ምድራችን በብዙ ጥፋት እየተመታች ነው፣ የታላቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ፍራንክሊን ግራሃም ዓለም ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መዘጋጀት አለበት አሉ።

የታላቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ዓለም ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መዘጋጀት አለበት አሉ።


እንኳን እግዚአብሔር ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። አዲስ ዓመት ሲመጣ ሁላችንም አዲስ ነገርን ተስፋ እናደርጋለን። በምእራቡ ዓለም ያሉ ሰዎች አዲስ ዓመታቸው ሲገባ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን በማለት ከራሳቸው ቃል ኪዳን ይገባሉ። ክርስቲያኖች የሆንን ሁሉ በአዲሱ ዓመት በበለጠ ወደ እግዚአብሔር ለመጠጋት፣ እርሱን በበለጠ ለማወቅና ለመታዘዝ ብንሻ ያንን መሻት እግዚአብሔር ይሰጠናል ብዬ አምናለሁ። “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት፣ ጽድቁንም ፈልጉ፣ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” ማቴዎስ 6፡33 ተብሎ ተጽፎአልና። በዚህ በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር ይህንን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር እንድንፈልግ እግዚአብሔር ይርዳን።
በግል ሕይወታችንም ሆነ በአካባቢያችን፣ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ሁሉ በአዲሱ ዓመት የምንሰማው ዜና በሙሉ መልካም ቢሆን ምንኛ ደስ ይል ነበር? ለጊዜው ግን እውነታው እንዲህ አይደለም። ዳግም በመምጣቱ ሁሉን ነገር አዲስ የሚያደርገው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር እስኪገለጽ ድረስ መልካምና ክፉ ዜና እየተደባለቀ መስማታችን የግድ ነው። በተለይም ደግሞ የጌታችን ዳግም ምጽዓት ቀን እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ዘመን ምድራችን በብዙ ትግልና ጣር ውስጥ መሆኗን ለማየት ሩቅ መሄድ አያስፈልገንም። በደቡብ ሱዳን ሲነጉድ የከረመው ጦርነት፣ በሶማሊያ ላለፉት 26 ዓመታት ሶማሊያን ያፈራረሳት የእርስ በርስ ጦርነት፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ብዙ ህዝብ የፈጀውና አገሪቱን ያወደመው የየመን ጦርነት፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአገራቸው ያፈናቀለው የሶሪያ ጦርነት፣ እኤአ ከ2003 የጀመረውና እስከ ዛሬ ድረስ አገሪቱን እያፈራረሰ ያለው የኢራቅ ጦርነት፣ ላለፉት 16 ዓመታት ሳያቆም በአፍጋኒስታን የሚካሄደው ጦርነት ወዘተ ጦርነትን በተመለከተ ልንጠቅሳቸው ከምንችላቸው ጥቂቶቹ ናቸው።  ይህ የሚያውከን ከሆነ ደግሞ ከዚህ የበለጠና ዓለም እስከ ዛሬ ድረስ ያላየችውን ጥፋት ሊያመጡ የሚችሉ መፋጠጦች በኤኮኖሚና በወታደራዊ ኃይላቸው ታላላቅ በሚባሉት አገሮች መካከልም በየጊዜው እየተካረሩ እየሄዱ ናቸው በማለት ብዙ ታዛቢዎች ያስጠነቅቃሉ። ታላቂቷ አገር አሜሪካ ከሩሲያ፣ ከቻይና፣ ከሰሜን ኮሪያና ከኢራን ጋር የገባችባቸው እሰጥ አገባዎች ወደ ሰላም የሚያመሩ አይመስሉም። ምድር ፍጹም ሰላም ያገኘችበት ጊዜ አልነበረም የሚሉ የታሪክ ባለሙያዎች እንኳን፣ ዛሬ ዓለማችን ያለችበት ውጥረት ግን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እጅግ ውስብስብና ከባድ መሆኑን አይክዱም።
ዘማሪው ወንድማችን ደረጃ ከበደ “ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ፣ የሚሆነው በምድር ዙሪያ፣ እየከፋ ሲሄድ ጊዜው መሸሸጊያ ኢየሱስ ነው” የሚለውን መዝሙር ከዘመረ ከአርባ ዓመት በላይ ሆኗል። የዚያ መዝሙር እውነተኛ መልእክት ግን ከዚያን ጊዜ ይልቅ ዛሬ እውን እየሆነ ነው ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም። ሆን ብለን አናይም፣ አንሰማም ካላልን፣ ወይም ደግሞ ብዙ ክፉ ዜናዎችን ከመስማታችን የተነሳ ልባችን ካልደነደነ በስተቀር በዓለም ሁሉ ዙሪያ ጎልቶ የሚታየውና የሚሰማው ዜና መልካም አይደለም። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘው ድረ ገጽ ላይ እንደምታነቡት ባለፉት ሁለት ሳምንታት እንኳን የተከሰቱትና ከባድ የህዝብ እልቂትና የንብረት ውድመት ያስከተሉትን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ብቻ እንኳን ስንመለከት ምድራችን ወደሚያስፈራ ሁኔታ ውስጥ እንደገባች እንረዳለን። የሚቀርበው የጥፋት ዜና ሁሉ ሆን ብሎ ከትንቢተ ኤርምያስ ምእራፍ 50 እና 51፣ ከትንቢተ ዳንኤል፣ ከትንቢተ ኢዩኤል ምእራፍ 2፣ ከማቴዎስ ምእራፍ 24፣ ማርቆስ 13፣ ሉቃስ 21 እና ከዮሐንስ ራዕይ መልእክቶች ላይ ተወስዶ የተጻፈ ይመስላል። በእርግጥ ዛሬ የምናያቸው ነገሮች ከጌታ ዳግም ምጽዓት በፊት በሚከሰተው የታላቁ የመከራ ዘመን ውስጥ ከሚፈጸሙት እጅግ አስፈሪ ነገሮች ጋር ሊወዳደር ባይችልም፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ግን በከፍተኛ አደጋና ችግር ውስጥ በየእለቱ እየገቡ ናቸው። ምናልባት እኛ ባለንባቸው ስፍራዎች ሰላም ከሆነ እግዚአብሔር ያን እድል የሰጠን ለሌሎቹ እንድንጸልይ መሆኑን አንዘንጋ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የምድር አካባቢዎች ከተከሰቱት ከፍተኛ ጥፋቶች መካከል የሚከተሉትን ብቻ መጥቀስ ይበቃል፡
*      California በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Oregon በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Washington በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png British Columbia በሚባለው የካናዳ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Alberta is on fire በሚባለው የካናዳ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Montana is on fire በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Nova Scotia በሚባለው የካናዳ ክፍለ ሃገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በግሪክ አገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በብራዚል ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በፖርቱጋል ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በአልጀሪያ ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በቱኒሲያ ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው

https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Greenland በሚባለው አገር ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png በሩሲያ Sakha Republic በሚባለው ግዛት ብዙ ስፍራዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f50/1/16/1f525.png Siberia በሚባለው አገር ብዙ ቦታዎች እየተቃጠሉ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f22/1/16/26c8.png Texas እና Florida በሚባሉት የአሜሪካ ክፍለ ሃገሮች ብዙ ቦታዎች በሞገድና በውሃ መጥለቅለቅ ወድመዋል፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰድደዋል፣ መብራት ጠፍቶ በጨለማ ውስጥ ናቸው
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f22/1/16/26c8.png 
በህንድ፣ ኔፓል፣ ፓኪስታንና ባንድላዴሽ እጅግ ከፍተኛና አደገኛ በሆነ ዝናብና ጎርፍ መጥለቅለቅ ብዙ ህዝብ አልቋል፣ ንብረት ወድሟል
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f22/1/16/26c8.png 
ሴራ ሊዮን እና ኒጀር በሚባሉት የአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ ጎርፍና የመሬት መደርመስ ብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ፈጅተዋል።
*                  ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ስፓኝ፣ ስዊዘርላንድ፣ ሃንጋሪ፣ ፖላንድ፣ ሮማኒያ፣ ቦስኒያ፣ ክሮኤሺያ እና ሰርቢያ የሚባሉት የአውሮፓ አገሮች እጅግ ከፍተኛና ከዚህ በፊት ከሆኑት በሚልቅ ሙቀት በመጠቃታቸው ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ከሙቀቱም ከፍተኛነት የተነሳ አንዳንዶች ሙቀቱን “ሉሲፈር” ወይም “ዲያብሎስ” ብለው ሰይመውታል።
https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/f5f/1/16/1f31e.png 
በተለምዶ አየሩ ቀዝቃዛ ነው በሚባልበት በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት ከሳንፍራንሲስኮ እስከ ሰሜን የክፍለ ሃገሩ ክፍሎች ድረስ የካሊፎርኒያ ግዛት ታይቶ በማይታወቅ ሙቀት እየተቃጠለ ነው።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
በአለም ትልቁ የሆነው የአሜሪካው Yellowstone volcano ይፈነዳል የሚል ትልቅ ፍርሃት አለ። ከሰኔ ወር ጀምሮ በዚህ የእሳተ ገሞራ አካባቢ 2,300 የሚሆኑ ትንንሽ የምድር መንቀጥቀጦች ተከስተዋል።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
አይዳሆ በሚባለው የአሜሪካ ክፍለ ሃገር 5.3 የሚለካ የምድር መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
ጃፓን በምድር ውስጥ ጥልቅ በሆነ 6.1 በሚለካ የምድር መንቀጥቀጥ ተመትታለች።
((https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/fc0/1/16/1f30e.png))
ከ 50 በላይ ሰዎችን የፈጀና 8.2 የሚለካ የምድር መንቀጥቀጥ በሜክሲኮ ተከስቷል።
ባለፉት 12 ዓመታት ያልሆነና ከፍተኛ የሆነ ከጸሃይ የተወረወረ ጨረር ምድርን በመምታቱ በብዙ የዓለም ስፍራዎች የሬድዮ ሞገድን አቋርጧል፣ አቃውሷል።ከፍተኛነቱ X10 C.M.E ነው የሚባለው ይህ ሞገድ በምድር መንቀጥቀጥና በአየር ንብረት ላይም ከፍተኛ ተጽእኖ ማድረጉ ተዘግቧል።
እነዚህ ዜናዎች መልካም ወይም የሚያበረታቱ አይደሉም። ነገር ግን ሕይወቱን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰጠ ክርትሲያን እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአጋጣሚ የሚሆኑና ተስፋ የሚያስቆርጡ አይደሉም። ጌታ ከመመለሱ በፊት በምድር ላይ የግድ ሊሆኑ አላቸው። እነዚህን ሁሉና ሌሎችንም በዚህ መልእክት ያልተጠቀሱ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ነው የታላቁ ወንጌላዊ የዶ/ር ቢሊ ግራሃም ልጅ የሆኑት ፍራንክሊን ግራሃም ዓለም ሁሉ ለክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ሊዘጋጅ ይገባዋል ያሉት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲገለጽና በጽድቅ ሲነግስ ምድር ሁሉ በሰላም ታድራለች። ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ያንን ቀን በናፍቆት ይጠብቃል። ተግተን በመጸለይና የምስራቹን ወንጌል ላልሰሙት በማድረስ መቅረዛችንን በዘይት ሞልተን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠብቀው። በሁለንተናችን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጽ ዝግጁ እንድንሆን ጌታ አምላክ ጸጋውን ሁሉ ያብዛልን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...