ከሶስት ቀናት በፊት ሃብታሞቹና ታላላቆቹ የምድር መንግስታት የምድርን አየር በሰው
ሰራሽ ቴክኖሎጂ በመቀየር ድርቅን፣ ጎርፍን፣ ማእበልንና ሌሎችም ምድርን የሚያጠፉ የአየር ንብረት ቀውሶችን ማምጣታቸው ወደ አደባባይ
ከወጣ ውሎ ማደሩን የሚያሳዩ መረጃዎችን አካፍዬ ነበር። ከዚህ መልእክት ጋር አያይዤ የላክሁት የ ዩ-ቲዩብ ማገናኛ፣ በ70ዎቹ አሜሪካ በቬትናም ባደረገችው ጦርነት የጦር ኃይሏ የአካባቢውን የአየር
ንብረት በመቀየስ ከፍተኛ ዝናብ፣ ጎርፍና ጥፋትን ታመጣ እንደነበር የሚያስረዱ ዘገባዎችን ይዟል። ተጨማሪ መረጃን የሚፈልግ ሰው
ደግሞ “Operation popeye” ብሎ በመፈለግ የአሜሪካ የጦር ኃይልና
የጦር መሳሪያ አምራቾች እንዲሁም ተኮናታሪዎች የአየር ንብረትን ምህንድስናን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀማቸው የአደባባይ ምስጢር መሆኑን
ማየት ይችላል። ይህን ማገናኛ በመጠቀም ቪዲዮውን ተመልከቱት፡ https://www.youtube.com/watch?v=Cpr5JVWjIW4
በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በመካከለኛው አሜሪካ በሚገኙ ደሴቶችና በደቡባዊና
ደቡባዊ ምስራቅ አሜሪካ ከፍተኛ ጥፋትን እያመጣች ያለችው ሃሪኬን ኢርማ ከ 600 ሺህ በላይ ሰዎች ከፍሎሪዳ ግዛት እንዲሰደዱ ባደረገችበት
በዚህ ወቅት፣ ይህች ታላቅ ሞገድም ሆነ ከእርስዋ በፊት ብዙ የቴክሳስን ግዛቶች ያጠፋው ሃሪኬን ሃርቪ፣ የአየር ንብረት ጦርነትን
በሚያካሂዱ ክፍሎች የተቀነባበሩ እንደሆኑ ብዙዎች እየዘገቡ ነው። ዋሽንግተን ፖስት የሚባለው ጋዜጣ እንኳን ሳይቀር፣ ይህች ሞገድ፣
ሃሪኬን ኢርማ፣ “በGPS ትመራ ይመስል በካሪቢያኑ ባህር ብዙ ደሴቶችን ካጠፋች በኋላ አሁን ደግሞ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትል
ቀጭን በሆነውን የፍሎሪዳ የመጥበሻ መያዣ መሰል መሬት ላይ ወደ አሜሪካ እየገባች መሆኗን ታዝቦ ዘግቦአል።
ሃሪኬን ኢርማ ከምታመጣው ጥፋት ሁሉ እጅግ እየተፈራ ያለው ደግሞ በዚያው በፍሎሪዳ
ግዛት የሚገኙ ሁለት የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎችን በመምታት የኑክሊየር ጥፋት ትፈጥር ይሆን የሚለው ሥጋት ነው። ሌሎች ደግሞ ከዚህም
አልፈው ይህች ሞገድ ከነዚህም አልፋ በአካባቢው ያሉ እስከ አስራ ሁለት የሚደርሱ የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎችንም ትጎዳ ይሆናል
ይላሉ። ሃሪኬን ኢርማ እያጣች ካለችው ጥፋት ሰው ገና ሸሽቶ ሳይጨርስ
ሌሎች ሁለት ሞገዶችም ከበስተኋላዋ እያደጉ እንደሆነ ተዘግቧል። ሁኔታውን ቀረብ ብለው የሚያጠኑ ባለሙያዎች ደግሞ የሁለቱ ትልልቅ
ሞገዶች ስም ራሱ የሚያስገርምና ምናልባት፣ በአጋጣሚ የተሰጠ ላይሆን ይችላል ይላሉ። ከሁለት ሳምንት በፊት ቴክሳስን ያጠፋው HARVEY
የሚለው ስም መሰረቱ ከፈረንሳይ ሲሆኑ ትርጉሙ “ተዋጊ” ወይም “ለጦርነት ዝግጁ፣ ብቁ የሆነ” ማለት ነው። አሁን ጥፋት እየሰራች
ያለችው ሞገድ IRMA ስም ደግሞ መሰረቱ ጀርመንኛ፣ ትርጉሙም “በሙሉ፣ ጠቅላላ፣ ዓለም አቀፍ” ማለት ነው። ከሃርቪም ይልቅ ከፍተኛ
ጥፋት ልታስከትል ስለምትችል ይህችን ሞገድ ብዙ አዋቂዎችና የመንግስት ባለስልጣናትም ሳይቀር “የኑክሊየር ሞገድ” በማለት ሰይመዋታል።
የሰው ያገኘውን እውቀትና ቴክኖሎጂ በመጠቀም በሌሎች ላይ ጥፋትን ለማምጣት፣ ደካሞችን
በማስፈራራትና በጉልበት ለመግዛት ሲሞክር ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ጌታ አምላክ በኖህ ዘመን የነበረውን ዘመንም በውሃ ያጠፋው
እንዲህ እንደ ዛሬው በምድር ላይ ዓመጽ ስለ በዛ ነበር። በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 17 እና 18 የተጠቀሰችው፣ በተለይም ደግሞ በምዕራፍ
18 ላይ የተገለጸችው፣ ምድርን ሁሉ እንደፈለጋት እየረጋገጠች ትገዛ የነበረችውና በኋላም ከጥልቁ የሚወጣው አውሬና ተከታዮቹ የሚያጠፉአት
ታላቂቲ ባቢሎን የዛሬዋ አሜሪካ ትሆን?!
በዚህ ሁሉ መካከል የሰው ነፍስ ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ግን በዙፋኑ አለ።
በእርሱ የሚታመኑ ሁሉ በማይናወጠው ዓለት በክርስቶስ ላይ የተመሰረቱ ስለሆኑ በምድር ላይ እየነፈሰ ያለው የዓመጽና የጥፋት ማእበል
አያጠፋቸውም። ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ጌታ አምላክ ግን በጎቹን ለመጠበቅ አይተኛም፣ አያንቀላፋም፣ አይደክምም አይታክትም። ሁሉንም
በጊዜው በክርስቶስ ውብ አድርጎ እንደገና ይሰራዋል። የጌታ ሰላምና ጸጋ ይብዛላችሁ። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ