ከሰውና ከሮቦት ልጆች እንዲወለዱ የሚያስችል "ቴክኖሎጂ" ተፈጥሮ እየተፈተሸ ነው። ለዚህ ይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛውን ክርስቶስን "የዓመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ" የሚለው?

ከሰውና ከሮቦት ልጆች እንዲወለዱ የሚያስችል "ቴክኖሎጂ" ተፈጥሮ እየተፈተሸ ነው። ለዚህ ይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛውን ክርስቶስን "የዓመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ" የሚለው?
ከሰውና ከሮቦት ልጆች እንዲወለዱ የሚያስችል "ቴክኖሎጂ" ተፈጥሮ እየተፈተሸ ነው። ለዚህ ይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛውን ክርስቶስን "የዓመጽ ሰው፣ የጥፋት ልጅ" የሚለው? ዜናው ለማመን ያስቸግራል፣ ነገር ግን እውነት ነው። በተለያዩ አደጋዎች መቁሰል ለደረሰባቸው፣ በድንገተኛ የደም ግፊት አደጋ (STROKE) አንጎላቸው ለተበላሸ፣ በህመም ወይም በእርጅና ለተጎዱ ህዋሳት መጠገኛ ይሆናል ተብሎ በኦሃዮ (Ohio State's College of Engineering እና Ohio State University Wexner Medical Center) የተሰራው TNT (Tissue Nano Transfection) የሚባለው ቴክኖሎጂ በአሳማዎችና በአይጦች ላይ ተፈትሾ 98 በመቶ እንደሚሰራ ተረጋግጧል። የዚህ ቴክኖሎጂ መገኘት ደግሞ በቅርቡ ሮቦቶች ከማንኛውም ወንድ ወይም ሴት የተወሰዱ የቆዳ ህዋሳትን (Cells) በዚህ ቴክኖሎጂ በማመሳቀል የወንድና የሴት አባለ ዘር መስራት እንደሚችሉ 2017 በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ ላይ ያመለከቱት OHIO State የሚገኘው Center for Regenerative Medicine and Cell Based Therapies የተባለው ማእከል ዲሬክተር ዶክተር ቻንዳን ሴን (Chandan Sen) ናቸው። ይህም ማለት ከአንድ ሰው ወይም ሴት ቆዳ ላይ የተወሰዱ ሴሎች በዚህ ቴክኖሎጂ ከተለወጡ በኋላ የወንድም የሴትም ዘር ሊወጣቸው እንደሚችልና እነዚያ በከፊል ሰው ሰራሽ አባላተ ዘር ደግሞ ተደባልቀው ወደ ኪራይ ማህጸን ወይም ሰው ሰራሽ ማህጸን ገብተው በማደግ "ሰው" ሆነው ሊወለዱ ይችላሉ ማለት ነው። በአጭሩ ልጅን ለመውለድ የግድ አባትና እናት፣ ወይም ወንድና ሴት አያስፈልጉም ማለት ነው። ከአንዱ ሰው ወይም ከአንዲት ሴት ቆዳ ላይ የተወሰዱ CELLS ብቻ DNA ጥንቅራቸው ተለውጦ የወንድና የሴት ዘር ሊወጣቸው ነው። የተጸነሱ ልጆች አያስፈልጉም ተብሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጽንሶች ሆን ተብለው በማስወረድ በሚገደሉበት በዚህ ዘመን ለምን ይሆን የሰው ልጅ እንደዚህ ባለ የአምላክን ስራ በሚዳፈርና በሚያራክስ ዓመጽ የተሰማራው? ስንቱ ቤተሰብ ልጆቹን በሚገባ የሚያሳድግበት አቅም አጥሮት በሚታገልበት ዘመን፣ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የሚፈስስባቸው ምርምር ተብዬዎች የሚካሄዱት ለምን ይሆን? እነዚህንና ከነዚህ ጋር የተያያዙ ረቂቅ ምርምሮችን፣ ቴክኖሎጂዎችንና የመጨረሻውን ዘመን የሚመለከቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ከላይ የተጠቀሰውና ሌሎችም ተዛማጅ ምርምሮችና ቴክኖሎጂዎች መጽሐፍ ቅዱስ የዓመጽ ሰው፣ ወይም የጥፋት ልጅ የሚለውን፣ ሐሰተኛውን ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም ለማምጣት በጨለማው ገዢና ተከታዮቹ የሚደረገው ጥረት አካል ነው ብለው ያምናሉ። የሐሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ ከጥልቁ የሚወጣ ሲሆን፣ (ራዕይ 17:8-14) ግሩም ድንቅ ሰው ነው ተብሎ የዓለም ህዝብ እንዲቀበለውና እንዲሰግድለት ደግሞ የሰው አካል መልበስ አለበት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለና የነበረው እግዚአብሔር ወልድ ሆኖ ሳለ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም የሰውን ስጋ ለብሶ እንደተወለደ ሁሉ፣ ሃሰተኛው ክርስቶስ ደግሞ እንደ ክርስቶስ ያለ አባት ነው የተወለድሁት ብሎ ለማውራት እንዲችል ምናልባት ሰይጣን ይህን ከላይ የተጠቀሰውን “ሰው ሰራሽ” የሚመስል የዓመጽ መንገድ ሊጠቀም ይችላል በማለት እነዚሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ተመራማሪዎች ያስረዳሉ። የሃሰተኛው ክርስቶስ አመጣጥ በሰይጣናዊ ጥበብና ተንኮል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።2ኛ ተሰሎንቄ 2፡7-12 የሰው ልጅ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን ሰርቶ ለመልካም አውሏል። ዛሬ ግን ቴክኖሎጂ ሰውን ከማገልገል ይልቅ የሰውን ዘር ለማጥፋትና ሰውም እርሱን እንዲያገለግለው ሊያስገድድ ወደሚችልበት ሰዓት ላይ ደርሰናል። ከሰው በላይ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ነገር ሁሉ ደግሞ አምላክ ለመሆን ከመሻት የሚያግደው የለም። ከምናስበው ይልቅ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምጽዓት እየተቃረበ መጥቷል። ቀኑንና ሰዓቱን አናውቅም። ነገር ግን ቶሎ ቶሎ ብለን የምስራቹን ወንጌል ላልሰሙ ሁሉ እናድርስ። ሙሽራው በድንገት በሚገለጽበት ጊዜ ተኝተን እንዳንገኝ እኛም እንንቃ፣ እንትጋ፣ እንጸልይ፣ ዘመኑን እንመርምር። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...