በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ ዕብራ 12፡2
የክርስቲያን ሕይወት ሩጫ ነው። የዚህ ሩጫ መነሻው እምነት፣ መድረሻው ተስፋ ሲሆን በሁለቱ መካከል ሯጩ እንዳይዝልና ተስፋ እንዳይቆርጥ የሚያደርገው ደግሞ ተመሳሳይ የሌለውን ለመረዳት እጅግ የሚያዳግተው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። እነዚህ ሶስት ነገሮች፣ እምነት፣ ተስፋና እና ፍቅር ጸንተው ይኖራሉ ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው ይለናል የእግዚአብሔር ቃል። በመንገድ ላይ የሚገጥሙን ፈተናዎችና መከራዎች ብዙ ሊሆኑ ቢችሉም፣ የተሰጠንን ተስፋ እስክናገኝ ድረስ ሩጫችንን ያስጀመረን እግዚአብሔር ሊያስጨርሰን ከእኛ ጋር ነው። እነዚህን ሃሳቦች ሰፋ ባለ መንገድ የሚቃኘው የመለከት ድምጽ መጽሔት ቁጥር 10 ዛሬ ወጥቶአል። ቅጂውን ከታች የተሰጠውን ማገናኛ በመጫን ወይም ደግሞ ከመለከት ድምጽ ብሎግ በመቅዳት እንድታነቡትና ሌሎችም እንድታካፍሉ ተጋብዛችኋል። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ