ከትልልቆቹ የመድሃኒት አምራቾች ድርጅቶች አንዱ የሆነው የፋይዘር የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት Gardasil የሚባለው ሴቶች ልጆችን ከማህጸን ካንሰር ይጠብቃል የሚባለው ክትባት አደገኛና ገዳይ ነው ሲሉ አጋለጡ።

ከትልልቆቹ የመድሃኒት አምራቾች ድርጅቶች አንዱ የሆነው የፋይዘር የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት Gardasil የሚባለው ሴቶች ልጆችን ከማህጸን ካንሰር ይጠብቃል የሚባለው ክትባት አደገኛና ገዳይ ነው ሲሉ አጋለጡ።
ስለ መጨረሻው ዘመን የሚናገሩ እንደ ማቴዎስ 24 ሉቃስ 21 እና ማርቆስ 13 ያሉ ትንቢት አዘል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ባሉት ጊዜያት በምድር ላይ አለመረጋጋትና ጦርነት፣ ረሃብና ብዙ ህዝብን የሚፈጁ በሽታዎች (ቸነፈር) እንደሚበዛ ይናገራሉ። ከእነዚህ መካከል የዛሬው አጭር መልእክት የሚያተኩረውቸነፈርበሚለው ላይ ነው። ባለፉት ብዙ አሰርት ዓመታት ክትባት ብዙ በሽታዎችን በመቀነስ የብዙ ሰዎችን ሕይወት ማዳኑ በሰፊው የሚዘገብ ነው። ይህ በአብዛኛው እውነት ቢሆንም ግን፣ ከክትባት ጋር ተያይዘው ስለሚመጡና ብዙ ሰዎችን ለህይወት ዘመናቸው ህመምተኛና አካለ ጎደሎ አድርገው ስለሚያስቀሩ ወይም የብዙዎችን ህይወት ስለሚያጠፉ ንጥረ ነገሮች ግን በሰፊው አለመዘገቡ የሚያስደንቅና የሚያሳዝን ነገር እንደሆነ ብዙ የህክምና እና የመድኃኒት ቅመማ ባለሙያዎች እንዲሁም ለህዝብ ጤና ተከራካሪ ድርጅቶች ይናገራሉ። ለምሳሌ ያህል በሰሜን አሜሪካና በምእራቡ ዓለም በሰፊው በስራ ላይ በዋሉና ተነባብረው በአንድ ጊዜ በሚሰጡ እንደ MMR እና እንፍሉዌንዛ ባሉ ክትባቶች ውስጥ በሰፊው በስራ ላይ ሲውል የቆየው ታይመሮሳል (Thimerosal) የሚባለው ከሜርኩሪ የሚሰራ ንጥረ ነገር ኦቲዝም የሚባለው የእጅግ ብዙ ወጣቶችን ሕይወት የቀጨውና ያበላሸው ህመም ምንጭ መሆኑ እርግጠኛ ነው የሚሉ ብዙ የህክምና እና የህዝብ ጤና ተከራካሪ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ቁጥር እየበዛ መጥቷል። ይህ Thimerosal እና የኦቲዝም መስፋፋት እጅግ ያሳዘናቸው 1960ዎቹ የተገደሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ዘመድ የሆኑት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ጁኒየር ጉዳዩ ያሳዘናቸውንና ያበሳጫቸውን እጅግ ብዙ ባለሙያዎች በማስተባበር እነዚህ ሰውን የሚጎዱ በክትባት ውስጥ የሚጨመሩ ንጥረ ነገሮች ከገበያ ላይ እንዲወገዱ ዘመቻ ሲያደርጉ ቆይተዋል። እኒሁ ታዋቂ ሰው ከሌሎች ዶክተሮችና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በጻፉት “Thimerosal, Let the Science Speak” በሚለው መጽሐፍ ላይ በThimerosal እና በኦቲዝም መካከል ያለው ቁርኝት ሳይንሳዊ መሆኑ የሚያሳዩ ብዙ ጥናቶችን ለአብነት ያቀርባሉ።

እነዚህን ክትባቶች የሚሰሩት በቢሊዮን ዶላር በመሸጥ የሚበለጽጉት የመድሃኒት ቀማሚ ድርጅቶች በመንግስትም ሆነ በግል የጤና ድርጅቶች ገንዘባቸውን በመጠቀም፣ በህክምና ባለሙያዎች፣ በትምህርትና በምርምር ተቋማት እንዲሁም በመገናኛ ብዙኃን ላይ በሚያደርጉት ተጽእኖ ምክንያት ክትባቶቻቸው በህዝብ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት እንደሚታፈን ከነዚያው ከክትባት ሰሪ ድርጅቶቹ ውስጥ ምስጢሩን የሚያጋልጡ ባለሙያዎች ጥቂት አይደሉም። በዚህ ምክንያት አንዳንድ ክትባቶች፣ በተለይም ደግሞ በክትባቶቹ ውስጥ ያሉ ጎጂ ንጥረ ነገሮች በብዙ ህጻናት፣ ጎልማሶችና አዋቂዎች ህይወት ላይ የሚያደርሱት ሞትና ጉዳት እንደ ውሸትና በሳይንስ ያልተረጋገጠ አወዛጋቢ ነገር ሆኖ በመገናኛ ብዙኃን ይቀርባል። በአሜሪካን አገር ብቻ እንደ አሸን የፈላው የኦቲዝም በሽታ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ልጆችን ህይወት የጎዳ በመሆኑና፣ ችግሩም እየተባባሰ በመሄዱ ባለፉት ብዙ ዓመታት የአሜሪካው ፌደራል መንግስት የተወካዮች ምክር ቤት እንኳን ሳይቀር በጉዳዩ ላይ ብዙ ውይይቶችን ማድረጉ የታወቀ ነው። ኦቲዝም የሚባለውና በአብዛኛው ወንዶች ልጆችን በከፍተኛ ቁጥር የሚያጠቃው ህመም ዋነኛ ምንጩ ከላይ የተጠቀሰው ከሚርኩሪ የሚቀመመውና በአንድ ላይ የሚሰጡ የተለያዩ በሽታ ክትባቶች ጊዜያቸው እንዳያልፍ የሚጨመረው ታይመሮሳል የሚባለው ንጥረ ነገር መሆኑ በብዙ ባለሙያዎችና ጉዳቱ በደረሰባቸው ልጆች ቤተሰቦችም የሚታመን ሆኗል። ምሳሌን ለመጥቀስ ያህል በካናዳ ስራ ላይ ከዋለና በብዙ ልጆች ላይ የሜኒንጃይተስ በሽታ ካስከተለ በኋላ በህዝብ ጩኽት ከገበያ ላይ የተወገደው MMR ክትባት ስሙ ወደ  Pluserix ተቀይሮ በ1980ዎቹና 90ዎቹ በእንግሊዝ አገር ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በዚያም ብዙ ልጆችን ስለጎዳ ታግዷል። ነገር ግን ክትባቱ በፍጹም ከገበያ ላይ በመነሳት ፈንታ እንደገና ስሙ ተቀይሮ እንደ ብራዚል ባሉ አዳጊ አገሮች በስራ ላይ መዋሉ በሰፊው ተዘግቧል። ለአብነት ያህል በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ አንዳንድ የባለሙያና የዜና ድርጅቶች ድረ ገጾች በዚህ ተመልክተዋል፡https://vaccinechoicecanada.com

http://www.nvic.org


ክትባቶች ሁሉ መጥፎ ናቸው ለማለት ወይም ክትባትን ሁሉ መውሰድ በሽታን ያስከትላል ለማለት አይቻልም። ነገር ግን በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየበዙ ከሄዱት እንደ ኦቲዝም፣ የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት መጨመር፣ የተለያዩ አለርጂዎችና የአእምሮ በሽታዎች እንዲሁም በሰውነት ውስጥ እብጠትን እና የማያቋርጥ ህመምን የሚያመጣው አውቶ ኢሚዩን የሚባለው ህመም ወረርሽኝ ብዙ ምንጮች መካከል አንዳንድ አደገኛ ክትባቶችም እንዳሉበት ለመጠቆምና የሚችል ሰው ሁሉ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሻ ለማሳሰብ ነው። በዚህ ላይ ሊጨመር የሚገባቸው ሁለት ትልልቅ ቁም ነገሮች አሉ። 1) ብዙ ክትባቶች እንደ ሌሎች መድኃኒቶች በብዙ ሙከራ ውስጥ አያልፉም። ስለዚህም ክትባቶቹን አምራች የሆኑት ታላላቅ የምእራቡ ዓለም (በተለይም የአሜኪካ) መድሃኒት አምራች ድርጅቶች በክትባት በሞቱና በተጎዱ ሰዎች ቤተሰቦች ሊደርስባቸው በሚችል ክስና የገንዘብ ቅጣት እንዳይከስሩ የአሜሪካው ምክር ቤት ብዙ ህጎችን አውጥቷል። የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ወደርሱ አቤት በተባሉ ክሶች ላይ ተመርኩዞ የእነዚሁኑ ክትባት አምራች ድርጅቶች ጥቅም ብቻ የሚጠብዙ ውሳኔዎችን አስተላልፎአል። ታሪክ የሚጻፈው በአሸናፊዎች፣ ክስም የሚሰምረው ገንዘብና ጉልበት ላላቸው ነው የሚለው አባባል ብዙ እውነትነት እንዳለው በክትባት ምክንያት የተጎዱ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኦቲዝም፣ የተለያዩ የአካልና የአእምሮ ህመሞች፣ የአለርጂና የእውቶ ኢሚዩን ህመም ሰለባዎች እየተረዱ ነው።  ከሁሉም በላይ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ዶክተሮችን ጨምሮ ብዙ የህክምና ባለሙያዎችም ቢሆን አንዳንድ ክትባቶች በእርግጥ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን አለማወቃቸው ነው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከክትባቶቹ ጋር ተያይዘው የሚላኩት ወረቀቶች ራሳቸው በግልጽ ክትባቱ ጉዳትና ሞትም ጭምር ሊያደርስ እንደሚችል ቢገልጽም አንዳንድ ሃኪሞች በማወቅም ባለማወቅም ይህን ማስጠንቀቂያ በማጣጣል “ይሄ እንደ አጋጣሚ ካልሆነ በቀር አይሆንም” ስለሚሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ልጆቻቸውን፣ የልጆቻቸውን ጤናና ደህን  አጥተው በመከራ ይኖራሉ።

እውቀትና ቴክኖሎጂ እያደገ በሄደበት በዚህ ዘመን ለብዙ ህመሞችና በሽታዎች ክትባትና መድሃኒት መገኘቱ የሚያስደስተውን ያህል፣ በታላላቆች የመድሃኒት አምራች ድርጅቶችና በተባባሪዎቻቸው ስግብግብነት ምክንያት አንዳንድ ክትባቶች እጅግ ብዙ ጉዳቶችን ማድረሳቸው፣ ይህም ደግሞ ከህዝብ መሰወሩ ቢያሳዝነንም ሊያስደንቀን አይገባም። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነውና። ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ዘመን እንደሚመጣ እወቅ ብሎ ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ያስጠነቀቀን። 2ኛ ጢሞ ምዕ 3። እንደምንገምተው ረሃብና ቸነፈር ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ አይደለም። እልቂትና ጦርነት ወይም ሁከት በአጋጣሚ አይከሰትም። ስለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ለመሪዎች፣ ለመኳንንትና ለባለስልጣናት ሁሉ በያለንበት እንድንጸልይ የሚያስተምረን። የክፋት፣ የጭካኔና የእልቂት ደራሲ የሆነው ዲያብሎስ የሚፈረድበት ጊዜ እንደደረሰ ስለሚያውቅ በስግብግብነትና በራስ ወዳድነት የተሞሉ የግል ድርጅቶችም ሆነ የመንግስት ባለ ስልጣኖችን በመጠቀም የሰውን ዘር የሚያጠፋበትን ስራ እንዳይሰራ መጸለይ በክርስቶስ ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ሁሉ ግዴታ ነው። እንንቃ፣ ለአገራችን፣ ለህዝባችን፣ ለምንኖርባቸው አገሮች መንግስታትና ባለ ስልጣናት ሁሉ ከልብ እንጸልይ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ ይመጣል። ያለንበት ዘመን አስጊና አስፈሪ ቢሆንም “እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጌዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” ማቴ 28፡20 ያለው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም ከሚያምኑት፣ ተስፋ ከሚያደርጉትና ከሚታዘዙት ሁሉ ጋር ነው። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...