ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል። ማቴዎስ 24፡7


የጌታ ዳግም ምጽዓት ሲቃረብ በምድር ላይ እየበዙ ከሚሄዱት ነገሮች አንዱ ቸነፈር ነው። እንደ ቀላሉ መልከት ብለን የምናልፈው "ቸነፈር" የሚለው ቃል ብዙ ህዝብን የሚጨርሱ በሽታዎችን የሚያመለክት ነው። የጌታ ቃል ቸነፈር ይሆናል አለ እንጂ ጌታ አምላክ ራሱ ቸነፈርን ይልካል አላለም። ኤች አይ ኤይድ ፓርኪንሰንስ፣ አልዛይመርስ፣ ዚካ፣ ኢቦላና ካንሰር ከቸነፈር አንዳንዶቹ ናቸው። ሃኪሞቻችን ካንሰር እንዴት እንደሚመጣ አናውቅም ይሉናል። የምርምር ድርጅቶች ነን የሚሉ ለካንሰር መፍትሔ እንፈልጋለን እያሉ በየጊዜው ገንዘብ አምጡ ይሉናል። እውነቱ ግን የእነዚህ በሽታዎች ዋነኛ መሰረቶቻቸው ሰው ሰራሽ ናቸው።  ሳያውቁ እናውቃለን በሚሉ አዋቂዎቻችን ተሰርተው፣ ገንዘብን በቀላሉ ማካበት በሚፈልጉ ሃብታሞች ተመርተው በምግባችን፣ በልብሳችን፣ በምንጠቀምባቸው እቃዎችና በምንተነፍሰው አየር እንዲሁም በምንውጠው መድኃኒትም ውስጥ ሳይቀር እንደ ካንሰር ያሉ ብቹ በሽታዎችን የሚያመጡት አንድ ጊዜ ብርቅና ድንቅ ተደርገው የቀረቡ የቴክኖሎጂና የስልጣኔ ውጤት የተባሉ ኬሚካሎች ናቸው። ሌሎቹ የቸነፈር ምንጮች ደግሞ ከላቦራቶሪ አምልጠው የሚወጡ ወይም በእንስሳትና በሰዎች ላይ ሲሞከሩ ሳያስቧቸው የሚሰራጩ ኃያላኑ አገሮች ሆን ብለው ለጠላቶቻቸው ማጥፊያ የሚሰሩአቸው ጀርሞች ናቸው። በተያያዘው በዚህ ዜና ላይ የምናነበው ሪፖርት እጅግ ብዙ ከሆኑትና ዛሬ በሰፊው ከሚገኙት ተጨባጭ መረጃዎች አንዱ ነው። ሰው አንብቦ ሊጨርሳቸው የማይችሉ ብዙ መጻህፍት በዶክተሮችተመራማሪዎች፣ ጋዜጠኞችና መርማሪዎችም ሳይቀር በዚህ ጉዳይ ላይ ተጽፈዋል። አፈሩ፣ ባህሩ፣ አየሩ በመርዛማ ንጥረ ነገሮች እጅግ ተመርዟል እየተመረዘም ነው፤ በተለይ ደግሞ አድገናል፣ በልጽገናል በሚባሉት አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ምእራብ አውሮፓና ሌሎችም በኢንዱስትሪ ገፍተዋል በሚባሉ አገሮች። ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ሃኪም ጋ ስንሄድና ሃኪሙ የበሽታህ ምንጭ ምን እንደሆነ አይታወቅም ቢለን ያን የሚለን የግድ እውነት ስለሆነ ሳይሆን ሌላ ምን ማለት እንደሚገባው ስለማያውቅ ወይም ደግሞ ችግሩ ይሄ ወይም ያ ነው ቢል ጣጣ ውስጥ ስለሚገባ ነው። የዶክተሩ ስራ የተነገሩትን መድሃኒት አይነቶች ለተነገሩት በሽታዎች መስጠት ብቻ ነው። ከዚያ ያለፈው አይገደውም ወይም ምንም ለማድረግ አቅሙ የለውም። ለህይወታችንም ሆነ ለጤናችን የሚገደው አምላክ ግን በሰማይ አለ። እኛም ደግሞ እንደ ባለ አእምሮ ለመረዳት በምንችለው መጠን የምንበላ የምንጠጣውን፣ የምናሸት የምንለብሰውን ወይም የምንጠምበትን እቃ ለማወቅ እንሞክር። ሊሆን የተጻፈው ሁሉ ይሆናል። በምንም ልንታወክ አይገባንም።  ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ፣ በተረፈው ደግሞ ሁሉን በሚችለው ጌታ እንታመን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...