የማይገለጽ የተሰወረ የለምና፣ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። ማቴዎስ 10፡26 ሉቃስ 8፡17
የሚከተለውን ማገናኛ (LINK) በመጫን የሚገርም የአርኪዎሎጂ መረጃን የሚያቀርበውን ቪዲዮ ተመልከቱ።
የዓለም ታሪክ፣ አርኪዎሎጂ፣ ፍልስፍና ወዘተ እየተባለ በዓለም ሁሉ ስንማረው የነበረው
ነበር ብዙ ውሸቶች የሞሉበትና እውነተኛውን የዓለም ታሪክ የደበቀ መሆኑ እየተጋለጠ ከመጣ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል። በትንቢተ ዳንኤል
ምእራፍ 12 በተለይም በቁጥር 4 ላይ እንደተጻፈው የዘመኑ መጨረሻና የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ስለተቃረበ፣ ተሰውረው
የነበሩ መረጃዎችና ታፍነው የነበሩ እውቀቶች ሁሉ ወደ አደባባይ እየወጡ ናቸው። ከዚህ መልእክት ጋር የተያያዘውን ቪዲዮ ስትመለከቱ
የእግዚአብሔር ቃል ምን ያህል የከበረ እውነትንና ታሪኮችን ይዞ እንዳቆየልን ማስተዋል ትችላላችሁ። ቪዲዮው ላይ የሚቀርበው ሪፖርት
የአርኪዎሎጂ እና የጥንት ታሪክ ጥናት ውጤት እንጂ የሃይማኖት ስብከት ስላልሆነ አቅራቢዎ የሚናገሩአቸውን ነገሮች ለመረዳት በመጀመሪያ
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበውን እውነተኛውን የጥንት ዘመን ታሪክ መረዳት ያስፈልጋል።
ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 6 በምድር ላይ ኔፊሊም የሚባሉ
እንደነበሩ ይነግረናል። ኔፊሊም የሚለው ቃሉ “የወደቁ” የሚል ሲሆን፣ ለነዚያ ፍጥረታት ኔፊሊም የሚለው ስም የተሰጠበት ምክንያትም
በዚያው በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1ና 2 ላይ ተገልጾአል። የእግዚአብሔር ልጆች (ብነይ ኤሎሂም) ከሚባሉት ከወደቁት መላእክት
አንዳንዱ በልኡል እግዚአብሔር የፍጥረት ስርዓት ላይ በማመጽ ወደ ምድር በመውረድ ከሰው ሴቶች ልጆች ጋር ዘራቸውን በማደባለቃቸው
የተወለዱት ከፊል የወደቁ መላእክትና ከፊል የሰው ዘር ያላቸው ፍጥረታት ናቸው ኔፊሊም የተባሉት። እነዚህ ፍጥረታት እንደ አባቶቻቸው
ሁሉ እኩያን ስለነበሩ ምድርን በዓመጽ ሞልተዋት ስለነበረ ነው ጌታ አምላክ እጅግ አዝኖና ተቆጥቶ በኖህ ዘመን የነበረውን ዓለም
በጥፋት ውኃ ያጠፋው። ለሰው ልጆች የጦር መሳሪያ መስራትን፣ ጽንስን ማስወረድን፣ ያልተፈቀደ ግብረ ስጋ መፈጸምን (እንደ ሰዶማዊነት
ያሉ)፣ ጥንቆላን፣ ኮከብ ቆጠራንና ሟርትን ያስተማሩ እነዚያ የኔፊሊም አባቶችና ኔፊሊም እንደነበሩ ሌሎች የታሪክና አዋልድ መጻህፍት
ብዙ ማስረጃ ይሰጣሉ። ከነዚህ ከረዓይት ዓመጽና የሰው ልጆችም እነሱን ተከትለው ዘራቸውን፣ የምድር እንስሳትንና እጽዋትንም ዘር
ሁሉ በመበከላቸው ነበር ጌታ አምላክ ተቆጥቶ ዓለምን በውኃ ያጠፋው።
ከጥፋት ውኃ በኋላም ደግሞ ኔፊሊም እንደገና በምድር
ላይ እንደነበሩ በዚያው በዘፍጥረት 6፡4 ላይ እናነባለን። “በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፣ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር
ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው”። ብዙዎቻችን የምናነበው የ1962 ዓም የአማርኛው ትርጉምና ብዙዎቹ የእንግሊዝኛ
ትርጉሞች እነዚያ ኔፊሊም “በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ” ቢልም፣ ብሉይ ኪዳን በመጀመሪያ የተጻፈበት እብራይስጡ ግን
ኔፊሊም ኃያላን የነበሩ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን፣ ግዙፍ ወይም ረዓይት (giants) እንደነበሩ ይናገራል። በ2000 ዓም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የተተረጎመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ትርጉምም
እነዚያን ኔፊሊም “ረዓይት” ብሎ የእብራይስጡን ሃሳብ በተሻለ መንገድ ተርጉሞታል። በዚሁ ትርጉም ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አዋልድ
መጻህፍት፣ በተለይም ደግሞ መጽሐፈ ሄኖክና መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ረዓይትና የተያያዙ ታሪኮች ተጨማሪ መረጃ ይሰጣሉ።
በባቢሎን እንዲሁም በሰዶምና ገሞራ የታየው ዓመጽና
የተከተለው የእግዚአብሔር ቁጣ ከጥፋት ውኃ በኋላ እንደገና በምድር ላይ በተባዙት በኔፊሊም የተመራ ነበር። ኔፊሊም በአካል እጅግ
ግዙፍ ፍጥረታት ነበሩ። ቁመታቸው እስከ 30 ጫማና ከዚያም በላይ
ይደርስ እንደነበር የሚያመለክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የአዋልድ መጻህፍት፣ የታሪክና የአርኪዎሎጂ መረጃዎች በምድር ሁሉ አሉ። በሙሴ
መሪነት እስራኤል ያሸነፋቸው የሃሴቦን ንጉስ ሴዎንና የባሳን ንጉስ ዓግ የኔፊሊም ዝርያ ያላቸውና እንደ አምላክ ይመለኩ የነበሩ
ናቸው። የእስራኤል ህዝብ ከነዓንን ከመውረሱ በፊት እንዲያጠፋቸው ታዝዞ የነበሩት የነዚሁ የኔፊሊም ዝርያ ያላቸው “ህዝቦች” ነበሩ።
በእስራኤል ዘመን የነበሩት እንደ አናቃውያን፣ ዘምዙማውያን፣ ኤዊያውያንና ሌሎችም የረዓይት ዝርያዎች ከኔፊሊም የተወለዱ እንደነበሩ
ኦሪት ዘሆልቁ ምዕራፍ 13 በተለይም ደግሞ ቁጥር 33 ያስረዳል። ዳዊት የገደለው ጎልያድና ዳዊት ከነገሰም በኋላ የሱ ወታደሮች
የገደሉአቸው ሌሎች የጎልያድ ወንድሞችና ዝርያዎችም ከነዚያው ከኔፊሊም ዝርያዎች የቀሩ ነበሩ። በእስራኤል ዘመን የኔፊሊም ዝርያዎች
ራፋይም ተብለው ይጠሩም ነበር።
ኔፊሊምና ዝርያዎቻቸው ከፊል የወደቀ መላእክትና ከፊል
ሰው ስለነበሩ ከፍተኛ እውቀት ቢኖራቸውም ሃሳባቸውና ስራቸው ሁሉ ግን እኩይ ነበር። ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ስለነበራቸው። የሰውንና የእንስሳትን
እንዲሁም የራሳቸውን ዘር በማደባለቅ የጌታ አምላክን ህግ በመጣስ ብዙ የሚያስፈሩና አደገኛ ፍጥረታትን እንዲወለዱ አድርገዋል። በግሪክ፣
በግብጽ፣በባቢሎን፣ በሮምና ሌሎችም የጥንት ሃይማኖቶች ይመለኩ የነበሩት ራሳቸው ኔፊሊምና እነሱ አዳቅለው የፈጠሩአቸው እኩያን ፍጥረታት
ነበሩ። ዛሬ በምድር ላይ አለ ከምንለው ቴክኖሎጂ የሚተካከልና በብዙ መንገድም የሚበልጥም ቴክኖሎጂ ስለነበራቸው በምድር ሁሉ እንደ
ፒራሚዶች ያሉ ግዙፍ ስራዎችን ሰርተዋል። በተያያዘው ቪዲዮ ላይ እንደምታዩትም የተራቀቀ የህዋ፣ የከዋክብትና የሌሎች ሳይንሳዊ እውቀት
ፈጣሪዎች እነሱ እንደነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ። የነዚያ የረዓይት
(ኔፊሊም) ዓጽሞች እንዳይገኙ እየሰበሰቡ ሲያቃጥሉና ሲደብቁ የኖሩት እንደ ቫቲካንና Smithsonian Institution ያሉ ድርጅቶች እውነቱን ለማፈን ቢጥሩም እነሱ ሊያጠፉአቸው
ወይም ሊደብቁአቸው ያልቻሉ ምስጢሮች ዛሬ ወደ አደባባይ እየወጡ ነው።
ዛሬ እንደ አሸን የፈላው ቴክኖሎጂ፣ Genetic Engineering፣ የጾታ ግራ መጋባት፣ የሰዶማዊነትና ሌሎችም በመጽሐፍ
ቅዱስ የተከለከሉ የረከሱ ፍትወተ ስጋ አይነቶች መስፋፋት፣ መንግስታት ከህሊና እና ከመጽሃፍ ቅዱስ እውነት ጋር የሚጻረሩ ህጎችን
በሰፊው ማውጣታቸው፣ እየተጋነነ የመጣው የ3ኛው የዓለም ጦርነት ወሬ፣ የእውነተኛ ክርስቲያኖች ስደት መብዛት ወዘተ ያ የኖህ ዘመን
የነበረው ሁኔታ እንደገና እየተከሰተ እንዳለ ያሳያል። ለዚህም ምክንያቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መቃረቡ ነው።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት፣ ከፖለቲካው ጫጫታ በተጨማሪ በአሜሪካ ኮንግረስ፣ በNASA እና በመገናኛ ብዙኃንና በኢንተርኔት ብዙ ሲነገር
የምንሰማው ስለ ALIENS እና Extra Terrestrials ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት
እነሲያ በኖህ ዘመን፣ በባቢሎንና በከነዓን የነበሩት የኔፊሊምና የራፋይም ዘሮች እንደገና ወደምድር ግልብጥ ብለው የሚወጡበት ጊዜ
ስለተቃረበ ነው። ነገር ግን፣ በመገናኛ ብዙኃን ወይም አዋቂ በሚባሉ ሰዎች እንደሚነገረን እነዚህ ፍጥረታት በሌላ ጋላክሲዎች፣ ዓለማትና
ፕላኔቶችና ዓለማት የሚኖሩ “የሰለጠኑ” ALIENS ወይም EXTRA
Terrestrial ሳይሆኑ ከሌሎች ከመንፈስ ወደ አካል ከአካል ወደ መንፈስ የሚቀያየሩ የኔፊሊም ዘሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው
ዘመን ይህ እንደሚሆን በግልጽ ነግሮናል። በክብር ዳግም ከመምጣቱ በፊት በምድር ላይ ስለሚሆነው ታላቁ የመከራ ጊዜ ሲናገር ጌታ
ኢየሱስ እንዲህ ብሎአል፡ “ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን (በዓለም ላይ ሊገለጽ ያለውን ነገር) ከመጠበቅ የተነሳ ይደክማሉ፣”
ሉቃስ 21፡26 የእነዚያ የኔፊሊም ዘሮች በምድር ላይ ዛሬ በስውር ከብዙ መንግስታት ጋር እየሰሩ እንዳሉ የሚያስረዱ መረጃዎች አሉ።
የመልእክቴ ዋነኛ ሃሳብ አንድ ነው። በጌታ በኢየሱስ
ክርስቶስ ለሚያምንና ህይወቱን ለእግዚአብሔር ላስገዛ ሰው፣ ሁሉ ነገር በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር ነውና መፍራት አያስፈልግም። ነገር
ግን ከጌታ ከአምላካችን ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ መታረቃችንን እናረጋግጥ። ህይወታችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያሳይ መሆኑን
እንመርምር። በጌታ ያላመንን ከሆንን ደግሞ የንስሃ ቀን ዛሬ ነው። ነገ አይደለም።
ከላይ ሰለ ተነሳው ርእስና ሌሎችም የመጨረሻው ዘመን
ምልክቶች ሰፋ ያሉ ትምህርቶችንና መረጃዎችን ከመለከት ድምጽ መጽሔትና ከመለከት ድምጽ ብሎግ ማግኘት ይቻላል። መጽሔቱንና ሌሎች
መልእክቶችን ከሚከተለው ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል;;
http://voice-of-trumpet-amharic@blogspot.ca
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ የሚመጣበት ዘመን
እጅግ ቅርብ ነው። ማራናታ !! አሜን ጌታችን ሆይ ቶ ሎ ና !
ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ