ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኃያላኑና ባለጸጎቹ አገሮች ወይም ድርጅቶች የምድርን አየር ንብረት እንዳሻቸው ለመለወጥ መቻላቸው ይፋ እየሆነ ነው። http://www.newsweek.com/artificially-cool-earth-volcano-eruptions-extremely-dangerous-711203
ከብዙ ሳምንታት በፊት በላክሁት መልእክት ሃብታሞቹ አገሮች ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም
በሚፈልጉት ቦታና ጊዜ ደመና እንዲፈጠር፣ ዝናብ እንዲዘንብ ወይም እንዳይዘንብ፣ ነጎድጓድና መብረቅ እንዲሁም በምእራቡ ዓለም ሃሪኬን
(Hurricane) በእስያ ደግሞ ታይፉን (Typhoon) የሚባሉ ከፍተኛ ጥፋት የሚያደርሱ የአየር ማእበሎችን መፍጠር
እንደሚችሉ ተጠቁሞ ነበር። ለብዙ አሰርት ዓመታት የዚህ ቴክኖሎጂ መኖርና በቬትናምና ሌሎችም ቦታዎች ላይ አሜሪካ ይህን ቴክኖሎጂ
ለጦርነት ማዋሏ ሲካድ ከቆየ በኋላ ጉዳዩ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በአሜሪካ ምክር ቤትም ሳይቀር ውይይት የሚካሄድበት ሆኗል። ይህን
ማገናኛ (link) በመጠቀም የአሜሪካው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ያደረገውን ስብሰባ የተመለከተ ዜናን ማግኘት ይቻላል፡http://www.homelandsecuritynewswire.com/us-congress-holds-hearings-geoengineering
ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ዜና እንደምታነቡት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የሚለቅቀውን አቧራ
ዓይነት ሰው ሰራሽ ግርዶሽ በምድር ከባቢ አየር ላይ በመፍጠር የምድርን ከባቢ አየር የሚያሞቀውን የጸሃይ ብርሃን በመቀነስ በሰሜን
ዋልታ አካባቢ በተፈለገው ጊዜ ቀዝቃዛ አየር በመፍጠር አሜሪካን በየጊዜው የሚጎዷትን ታላላቅ የአየር ማእበሎች (hurricanes) ለመቀነስ እንደሚቻል ቴክኖሎጂውን በቅርብ የሚያውቁ ባለሙያዎች ስለ ጉዳዩ ያላቸውን ፍራቻ በአደባባይ መዘገብ ጀምረዋል።
በእንግሊዝ የሚገኘው የኤግዘተር ዩኒቨርሲቲ ዋነኛ ተመራማሪ የሆኑት አንቶኒ ጆንስ የተባሉት ባለሙያ Nature Communications በሚባለው መጽሔት ላይ እንዳሰፈሩት ይህ ቴክኖሎጂ በሰሜናዊው የምድር ግማሽ ስራ ላይ ሲውል በአሜሪካና በካሪቢያን
አገሮች አካባቢ የሚከሰቱትንና ብዙ ጥፋት የሚያደርሱትን የአየር ማእበሎች ሲቀንስ፣ በሌላ ወገን ደግሞ በአፍሪካ የሳሄል አካባቢ
ከፍተኛ ድርቅን ያስከትላል። ቴክኖሎጂው በደቡባዊው ክፍለ ዓለም በስራ ላይ ቢውል ደግሞ አሜሪካንና የካሪቢያን አገሮችን በየጊዜው
የሚጎዱትን የአየር ማእበሎች እንደሚያባብስም ተደርሶበታል ይላል ይኸው ከላይ የተጠቀሰው ሪፖርት። በመቀጠልም ሪፖርቱ ገንዘቡና ቴክኖሎጂው
ያላቸው አገሮች ወይም ድርጅቶች ይህን ቴክኖሎጂ በፈለጉት ጊዜና ቦታ
ስራ ላይ እንዳያውሉት የሚከለክላቸው ነገር ስለሌለ በአፍሪካና ሌሎችም አካባቢዎች ትልቅ ጥፋትን ሊያስከትል እንደሚችል ፍርሃቱን
ገልጿል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ