የካናዳ ሴኔት (ፓርላማ) ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች በማመኑ፣ በተፈጥሮ ህሊናውና በባህሉ የማይቀበለውን ፍትወተ ስጋ መቃወምን ወንጀል የሚያደርግ ህግ አጸደቀ።

በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የምናምን ክርስቲያኖች በካናዳና በዓለም ዙሪያ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር መመልከት ከቻልን በእርግጥም በኖህ ዘመን የነበረውን የጥፋት ውኃ የሚመስለው የመጨረሻው ዘመን ዓመጽ አንገታችን አጠገብ እየደረሰ እንዳለ እንረዳለን።

ባለፈው ሳምንት በኦንታሪዮ የልጆችን መብት መጠበቅ በሚል ሰበብ የብዙ ክርስቲያኖችንና ሌሎች ካናዳውያን ወላጆችን መብት የሚጋፋና መንግስት ተቀበሉ የሚለውን ፍልስፍና፣ ከፈጣሪ ህግ ጋር የሚቃረኑና አብዛኛው ዓለም (ኢትዮጵያ ሃገራችንም ጭምር) የማይቀበላቸውን ፍትወተ ስጋና ሰው ፈጠር “ጾታዎች” ከማይቀበሉ ወላጆች ላይ ልጆቻቸውን ለመቀማት ስለወጡ ህጎች የወጣ ዜናን አካፍዬ ነበር። የዛሬው ደግሞ ከዚያም የባሰና እጅግ የሚያስፈራ ነው። የካናዳ ሴኔት በዚህ ሳምንት በከፍተኛ ድምጽ ያሳለፈው ህግ ማንኛውም ካናዳዊ ሰው በግል ህሊናው፣ በሃይማኖቱና በባህሉ የማይቀበላቸውን ሃሳቦች በግድ ካልተቀበለ በስተቀር “የጥላቻ” ንግግር ተናግረሃል ተብሎ ወንጀለኛ እንደሚሆን የሚደነግግ ህግን አውጥቶአል። የካናዳ መንግስትና ይህን የሚደግፉት የዜና አውታሮች በሙሉ ዜና ብለው የሚነግሩን ግን ህጉ የወጣው አናሳ የሆኑ ሰዎችን መብት ለማስከበር እንደሆነ ነው። ይህ ግን በመርዙ ላይ ማርን ከመቀባት የተለየ አይደለም። ይህን ህግ ሴኔቱ አሳልፎታል። በንግስቲቱ ተወካይ ጸድቆ ህግ ሆኖ ከወጣ (ይህም የማይቀር ይመስላል) ማንኛውም ሰው በተፈጥሮአዊ ህሊናው፣ በእምነቱና፣ በባህሉ የሚያምንበትንና አብዛኛው የሰው ዘር የሚያምንበትን ነገር ጥሎ እንደ አሻንጉሊት መንግስት ያዘዘውን ነገር ብቻ ነው መናገር የሚችለው። ይህ ምን ማለት ነው? ባለፉት አስርና ሃያ ዓመታት የፈለግነውን ዓይነት ፍትወተ ስጋ መፈጸም መብታችን ስለሆነ ይከበርልን የሚሉ ወገኖችን ሰብዓዊ መብት እናስከብራለን በሚል ሽፋን ብዙ ህጎች ሲወጡ ከርመዋል። ብዙ ክርስቲያኖችም በየዋህነትና መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ሰው በሰውነቱና በህይወቱ ላይ የፈለገውን (መንግስተ ሰማያትን ወይም ሲኦልንም ጭምር) መምረጥ ይችላል ብለው በማመን እነዚህ ሁሉ ህጎች ሲወጡ ብዙም ተቃውሞ አላሳዩም። ብዙዎቻችን ኢትዮጵያውያንም ሃይማኖት በሰው ህይወትና በባህላችን ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጥበትና ከሚከበርበት አገር ስለመጣን እንዲህ ያለ ህግ እንዴት በካናዳ ሊወጣ ይችላል ብለን እናስባለን። የሚካሄደውንም ነገር መረዳት የምንፈልገው ከፖለቲካ አንጻር ይህ የሊበራሎች ነው፣ ይህ ደግሞ የኮንሰርቫቲቭ ነው እያልን ነው። ጉዳዩ ግን በየጊዜው ከሚቀያየረው ፖለቲካ በላይ ነው። መንፈሳዊ ነው። ስለ ሰው ዘር የወደፊት መቀጠል ነው። ጉዳዩ በወንድና ወንድ ወይም ሴትና ሴት መካከል ስለሚፈጸም ፍትወተ ስጋ ብቻም አይደለም።
የእኔን መብት እስካልነኩ ድረስ እንደፈለጋቸው የሚለው አስተሳሰብ ብዙ ሰዎች የሚያምኑበት ነው ስንል ኖረናል። እኔም ብዙ ጊዜ እንዲህ ብያለው። ምክንያቱም ይህ አስተሳሰብ፣ ሰዎች በግል ህይወታቸው የሚፈልጉትን ማድረግ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ያማከለ ነው ። በየደረጃው ያሉ የካናዳና አንዳንድ የሌሎች መንግስታት ባለስልጣኖች የሚከተሉት መመሪያ ግን መጽሐፍ ቅዱስን ወይም ደግሞ አብዛኛው ዓለም የሚከተለውን የተፈጥሮን ህግ ሳይሆን እነሱ ባሉበት በመንግስት ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የያዙ ሰዎች የሚያራምዷቸውን የፖለቲካ ዓላማዎች ነው። እነዚያ ዓላማዎች ደግሞ ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉትን እውነቶች የሚጻረሩ ናቸው። ዲሞክራሲ ተብሎ ተመርጠናል ተብለው ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ የሚሰሩት ስራ ግን ህዝቡ የሚሻውን ሳይሆን ህዝቡ ራሱ በነሱ ፍልስፍናና አምላክ የለሽ የኑሮ ዘይቤ እንዲያምን ነው።  ስለዚህ የፈለግነውን ፍትወተ ስጋ ዓይነት (ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት፣ ወንድ ከሴትም ከወንድም ወዘተ) መፈጸም መብታችን ነው የሚሉ ሰዎች የመንግስትን፣ የመገናኛ ብዙኃንን፣ ዋና ዋና የግል ድርጅቶችን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አመራር ስለ ያዙ ማራመድ የሚፈልጉትም ያንን የነርሱን ምርጫ ብቻ ነው። የእነርሱ መብት በህግ የተከበረ መሆኑ ብቻ በቂ ስላልሆነ ገና በእግራቸው መሄድ ከጀመሩ ህጻናት መዋያ ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የእነርሱን የኑሮ ዘይቤ አልፈልግም፣ አልደግፍም ከዚያም ጋር መተባበር አልሻም እነሱ ግን የፈለጋቸው መሆን ይችላሉ የሚሉ ሰዎችን ሁሉ ሃሳባቸውን በግድ እንዲቀበሉ በአደባባይና የመንግስትንም ስልጣን በመጠቀም እያራመዱ ናቸው። ይህ በአጋጣሚ አይደለም። የእግዚአር የፍርዱ ቀን ስለደረሰ የዓለም የዓመጽ ጽዋ መሙላት ስላለበት ነው።

ብዙዎቻችን የሳትነው ትልቅ ነገር አለ። እነዚህ የፈለግነውን ዓይነት ወሲብ መፈጸም መብታችን ነው (LGBTQ) ፣ ወይም ደግሞ ወንድና ሴት፣ አቶና ወይዘሮ፣ ወይም ልጅ እከሌና ወይዘሪት መባል አንፈልግም (Transgender) የሚሉ ሰዎች ፍላጎት ሌላው ሰው እንደፈለጋቸው ብሎ እንዲተዋቸው ብቻ ሳይሆን ሌላው ህዝብ እነሱ የሚሉትን እንዲልም  ነው። ጾታችንን እንደፈለግነው እንቀይራለን፣ ስንፈልግ ወንድ፣ስንፈልግ ሴት፣ ካልፈለግን ደግሞ በአንድ ጊዜ ወንድም ሴትም፣ ወይም ምንም ጾታ የሌለን ወይም ደግሞ ያልተወሰነና በየጊዜው የሚለዋወጥ ጾታ አለን ይላሉ። ስለዚህ በአዲሱ ህግ መሰረት መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎችም አንዳንድ የእምነት መጽሃፎች ህገ ወጥ ሊሆኑ ነው። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሰውን ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ይላል። የካናዳ መንግስት ይህን ህግ ሲያወጣ ታዲያ አንድ ሰው ክርስቲያን ነኝና እኔ የማምነው የሰው ዘር ወንድና ሴት እንደሆነ ነው ብሎ ቢናገር ወንጀለኛ ነው ማለት ነው። ይህ ይግ ከወጣ በኋላ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን በአደባባይ አንብቦ መስበክና ሰው ወንድና ሴት ብቻ ነው ማለት የጥላቻ ንግግር ስለሚሆን ወንጀል ሊሆን ነው። ይህን ህግ ያወጣው መንግስትና እኛ የዜና አውታሮች ብለው የምንሰማቸው ብዙዎቹ የቴሌቪዝን፣ የሬድዮ፣የጋዜጣ፣ የመጽሔትና የኢንተርኔት ተቋሞች ሁሉ ይህን ቢያስተባብሉ የሚሉት እውነት ነው ማለት አይደለም። ሰይጣን የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር ለመለየትና ለማጥፋት የፈጠረው ትልቁ መሳሪያ እውነት የሚመስል ውሸትን ነው። ይህ እውነት የሚመስል ውሸት በመጀመሪያ ሄዋንን ከዚያም አዳምን አታልሎ ዛሬ የሰው ልጅ ወደሚገኝበት መንፈሳዊ፣ ሞራላዊና ማህበረሰባዊ ውጥንቅጥ ውስጥ ከተተ። ይህን እውነት የሚመስል ውሸትን የመፍጠር እኩይ መሳሪያ ዛሬ በፖለቲካውና በንግዱ እንዲሁም መንፈሳዊ በሚመስሉና በሌሎችም የህይወት ዘርፎች ውስጥ በግልጽ ይሰራል። ይሰራል ግን አናየውም። በ20ኛው ክፍለ ዘመን ይህ መሳሪያ ከፈለፈላቸው ሃሳቦች አንዱ “ሰብዓዊ መብት” የሚባል ነው። ከላይ ሲመለከቱት “ሰብዓዊ መብት” መልካም ሃሳብ ይመስላል። ሰብዓዊ መብትን ሁላችንም እንወዳለን። መብታችንም እንዲከበር አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ እንከፍላለን። ችግሩ ያለው ግን “መብት” የሚለው ቃል ላይ ነው። ሰብዓዊ መብትን ለሰብዓዊ ፍጡር የሰጠው ማን ነው። ክርስቲያኖችና ሌሎችም የእምነት ሰዎች ይህን መብት ለሰው የሰጠው እግዚአብሔር ነው ብለን ስለምንቀበል ከበስተኋላው ክፉ ነገር አለ ብለን አናምንም። እግዚአብሔር የለም ወይም ደግሞ ብዙ አማልክት አሉ ብለው የሚያምኑ ደግሞ ሰብዓዊ መብትን ለሰው የሚሰጠው ሰው ራሱ፣ ማለትም መንግስታትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ናቸው ብለው ያምናሉ። ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች እንደምናምነው የእግዚአብሔርን ቃል ስለማይቀበሉ መልካምና ክፉ የሆነውን የሚወስን መንግስት፣ ግለሰቦችና ድርጅቶች እንጂ አምላክ አይደለም ብለው ያምናሉ። በእግዚአብሔር ቃል እውነትና በተፈጥሮ ህግ ላይ የተመሰረቱት የካናዳና ሌሎች አንዳንድ መንግስታት ህጎች አንድ በአንድ እየተቀየሩ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምን እውነተኛ ክርስቲያን ሁሉ እንደ ወንጀለኛ በሚቆጠርበት፣ ወንድን ወንድ፣ ሴትን ሴት ብሎ መጥራት በህግ በተከለከለበት አገር ልንኖር የቀረን ጊዜ በቀናት፣ምናልባትን በሳምንታት ወይም ቢበዛ በጥቂት ወራት ይቆጠራሉ። እኛንም ህግ ይጠብቀናል ብለን ካመንን ሃሳባችን መልካም ቢሆንም ዘመኑ መቀየሩ ግን አልገባንም። መንግስታት በህግ ሲተዳደሩ የኖሩባቸው ዘመናትና አገሮች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትንና በህሊና የተጻፉ የተፈጥሮ ህጎችን የሚያከብሩባቸው ብቻ ነበሩ። ዛሬም ከሞላ ጎደል እንዲሁ ነው። አሁን ግን ሰልጥኗል የሚባለው፣ በተለይም ደግሞ ሰሜን አሚሪካና ምእራብ አውሮፓ የስልጣኔው መሰረት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነትን ጥሎ በትልቅ ፍጥነት ዓለም ከ2ሺ ዘመን በፊት ወደነበረችበት አምልኮ ጣዖት፣ ገደብ የለሽ የፍትወተ ስጋ አስረሽ ምቺውና ክርስቲያኖችን ወደ ማሳደድ እየገባ ነው። ለራሳችንና ለቤተሰባችን እንጸልይ። ቶሎ ቶሎ ወንጌልን ላልሰሙ እናድርስ። በግል ህይወታችንም እምነታችንን ይዘን መኖር የምንችልባቸውን አማራጮች ማሰቢያው ጊዜ አሁን ነው። ከእንግዲህ በኋላ ግን እንደ ካናዳ ባሉ አንዳንድ ምእራባውያን አገሮች በእውነተኛ ክርስቲያናዊ ህይወት እየኖርንና፣ በህሊናችን ያለውን እየተናገርንና ልጆቻችንን በፈሪሃ እግዚአብሔር እያሳደግን በነጻነት ለመኖር እንችላለን ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።  ሁሉም ሲመሰቃቀልና ሲፈራርስ እውነተኛ ክርስቲያን በሰማይ ሃገር አለው። ዳግም እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ ያለው ጌታም አይዘገይም። ተስፋ አንቆርጥም፣ ተስፋችን ግን በፍጹም ከዚህ ምድር በሆኑ ነገሮች ላይ ሊሆን አይችልም። ሰማያዊውን ተስፋ ላላወቁ ወገኖቻችን ግን የዚህን ጌታ ማዳን ቶሎ ቶሎ እንንገራቸው። ጌታ ይባርካችሁና ይጠብቃችሁ። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

የመለከት ድምጽ መጽሔት ቁጥር 8

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ ለዘላለምም ያው ነው ብለን ካመንን በሐዋርያት ዘመንና ከነሱም በኋላ በነበረችው እውነተኛይቱ ቤት ክርስቲያን ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ ዛሬም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑትን በመንፈስ ቅዱስ ይሞላቸዋል ወይ?
ዛሬም እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተአምራትን ይሰራል ወይ? በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመንም እንደ ትንቢት ያሉ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አሉ? ይሰራሉ? ዛሬም እግዚአብሔር ነቢያትን ይልካል? የሚሉ ጥያቄዎች በብዙ መድረኮች ይነሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ለነዚህ ጥያቄዎች ሙሉና የማያሻማ መልሶች አሉት። እነዚህንና ከነዚህ ጋር በተያያዙ ሃሳቦች ላይ ትምህርቶችንና ትንተናዎችን ይዛ የመለከት ድምጽ ቁጥር 8 ዛሬ ወጥታለች።በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘለዓለም ሕይወትን ያገኙ ቅዱሳን ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ሙላትንና የእርሱን ድንቅ ስራዎችን በተመለከተ ትምህርትና መጽናናት እንዲያገኙበት ጸሎቴ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ገና ያልተቀበሉት ወገኖቼም ደግሞ የሰው ዘር ብቸኛ የመዳን ተስፋ የሆነውን ይህን ጌታ እንዲቀበሉት የልቤ ምኞችና ጸሎት ነው። እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ

ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል። ማቴዎስ 24፡7


የጌታ ዳግም ምጽዓት ሲቃረብ በምድር ላይ እየበዙ ከሚሄዱት ነገሮች አንዱ ቸነፈር ነው። እንደ ቀላሉ መልከት ብለን የምናልፈው "ቸነፈር" የሚለው ቃል ብዙ ህዝብን የሚጨርሱ በሽታዎችን የሚያመለክት ነው። የጌታ ቃል ቸነፈር ይሆናል አለ እንጂ ጌታ አምላክ ራሱ ቸነፈርን ይልካል አላለም። ኤች አይ ኤይድ ፓርኪንሰንስ፣ አልዛይመርስ፣ ዚካ፣ ኢቦላና ካንሰር ከቸነፈር አንዳንዶቹ ናቸው። ሃኪሞቻችን ካንሰር እንዴት እንደሚመጣ አናውቅም ይሉናል። የምርምር ድርጅቶች ነን የሚሉ ለካንሰር መፍትሔ እንፈልጋለን እያሉ በየጊዜው ገንዘብ አምጡ ይሉናል። እውነቱ ግን የእነዚህ በሽታዎች ዋነኛ መሰረቶቻቸው ሰው ሰራሽ ናቸው።  ሳያውቁ እናውቃለን በሚሉ አዋቂዎቻችን ተሰርተው፣ ገንዘብን በቀላሉ ማካበት በሚፈልጉ ሃብታሞች ተመርተው በምግባችን፣ በልብሳችን፣ በምንጠቀምባቸው እቃዎችና በምንተነፍሰው አየር እንዲሁም በምንውጠው መድኃኒትም ውስጥ ሳይቀር እንደ ካንሰር ያሉ ብቹ በሽታዎችን የሚያመጡት አንድ ጊዜ ብርቅና ድንቅ ተደርገው የቀረቡ የቴክኖሎጂና የስልጣኔ ውጤት የተባሉ ኬሚካሎች ናቸው። ሌሎቹ የቸነፈር ምንጮች ደግሞ ከላቦራቶሪ አምልጠው የሚወጡ ወይም በእንስሳትና በሰዎች ላይ ሲሞከሩ ሳያስቧቸው የሚሰራጩ ኃያላኑ አገሮች ሆን ብለው ለጠላቶቻቸው ማጥፊያ የሚሰሩአቸው ጀርሞች ናቸው። በተያያዘው በዚህ ዜና ላይ የምናነበው ሪፖርት እጅግ ብዙ ከሆኑትና ዛሬ በሰፊው ከሚገኙት ተጨባጭ መረጃዎች አንዱ ነው። ሰው አንብቦ ሊጨርሳቸው የማይችሉ ብዙ መጻህፍት በዶክተሮችተመራማሪዎች፣ ጋዜጠኞችና መርማሪዎችም ሳይቀር በዚህ ጉዳይ ላይ ተጽፈዋል። አፈሩ፣ ባህሩ፣ አየሩ በመርዛማ ንጥረ ነገሮች እጅግ ተመርዟል እየተመረዘም ነው፤ በተለይ ደግሞ አድገናል፣ በልጽገናል በሚባሉት አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ምእራብ አውሮፓና ሌሎችም በኢንዱስትሪ ገፍተዋል በሚባሉ አገሮች። ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ሃኪም ጋ ስንሄድና ሃኪሙ የበሽታህ ምንጭ ምን እንደሆነ አይታወቅም ቢለን ያን የሚለን የግድ እውነት ስለሆነ ሳይሆን ሌላ ምን ማለት እንደሚገባው ስለማያውቅ ወይም ደግሞ ችግሩ ይሄ ወይም ያ ነው ቢል ጣጣ ውስጥ ስለሚገባ ነው። የዶክተሩ ስራ የተነገሩትን መድሃኒት አይነቶች ለተነገሩት በሽታዎች መስጠት ብቻ ነው። ከዚያ ያለፈው አይገደውም ወይም ምንም ለማድረግ አቅሙ የለውም። ለህይወታችንም ሆነ ለጤናችን የሚገደው አምላክ ግን በሰማይ አለ። እኛም ደግሞ እንደ ባለ አእምሮ ለመረዳት በምንችለው መጠን የምንበላ የምንጠጣውን፣ የምናሸት የምንለብሰውን ወይም የምንጠምበትን እቃ ለማወቅ እንሞክር። ሊሆን የተጻፈው ሁሉ ይሆናል። በምንም ልንታወክ አይገባንም።  ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ፣ በተረፈው ደግሞ ሁሉን በሚችለው ጌታ እንታመን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ወላጆች የልጆቻቸውን ወሲባዊና ጾታዊ ምርጫ ካላከበሩ ልጆቻቸውን መንግስት ሊነጥቅ የሚያስችል ህግ ኦንታሪዮ ካናዳ አወጣ


ያለንበት ዘመን በማቴዎስ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው የኖህን እንዲሁም የሰዶምንና የገሞራን ዘመን መምሰሉ እለት በእለት እየተረጋገጠ መጥቷል። እያንዳንዱ ሰው በህይወቱ ላይ የሚፈልገውን የመወሰን መብቱ የተሰጠው በፈጣሪ ነው። ሰው ትክክለኛ ውሳኔንም ማድረግ የሚያስችለውን የሚያስብ አእምሮ ፈጣሪ ሰጥቶታል። ፈጣሪ ማንም ለዘለዓለም እንዳይጠፋም ከኃጢዓት የመዳን መንገድን በክርስቶስ አዘጋጅቶአል። ይህ ያለንበትን ዘመን ከኖህና ከሎጥ ዘመን ጋር የሚያመሳስለውና የእግዚአብሔርም የፍርድ ቀን እጅግ እንደተቃረበ የሚያሳየን አንዱ ነገር ሰዎች በግል ህይወታቸው የሚፈልጉትን ዓመጽና ኃጢዓት በአደባባይ ምርጫቸው ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎች ሰዎች ደግሞ እንደነሱ የራሳቸውን ምርጫ በማድረግ ወይም እንደ እምነታቸው መኖር እንዳይችሉ በግልጽ የሌሎችን መብት ለመጋፋት መነሳሳታቸው ነው። በተለይ ሰልጥነናል በሚባሉ እንደ ካናዳና አንዳንድ የምእራብ አውሮፓ ባሉ አገሮች ሰዶማዊነትን ምርጫቸው ያደረጉ ሰዎች ዛሬ እያደረጉ ያሉት ለመብታቸው መከራከር ሳይሆን፣ ይህን የኑሮ ዘይቤ የማይቀበሉትን ሰዎች በሙሉ በአንድም በሌላም መንገድ መጋፋትና ኑሮአቸውን ለማፍረስ መሞከር ነው። በነዚህ አገሮች ውስጥ ይህን የኑሮ ዘይቤ የሚከተሉ ሰዎች አናሳ ነንና መብታችን ይከበር የሚሉ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎችን ሲያነሱ ከቆዩና መብታቸው ከተከበረ በኋላ፣ እንዲሁም ደግሞ በእኩልነት መብታቸው በመጠቀም በመገናኛ ብዙኃን በትምህርት ተቋሞችና በመንግስታዊ ስልጣን ቦታዎች ላይ ከተቀመጡ በኋላ የነሱን ምርጫ የማይቃወሙትን፣ ነገር ግን ለራሳቸው እንደ እምነታቸውና እንደ ህሊናቸው መኖር የሚፈልጉትን ሰዎች መብት የሚጋፉና የሚያውኩ፣ ሌሎች ሃገራዊና አለም አቀፋዊ ህጎችን የሚጻረፉ ህጎችን በማውጣት፣ ዜና መሰል ፕሮፓጋንዳዎችን በማናፈስ፣ በየትምህርት ቤቱና ዩኒቨርሲቲዎች ልጆችን በተጽእኖ የነሱን የኑሮ ዘይቤ ለማስተማር በድፍረት እየሰሩ ይገኛሉ። እጅግ የሚያስፈራው ግን እነሱ የራሳቸውን የኑሮ ዘይቤ ለማስፋፋት መሞከራቸው ሳይሆን የሌሎችን ሰብዓዊና በአምላክ የተሰጡ የህሊናና የእምነት ነጻነት መጻረራቸው ነው። በዚህ ዜና ላይ እንደተያያዘው በቅርቡ በዚህ በኦንታሪዮ ካናዳ ተቀይሮ የወጣው ህግ ለምሳሌ ክርስቲያኖች፣ የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ወይም እምነት ባይኖራቸውም የሰዶማዊነትን የኑሮ ዘይቤ የማይቀበሉ  ሰዎች ምናልባት ልጆቻቸው ወንዱ ሴት ነኝ፣ ወይም ሴቷ ወንድ ነኝ ብትልና ቤተሰብ ደግሞ በዚህ ባይስማማ መንግስት ልጆቹን ከወላጆቹ መንጠቅ እንዲችል መብት የሚሰጥ ነው። ይህ በሌላው ዓለም እስከ ዛሬ ታይቶ የማይታወቅ ህገ ወጥ ህግ ሲወጣ በህጋዊ መንገድ ለመቃወም የተነሱት ብዙዎች አይደሉም። ከህዝቡ 80 በመቶ የሚሆነው ክርስቲያን (ካቶሊክና ፕሮቴስታንት) በሚባልበት በካናዳ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ በሌላው ዓለም ያለው ሰው ቢደነቅ አያስገርምም። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የዚሁ የኦንታሪዮ ክፍለ ሃገር መሪ የሆኑት ሴት የሰዶማዊነትን የኑሮ ዘይቤ የሚከተሉ መሆናቸው ነው። ወዮ ለዘመኑ፣ ወዮ ለምድር የሚያሰኝ ዘመን ላይ ደርሰናል። ክርስቲያን የሆነ ካናዳዊ ሁሉ ይህን በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ድምጹን በማሰማት ሊቃወም ይገባል።  ከዚህ በላይ ግን ክርስቲያን ሁሉ ለኒህ የኦንታሪዮ ጠቅላይ ሚኒስር፣ ይህን ህግ ላረቀቁ ሚኒስትሮቻቸውና ላጸደቀው ፓርላማም ሊጸልይ ያስፈልጋል። በዮሐንስ ራዕይ ላይ ጌታ አምላክ ዓመጸኛው ያምጽ፣ ጻድቁም ጽድቁን ያድርግ ብሎ የሰው ልጅ ሁሉ የህይወቱን አቅጣጫ እንዲመርጥ ስልጣኑን ሰጥቶታል። ይኸው የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የዘላለምን ህይወት እንዲመርጡ ያስተምራል። ምርጫው የእያንዳንዱ ሰው ነው። አገርን በህግ እናስተዳድራለን ብለው የመንግስትን ስልጣን ከያዙ በኋላ የህዝብን መሰረታዊ የእምነትና የህሊና ነጻነት የሚጻረሩ ህጎችን ማውጣት ግን ኢሰብአዊ ብቻ ሳይሆን ሰይጣናዊም ነው። እንደ ለኦንታሪዮ ላሉ መንግስታት እንጸልይ። መብቱ ያለንም በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ አመጽን ለመቃወም ድምጻችንን እናንሳ። በጌታ ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።


የወደቁት መላእክት ዘሮች ኔፊሊም በአዲስ ስም ET ALIENS ተብለው ለዓለም እየቀረቡ ነው

የወደቁት መላእክት ዘሮች ኔፊሊም በአዲስ ስም ET ALIENS ተብለው ለዓለም እየቀረቡ ነው

የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፣ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።ሉቃስ 8፡17

ሰልጥነናል የሚለው የዚህ ዘመን ሰው በቀላሉ እንዲቀበሉአቸው በዘመናዊ ስም “ALIENS”  “EXTRA-TERRESTRIALS” “MARTIANS”  ወዘተ ይሉአቸዋል። የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስና የህዋ ምርምር ማእከላቸው ባለስልጣኖች ከእኛ ከሰው የተሻሉ፣ የበለጡ፣ ምናልባትም ኃጢዓት የሌለባቸውና የሰውን ዘር ከችግሩ እንዲወጣ ሊረዱ የሚችሉ ይሆናሉ ብለዋቸዋል። ስለማይታወቁ በራሪ ዲስኮችና ስለነዚህ ፍጡራን የሚያወሩ ሰዎች አእምሮአቸው ትክክል ያልሆነ፣ የቃዡ፣ ወይም በ “CONSPIRACY THEORY” የሚያምኑ ብቻ ናቸው ሲባል ከርሞአል። ታላላቆቹ የዓለም መንግስታት ብዙ መረጃ ቢኖራቸውም ጸጥታንና መረጋጋትን ያሰጋል በማለት በከፍተኛ ምስጢር የያዙት ጉዳይ ነው። ባለፈው ዓመት ለምርጫ የተወዳደሩት ሂላሪ ክሊንተን እኔ ብመረጥ ይህ ጉዳይ ወደ አደባባይ እንዲወጣ ለማድረግ እሞክራለሁ ብለው ነበር። በተያያዘው ዜና ላይ የቀረበው ከአሜሪካ ዋና ዋና የህዋ ምርምር ባለሙያዎች አንዱና እጅግ ባለጸጋ የሆኑት ሮበርት ቢገሎ እነዚህ ፍጡራን መኖርና ምድርን መጎብኘት ብቻ ሳይሆን ዛሬ በምድር ላይ አሉ ብለው ሲናገሩ ይሰማሉ። እነሱ ምንም ሆነ ምን ስም ይስጡአቸው እንጂ እነዚህ ነገሮች አዲስ ወይም ከሌላ ዓለማት የመጡና ከሰው በላይ የሰለጠኑ ፍጥረታት አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በምድር ላይ የተከሰቱት በኖህ ዘመን እንደነበር ይገልጻል። ስማቸው ኔፊሊም፣ ራፋይም፣ አናቃውያን ወዘተ በማለት ይጠቅሳቸዋል። የወደቁ መላእክት ከሰው ሴቶች ልጆች ጋር ዘራቸውን በማደባለቅ የፈጠሩአቸው እኩይ ፍጥረታት ናቸው። ሲሞቱ አጋንንት የሆኑት እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው የመጨረሻው ዘመን ላይ ስለደረስን ዛሬ ደግሞ እንደገና መምጣት ጀምረዋል ማለት ነው። እኒህ ባለሙያና ሌሎች ብዙ ጉዳዩን በጥልቅ የሚመራመሩና ከነዚህ ፍጥረታት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያደረጉ አዋቂዎች እንደሚናገሩት ፍጥረታቱ በድብቅ ለአንዳንድ ታላላቅ መንግስታት ጋር ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎችን (በተለይም ደግሞ የጦርነት ቴክኖሎጂዎችን) ሲያቀብሉ ኖረዋል የሚሉም ብዙ መረጃዎች አሉ። ይህ መረጃ ጥቂት በጥቂት ወደ አደባባይ እየወጣ ነው። ለምሳሌ የእንግሊዝ መንግስት በሚቀጥሉት ጥቂት ወሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አንዳንድ መረጃ ወደ አደባባይ ያወጣል። ባለፈው ዓመት CIA የሚባለው የአሜሪካ ስለላ ድርጅትም ትንሽ መረጃ ለቅቆ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ የመጨረሻው ጨዋታ መንፈሳዊ ነው። ከእኛ ይሻላሉ፣ እንዲያውም የፈጠሩን እነሱ ናቸው የሚሉና የሚያመልኳቸውም አሉ። የሮም፣ የግሪክ፣ የግብጽ ጀግኖች፣ ግዙፍ ሰዎች፣ አማልክትና ነገስታት የነበሩትም ከነዚሁ ወገን መሆናቸው ተዘግቦአል። በተለያየ ቀውስ ውስጥ የምትታገለው ዓለማችን ከኛ የተሻሉ መሪዎች ያስፈልጓታልና እነሱ ሊረዱን መጡ ቢባል ብዙ ሰው ሊቀበለው ይችላል ተብሎ ስለተገመተ ነው ኔፊሊም ዘመናዊ ስም ተሰጥቶአቸው እየተገለጹ ያሉት። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ምድርን ሁሉ የሚያስተው ሃሰተኛው ክርስቶስ የሚገለጽበት ዘመን ምናልባት ተቃርቦ ይሆን? ከነዚህ መካከል ወይም የነዚህ ALIENS ወይም EXTRA TERRESTRIALS መሪ ይሆን እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ የሚገለጸው? ጊዜ ይገልጸዋል። ክርስቲያን ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሱን ገልጾ የማጥኛውና የሚሰሙትን ዜናዎች በእግዚአብሔር ቃል መሰረት መመዘኛው ጊዜም ዛሬ ነው። አለበለዚያ የምንሰማው ሁሉ እውነት እየመሰለን ልንስት እንችላለን። በጌታ ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...