የኢሉሚናቲን ምስጢር የሚያሳዩ ዘግናኝ የባእድ አምልኮ ልብሶችና ጌጦች እንደ ፋሽን በለንደን ከተማ ቀረቡ ተባለ።
በመጨረሻው ዘመን መጨረሻ ላይ መሆናችንን ገና ለሚጠራጠሩ ብዙ ማስረጃዎች በግልጽ ወደ አደባባይ እየወጡ ነው። ከዛሬ ጥቂት ዓመታት በፊት እንኳን "ኢሉሚናቲ" የሚባል የምስጢር ድርጅት አለ ብሎ የሚያወራ ምንም እንደማያውቅ ወይም መሰረት የሌለውን የሴራ ወሬ የሚያምን ሰው ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ኢሉሚናቲ ማለት በላቲን ቋንቋ "የበራላቸው" "የተገለጸላቸው" "ሰው የማይውቀውን ትልቅ ምስጢር የሚያውቁ" ወዘተ ማለት ነው። በዚህ ስም ስር የታቀፉ እጅግ ብዙ የምስጢር ድርጅቶች አሉ። የነዚያ ድርጅት አባላት በምድር ላይ ታላላቅ፣ ሃብታም፣ ዝነኛ፣ ባለስልጣን፣ ዘፋኞች፣ ተዋናዮች ናቸው። በዚህ ልንደነቅ አይገባም። ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሰይጣንን "የዚህ ዓለም ገዥ" ብሎ በተደጋጋሚ በወንጌል ላይ ጠርቶታል። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክነት (ወልድነት) እና ፍጹም ሰው ሆኖ መምጣቱን፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ በመስቀል ላይ መሞቱን፣ በሶስተኛው ቀን መነሳቱ፣ በክብር ማረጉንና ዳግም ተመልሶ መምጣቱን ከሚያምኑ ክርስቲያኖች በስተቀር ዓለም በሙሉ ዛሬ የሚገዛው በዚህ ዓለም ገዥ በዲያብሎስ ነው። ይህን ዲያብሎስ ነው በተለያየ ስም እያሽሞነሞኑ ትልቅ ምስጢር አድርገው ሊያቀርቡልን የሚሹት። የኢሉሚናቲ አባላትና አጃቢዎቻቸው ያውቁታል የሚባለው ትልቅ ምስጢር ደግሞ "ሉሲፈር" ወይም "ዲያብሎስ" አምላክ ነው ብለው መቀበላቸውን ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈው ውጭ አንድም አዲስ ነገር ወይም ምስጢር የለም። በኤደን ገነት ሄዋንን እና አዳምን ያሳተው ያ የቀደመው እባብ በየዘመናቱ በተለያየ ስም የሰውን ዘር ሲያታልል ቆይቶ አሁን ደግሞ ታዋቂ፣ ሃብታም፣ ዝነኛና ባለ ስልጣን በሚባሉ ሰዎች በመጠቀም የሰውን ዘር እንደ ኖህ ዘመን፣ እንደ ሰዶምና ገሞራ ለሳትና ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቷል። መጽሐፍ ቅዱሱን የሚያነብ ክርስቲያን ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ከመገለጡና የዘላለም መንግስቱን ከመመስረቱ በፊት ሃሰተኛው ክርስቶስ (ሃሳዊው መሲህ) እንደሚገለጽና ብዙዎችን እንደሚያስት ሊረዳ ይችላል። ይህ ያለንበት ዘመን ሃሳዊው መሲህ ሊገለጽ እጅግ የተቃረበበት ጊዜ ነው። ለዚህ ነው ብዙ አስፈሪና ዘግናኝ ነገሮችን እየሰማንና እያየን ያለነው። በተያያዘው ዜና ላይ እንደምናየው፣ ድሮ ልጆች ሆነን ወላጆቻችን ጭራቅ እያሉ ሲነግሩን የነበሩት አስደንጋጭና አስፈሪ ነገሮች ሁሉ ዛሬ ፋሽን ተብለው በአደባባይ፣ ለዚያውም በለንደን ከተማ በሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ ሲቀርቡ ማየት የማይጠበቅ ቢሆንም፣ ዓለማችን ወደ ምን ዓይነት መንፈሳዊ ዝቅጠትና ጨለማና ውስጥ እየገባች እንዳለ ያስረዳል። አባቶቻችን ነቢያትና ሐዋርያት ወዮ እያሉ የተነበዩት ዘመን ውስጥ መሆናችንን የሚያመለክተው ከዚህ መልእክት ጋር የተያያዘው ዜና ብቻ አይደለም። ጦርነትና የጦርነት ወሬ፣ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ ማእበል፣ የምድር መናወጥ፣ ህዝብ በህዝብ ላይ፣ መንግስትም በመንግስት ላይ መነሳታቸው የየዕለት ዜና ከሆነ ውሎ አድሮአል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል እንደተናገረው ይህ ጊዜ የንስሐ ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ከክፉ መንገዳችን ሁሉ ልንመለስና የወንጌሉን መልእክት ተቀብለን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መዳናችንን የምናረጋግጥበት ጊዜ ነው። እግዚአብሔር ወልድ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ "እኔ መንገድና እውነት ሕይትም ነኝ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።" ዮሐንስ 14፡7 ብሎ ተናግሮአል። ሐዋርያቱም "መዳንም በሌላ በማንም የለም፣ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና" የሐዋርያት ሥራ 4፡12 ብለው ነግረውናል። ሁሉ ነገር እንዳለ ይቀጥላል በማለት ተዘናግተን እንደ ኖህ ዘመን ሰዎች ስንበላና ስንጠጣ ከዘለዓለማዊው የነፍሳችን ነገር ተዘናግተን የጌታ ቀን በድንገት እንዳይደርስብን እንንቃ። እንደዚህ ዜና፣ በዓለም ላይ የሚሆነው ክፉ ነገር ሁሉ ሊያነቃን እንጂ ሊያስደነግጠን አይገባም። በእርግጥ የሚያስፈራውና የሚያስደነግጠው ግን ንስሃ ገብተን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ታርቀን ሳንዘጋጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊፈርድ ተመልሶ የመጣብን እንደ ሆነ ነው። እግዚአብሔር ዘመኑን የምንለይበትና እርሱን በንስሃ በመፈለግ ወደ እርሱ የምንመለስበትን ልብ ይስጠን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
የመለከት ድምጽ ብሎግ የአማርኛን ቋንቋ በተቀዳሚነት ለሚጠቀሙ ሰዎች በሙሉ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የወንጌል የምስራች ለማድረስ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ክርስቲያኖች ደግሞ መሰረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ለማስተማር ያገለግላል።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ
በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...
-
የኖኀ ዘመን ፥ ኔፊሊም እነማን ናቸው? ከየት መጡ? ምን አደረጉ? ፍጻሜያቸውስ? ትምሕርት 5 ዘፍጥረት ምዕራፍ 6 “በዚያን ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ...
-
የኖህ ዘመን እንደነበር የጌታ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፡ ኔፊሊም ከየት መጡ? ከሰው ሴቶች ልጆች የወለዷቸው እነዚያ “የእግዚአብሔር ልጆች” የተባሉት እነማን ናቸው? ትምሕርት 6 ባለፉት 5 ትምህርቶች ጌታ ኢየሱስ...
-
በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግም መወለድ ማለት ምን ማለት ነው? ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ፣ May 6, 2018 አንድ ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግም ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊ...
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ