የሮማው ሊቀ ጳጳስ ሲኦ የለም አሉ


የሰውን ዘር በኃጢዓት ምክንያት ከሚሆነው የዘለዓለም ሞት፣ እርሱም ሲኦል ወይም የእሳት ባህር ለማዳን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተቀበለውን መከራና ሞት እንዲሁም ትንሳኤውን በዓለም ሁሉ ያሉ ክርስቲያኖች በሚያስቡበት በዚህ በህማማት ሳምንት የሮማው ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ሲኦል የለም ብለው ማወጃቸው በካቶሊኳ ቤተ ክርስቲያንና በሌሎችም የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ማእበልን ቀስቅሶአል። “እግዚአብሔር የለም” ባይ ወይም ATHEIST የሆነ የረጅም ጊዜ ወዳጃቸውና ላ ሬፑብሊካ የሚባለው ጋዜጣ መስራች ሚስተር ኢዩጄኒዮ ስካልፋሪ ነበር እኒህ ትልቅ የሃይማኖት መሪ የሚመስሉ ሰው ይህን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚቃረን፣ የራሳቸውን የካቶሊክን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና ከሁለት ቢሊዮን በላይ የሆነውን ህዝበ ክርስቲያን እምነት የሚጻረር የተሳሳተ ትምህርት በአደባባይ የተናገሩት፣ ለዚያውም ወንጌልን ሊሰብኩለት ለሚገባ እግዚአብሔር የለም ባይ ሰው። ኢዩጄኒዮ ስካልፋሪ በበኩሉ “እርስዎ አብዮተኛ ወይም ተራማጅ ነዎት” ብሎ የክህደትና የስህተት ትምህርታቸውን ሲያደንቅላቸው ደግሞ “ተራማጅ ወይም አብዮተኛ መባሉ ትልቅ ክብር ነው” በማለት ነበር የተቀበሉት። ታዲያ ሲኦል ከሌለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ሞተ? ለነገሩማ እኮ እኒህ የዛሬ አምስት ዓመት (MARCH 19 2013)  በአሜሪካና በብዙ የምእራባውያን አገሮች ድጋፍ እንዲሁም በCNN፣ በBBC በ HOLYWOOD እና በሌሎችም የመገናኛ ብዙኃንና የመዝናኛ ተቋማት ጻድቅነታቸውና ዝናቸው ተናፍሶላቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስልጣን ላይ የወጡት ሰው እንዲህ ያሉ መጽሐፍ ቅዱስንና የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚጻረሩ ነገሮች ሲናገሩ ውለው አድረዋል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያሉት ብዙ መሪዎችም ይህንኑ ጉዳይ እያስመለከቱ ሰውየው ቫቲካንን እና የካቶሊክን ምእመናን ወደ ስህተት እየመሩ ነው በማለት ሲጮሁና ሲያስጠነቅቁ ሰንብተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት የሚያጠኑ ብዙ መምህራንና በራሷ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ያሉ አንዳንድ መሪዎች አባ ፍራንሲስ ሲናገሩአቸው የከረሙት የተሳሳቱ ትምህርቶች በአጋጣሚ የተከሰቱ ሳይሆኑ የሰውየውን ማንነትና ሊያከናውኗቸው የሚሹትን ነገሮች የሚያንጸባርቁ ናቸው ይላሉ። አንዳንዶች ከዚህም አልፈው ምናልባት ሰውየው ዓለምን ሁሉ ሊያስትና ሊገዛ ላለው ለሃሳዊው መሲህ መንገድ ጠራጊ ወይም ጭራሹኑ በዮሐንስ ራእይ ምእራፍ 13 ላይ የተገለጸው ሃሰተኛው ነቢይ ሊሆኑ ይችላሉ በማለት ጽፈዋል። የዚህ አጭር መልእክቴ ዓላም አንድና አንድ ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ እንደሚያስተምረው የኃጢዓት ደሞዝ የዘለዓለም ሞት ነው። የዘለዓለም ሞት ማለት ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የኃጢዓትን ይቅርታ ካገኙ ሰዎች በስተቀር የማያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ክብር ተለይተው በዘለዓለም ጨለማ፣ እሳቱ በማይጠፋ ትሉ በማያንቀላፋ ሲኦል (ማርቆስ 9:48) መውደቅ ማለት ነው። እኒህ ሰው በፈቀዳቸው ስልጣን ይቀመጡ ወይም የፈቀዳቸውን ታዋቂነት ያግኙ የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ሊለውጡት አይችሉም። ስቅለት ብለን በምናከብረው በዚህ እለተ አርብ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የለምን ሁሉ የኃጢዓት እዳ ሊከፍልና ሰዎችን ሁሉ ከሲኦልና ከዘለዓለም እሳት ለማዳን በመስቀል ላይ ሞቷል፣ ሞትን ደግሞ ድል አድርጎ በሶስተኛው ቀን ተነስቷል። የሚያምኑትን ሁሉ ወዳዘጋጀው የዘለዓለም የክብር ህይወት ይዞ ለመግባትና በማያምኑት ሁሉ ላይ ሊፈርድ ዳግም ተመልሶ ይመጣል። ያ ዳግም ተመልሶ የሚመጣበት ጊዜ እጅግ ስለተቃረበ ነው ዛሬ እንደ አባ ፍራንሲስ ካሉ የቤተ ክርስቲያን መሪ ከሚባሉ በዓለም ፊት ትልልቅ ሰዎች የክህደትን ቃል እየሰማን ያለነው። ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ (ማለትም ዓለምን ሁሉ በማታለል የሚገዛው ሃሰተኛው መሲህ) ሳይገለጥ የጌታ ዳግም ምጽዓት አይሆንም ተብሎ በ2ኛ ተሰሎንቄ 2 ቁጥር 3 እስከ 12 ተጽፎአል። ነቢዩ ዳንኤል በምእራፍ 7፣23 እስከ 28፣ በምእራፍ 9 ቁጥር 27 እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 24 በማርቆስ ወንጌል ምእራፍ 13 በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 17 እና ምእራፍ 21 እንዲሁም  በዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 5 ቁጥር 43 ላይ ዳግም ከመምጣቱ በፊት በምድር ላይ የሚሆኑትን ነገሮች፣ የሃሰተኞች ነቢያትና የሃሰተኞች ክርስቶሶችን መምጣት በተመለከተ በዝርዝር አስተምሮአል፣ አስጠንቅቆአልም። ያ የዘመን መጨረሻ ይህ ያለንበት ቀን ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ስለዚህ እንንቃ፣ በመጠን እንኑር፣ ወንጌልን እንስበክ እንጂ አንደናገጥ። በእርግጥም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል፣ ያም ዘመን ቀርቦ በደጅ ነው። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ከሰውና ከሮቦት ልጆች እንዲወለዱ የሚያስችል "ቴክኖሎጂ" ተፈጥሮ እየተፈተሸ ነው። ለዚህ ይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛውን ክርስቶስን "የዓመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ" የሚለው?

ከሰውና ከሮቦት ልጆች እንዲወለዱ የሚያስችል "ቴክኖሎጂ" ተፈጥሮ እየተፈተሸ ነው። ለዚህ ይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛውን ክርስቶስን "የዓመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ" የሚለው?
ከሰውና ከሮቦት ልጆች እንዲወለዱ የሚያስችል "ቴክኖሎጂ" ተፈጥሮ እየተፈተሸ ነው። ለዚህ ይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛውን ክርስቶስን "የዓመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ" የሚለው? ዜናው ለማመን ያስቸግራል፣ ነገር ግን እውነት ነው። በተለያዩ አደጋዎች መቁሰል ለደረሰባቸው፣ በድንገተኛ የደም ግፊት አደጋ (STROKE) አንጎላቸው ለተበላሸ፣ በህመም ወይም በእርጅና ለተጎዱ ህዋሳት መጠገኛ ይሆናል ተብሎ በኦሃዮ (Ohio State's College of Engineering እና Ohio State University Wexner Medical Center) የተሰራው TNT (Tissue Nano Transfection) የሚባለው ቴክኖሎጂ በአሳማዎችና በአይጦች ላይ ተፈትሾ 98 በመቶ እንደሚሰራ ተረጋግጧል። የዚህ ቴክኖሎጂ መገኘት ደግሞ በቅርቡ ሮቦቶች ከማንኛውም ወንድ ወይም ሴት የተወሰዱ የቆዳ ህዋሳትን (Cells) በዚህ ቴክኖሎጂ በማመሳቀል የወንድና የሴት አባለ ዘር መስራት እንደሚችሉ 2017 በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ ላይ ያመለከቱት OHIO State የሚገኘው Center for Regenerative Medicine and Cell Based Therapies የተባለው ማእከል ዲሬክተር ዶክተር ቻንዳን ሴን (Chandan Sen) ናቸው። ይህም ማለት ከአንድ ሰው ወይም ሴት ቆዳ ላይ የተወሰዱ ሴሎች በዚህ ቴክኖሎጂ ከተለወጡ በኋላ የወንድም የሴትም ዘር ሊወጣቸው እንደሚችልና እነዚያ በከፊል ሰው ሰራሽ አባላተ ዘር ደግሞ ተደባልቀው ወደ ኪራይ ማህጸን ወይም ሰው ሰራሽ ማህጸን ገብተው በማደግ "ሰው" ሆነው ሊወለዱ ይችላሉ ማለት ነው። በአጭሩ ልጅን ለመውለድ የግድ አባትና እናት፣ ወይም ወንድና ሴት አያስፈልጉም ማለት ነው። ከአንዱ ሰው ወይም ከአንዲት ሴት ቆዳ ላይ የተወሰዱ CELLS ብቻ DNA ጥንቅራቸው ተለውጦ የወንድና የሴት ዘር ሊወጣቸው ነው። የተጸነሱ ልጆች አያስፈልጉም ተብሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጽንሶች ሆን ተብለው በማስወረድ በሚገደሉበት በዚህ ዘመን ለምን ይሆን የሰው ልጅ እንደዚህ ባለ የአምላክን ስራ በሚዳፈርና በሚያራክስ ዓመጽ የተሰማራው? ስንቱ ቤተሰብ ልጆቹን በሚገባ የሚያሳድግበት አቅም አጥሮት በሚታገልበት ዘመን፣ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የሚፈስስባቸው ምርምር ተብዬዎች የሚካሄዱት ለምን ይሆን? እነዚህንና ከነዚህ ጋር የተያያዙ ረቂቅ ምርምሮችን፣ ቴክኖሎጂዎችንና የመጨረሻውን ዘመን የሚመለከቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ከላይ የተጠቀሰውና ሌሎችም ተዛማጅ ምርምሮችና ቴክኖሎጂዎች መጽሐፍ ቅዱስ የዓመጽ ሰው፣ ወይም የጥፋት ልጅ የሚለውን፣ ሐሰተኛውን ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም ለማምጣት በጨለማው ገዢና ተከታዮቹ የሚደረገው ጥረት አካል ነው ብለው ያምናሉ። የሐሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ ከጥልቁ የሚወጣ ሲሆን፣ (ራዕይ 17:8-14) ግሩም ድንቅ ሰው ነው ተብሎ የዓለም ህዝብ እንዲቀበለውና እንዲሰግድለት ደግሞ የሰው አካል መልበስ አለበት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለና የነበረው እግዚአብሔር ወልድ ሆኖ ሳለ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም የሰውን ስጋ ለብሶ እንደተወለደ ሁሉ፣ ሃሰተኛው ክርስቶስ ደግሞ እንደ ክርስቶስ ያለ አባት ነው የተወለድሁት ብሎ ለማውራት እንዲችል ምናልባት ሰይጣን ይህን ከላይ የተጠቀሰውን “ሰው ሰራሽ” የሚመስል የዓመጽ መንገድ ሊጠቀም ይችላል በማለት እነዚሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ተመራማሪዎች ያስረዳሉ። የሃሰተኛው ክርስቶስ አመጣጥ በሰይጣናዊ ጥበብና ተንኮል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።2ኛ ተሰሎንቄ 2፡7-12 የሰው ልጅ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን ሰርቶ ለመልካም አውሏል። ዛሬ ግን ቴክኖሎጂ ሰውን ከማገልገል ይልቅ የሰውን ዘር ለማጥፋትና ሰውም እርሱን እንዲያገለግለው ሊያስገድድ ወደሚችልበት ሰዓት ላይ ደርሰናል። ከሰው በላይ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ነገር ሁሉ ደግሞ አምላክ ለመሆን ከመሻት የሚያግደው የለም። ከምናስበው ይልቅ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምጽዓት እየተቃረበ መጥቷል። ቀኑንና ሰዓቱን አናውቅም። ነገር ግን ቶሎ ቶሎ ብለን የምስራቹን ወንጌል ላልሰሙ ሁሉ እናድርስ። ሙሽራው በድንገት በሚገለጽበት ጊዜ ተኝተን እንዳንገኝ እኛም እንንቃ፣ እንትጋ፣ እንጸልይ፣ ዘመኑን እንመርምር። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...