ወላጆች የልጆቻቸውን ወሲባዊና ጾታዊ ምርጫ ካላከበሩ ልጆቻቸውን መንግስት ሊነጥቅ የሚያስችል ህግ ኦንታሪዮ ካናዳ አወጣ


ያለንበት ዘመን በማቴዎስ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው የኖህን እንዲሁም የሰዶምንና የገሞራን ዘመን መምሰሉ እለት በእለት እየተረጋገጠ መጥቷል። እያንዳንዱ ሰው በህይወቱ ላይ የሚፈልገውን የመወሰን መብቱ የተሰጠው በፈጣሪ ነው። ሰው ትክክለኛ ውሳኔንም ማድረግ የሚያስችለውን የሚያስብ አእምሮ ፈጣሪ ሰጥቶታል። ፈጣሪ ማንም ለዘለዓለም እንዳይጠፋም ከኃጢዓት የመዳን መንገድን በክርስቶስ አዘጋጅቶአል። ይህ ያለንበትን ዘመን ከኖህና ከሎጥ ዘመን ጋር የሚያመሳስለውና የእግዚአብሔርም የፍርድ ቀን እጅግ እንደተቃረበ የሚያሳየን አንዱ ነገር ሰዎች በግል ህይወታቸው የሚፈልጉትን ዓመጽና ኃጢዓት በአደባባይ ምርጫቸው ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎች ሰዎች ደግሞ እንደነሱ የራሳቸውን ምርጫ በማድረግ ወይም እንደ እምነታቸው መኖር እንዳይችሉ በግልጽ የሌሎችን መብት ለመጋፋት መነሳሳታቸው ነው። በተለይ ሰልጥነናል በሚባሉ እንደ ካናዳና አንዳንድ የምእራብ አውሮፓ ባሉ አገሮች ሰዶማዊነትን ምርጫቸው ያደረጉ ሰዎች ዛሬ እያደረጉ ያሉት ለመብታቸው መከራከር ሳይሆን፣ ይህን የኑሮ ዘይቤ የማይቀበሉትን ሰዎች በሙሉ በአንድም በሌላም መንገድ መጋፋትና ኑሮአቸውን ለማፍረስ መሞከር ነው። በነዚህ አገሮች ውስጥ ይህን የኑሮ ዘይቤ የሚከተሉ ሰዎች አናሳ ነንና መብታችን ይከበር የሚሉ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎችን ሲያነሱ ከቆዩና መብታቸው ከተከበረ በኋላ፣ እንዲሁም ደግሞ በእኩልነት መብታቸው በመጠቀም በመገናኛ ብዙኃን በትምህርት ተቋሞችና በመንግስታዊ ስልጣን ቦታዎች ላይ ከተቀመጡ በኋላ የነሱን ምርጫ የማይቃወሙትን፣ ነገር ግን ለራሳቸው እንደ እምነታቸውና እንደ ህሊናቸው መኖር የሚፈልጉትን ሰዎች መብት የሚጋፉና የሚያውኩ፣ ሌሎች ሃገራዊና አለም አቀፋዊ ህጎችን የሚጻረፉ ህጎችን በማውጣት፣ ዜና መሰል ፕሮፓጋንዳዎችን በማናፈስ፣ በየትምህርት ቤቱና ዩኒቨርሲቲዎች ልጆችን በተጽእኖ የነሱን የኑሮ ዘይቤ ለማስተማር በድፍረት እየሰሩ ይገኛሉ። እጅግ የሚያስፈራው ግን እነሱ የራሳቸውን የኑሮ ዘይቤ ለማስፋፋት መሞከራቸው ሳይሆን የሌሎችን ሰብዓዊና በአምላክ የተሰጡ የህሊናና የእምነት ነጻነት መጻረራቸው ነው። በዚህ ዜና ላይ እንደተያያዘው በቅርቡ በዚህ በኦንታሪዮ ካናዳ ተቀይሮ የወጣው ህግ ለምሳሌ ክርስቲያኖች፣ የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ወይም እምነት ባይኖራቸውም የሰዶማዊነትን የኑሮ ዘይቤ የማይቀበሉ  ሰዎች ምናልባት ልጆቻቸው ወንዱ ሴት ነኝ፣ ወይም ሴቷ ወንድ ነኝ ብትልና ቤተሰብ ደግሞ በዚህ ባይስማማ መንግስት ልጆቹን ከወላጆቹ መንጠቅ እንዲችል መብት የሚሰጥ ነው። ይህ በሌላው ዓለም እስከ ዛሬ ታይቶ የማይታወቅ ህገ ወጥ ህግ ሲወጣ በህጋዊ መንገድ ለመቃወም የተነሱት ብዙዎች አይደሉም። ከህዝቡ 80 በመቶ የሚሆነው ክርስቲያን (ካቶሊክና ፕሮቴስታንት) በሚባልበት በካናዳ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ በሌላው ዓለም ያለው ሰው ቢደነቅ አያስገርምም። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የዚሁ የኦንታሪዮ ክፍለ ሃገር መሪ የሆኑት ሴት የሰዶማዊነትን የኑሮ ዘይቤ የሚከተሉ መሆናቸው ነው። ወዮ ለዘመኑ፣ ወዮ ለምድር የሚያሰኝ ዘመን ላይ ደርሰናል። ክርስቲያን የሆነ ካናዳዊ ሁሉ ይህን በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ድምጹን በማሰማት ሊቃወም ይገባል።  ከዚህ በላይ ግን ክርስቲያን ሁሉ ለኒህ የኦንታሪዮ ጠቅላይ ሚኒስር፣ ይህን ህግ ላረቀቁ ሚኒስትሮቻቸውና ላጸደቀው ፓርላማም ሊጸልይ ያስፈልጋል። በዮሐንስ ራዕይ ላይ ጌታ አምላክ ዓመጸኛው ያምጽ፣ ጻድቁም ጽድቁን ያድርግ ብሎ የሰው ልጅ ሁሉ የህይወቱን አቅጣጫ እንዲመርጥ ስልጣኑን ሰጥቶታል። ይኸው የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የዘላለምን ህይወት እንዲመርጡ ያስተምራል። ምርጫው የእያንዳንዱ ሰው ነው። አገርን በህግ እናስተዳድራለን ብለው የመንግስትን ስልጣን ከያዙ በኋላ የህዝብን መሰረታዊ የእምነትና የህሊና ነጻነት የሚጻረሩ ህጎችን ማውጣት ግን ኢሰብአዊ ብቻ ሳይሆን ሰይጣናዊም ነው። እንደ ለኦንታሪዮ ላሉ መንግስታት እንጸልይ። መብቱ ያለንም በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ አመጽን ለመቃወም ድምጻችንን እናንሳ። በጌታ ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ

በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...