆችንና አዋቂዎችን በረቀቀ መንገድ ወደ ኃጢዓትና አጋንንታዊ ዓመጽ ለመሳብ የታቀዱና የተዘጋጁ ናቸው። ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረንና እንዳስጠነቀቀን (ማቴዎስ 18፡8-9፣ ማርቆስ 4:24) እኛም ሆን ልጆቻችን ምን እንደምናይና ምን እንደምንሰማ እንጠንቀቅ። መስማት የሚያስፈልገን ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ሳይሆን እውነቱን ሁሉ ነው። ያለንበ ዘመን በብዙ መንገድ የኖህን ዘመን፣ የሰዶምና የገሞራን ዘመን ይመስላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ባላሰብነው ቀንና ሰዓት ከተፍ ይላል። ነቅተን ልብሳችንን እንጠብቅ። አምላካችን ፍጹም፣ ጻድቅና እውነተኛ ነውና ሲመጣ ተኝተን ወይም ከጸጋው ርቀን፣ ራቁታችንን እና ከነውር ጋር እንዳንገኝ ዛሬውኑ ልብሳችንን እንጠብ፣ ወደ እርሱ እንመለስ፣ እንቀደስ፣ ላለንበት ህብረተሰብም የመልካም ባህርይና ህይወት ምሳሌ እንሁን። በዚህ ክፉ ዘመን እግዚአብሔር እርሱን ብቻ የሚፈራና ለቃሉና ለመንፈስ ቅዱስ እምጽ የሚታዘዝ ልብን ይስጠን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
You are here
JUSTICE NEWS
Department of Justice
Office of Public Affairs
FOR IMMEDIATE RELEASE
Tuesday, June 12, 2018
More Than 2,300 Suspected Online Child Sex Offenders Arrested During Operation “Broken Heart”
The Department of Justice today announced the arrest of more than 2,300 suspected online child sex offenders during a three-month, nationwide, operation conducted by Internet Crimes Against Children (ICAC) task forces. The task forces identified 195 offenders who either produced child pornography or committed child sexual abuse, and 383 children who suffered recent, ongoing, or historical sexual abuse or production of child pornography.
The 61 ICAC task forces, located in all 50 states and comprised of more than 4,500 federal, state, local and tribal law enforcement agencies, led the coordinated operation known as “Broken Heart” during the months of March, April, and May 2018. During the course of the operation, the task forces investigated more than 25,200 complaints of technology-facilitated crimes against children and delivered more than 3,700 presentations on Internet safety to over 390,000 youth and adults.
"No child should ever have to endure sexual abuse," Attorney General Jeff Sessions said. "And yet, in recent years, certain forms of modern technology have facilitated the spread of child pornography and created greater incentives for its production. We at the Department of Justice are determined to strike back against these repugnant crimes. It is shocking and very sad that in this one operation, we have arrested more than 2,300 alleged child predators and investigated some 25,200 sexual abuse complaints. Any would-be criminal should be warned: this Department will remain relentless in hunting down those who victimize our children."
The operation targeted suspects who: (1) produce, distribute, receive and possess child pornography; (2) engage in online enticement of children for sexual purposes; (3) engage in the sex trafficking of children; and (4) travel across state lines or to foreign countries and sexually abuse children.
The ICAC Program is funded through the Department’s Office of Juvenile Justice and Delinquency Prevention (OJJDP). In 1998, OJJDP launched the ICAC Task Force Program to help federal, state, and local law enforcement agencies enhance their investigative responses to offenders who use the Internet, online communication systems or computer technology to exploit children. To date, ICAC Task Forces have reviewed more than 775,000 complaints of child exploitation, which resulted in the arrest of more than 83,000 individuals. In addition, since the ICAC program's inception, more than 629,400 law enforcement officers, prosecutors and other professionals have been trained on techniques to investigate and prosecute ICAC-related cases.
For more information, visit the ICAC Task Force webpage at: https://www.icactaskforce.org/. For state-level Operation Broken Heart results, please contact the appropriate state ICAC task force commander. Contact information for task force commanders are available online at: https://www.icactaskforce.org/Pages/ContactsTaskForce.aspx.
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ