የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፣ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።ሉቃስ 8፡17
ሰልጥነናል የሚለው የዚህ ዘመን ሰው በቀላሉ እንዲቀበሉአቸው በዘመናዊ ስም “ALIENS”
“EXTRA-TERRESTRIALS” “MARTIANS” ወዘተ
ይሉአቸዋል። የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስና የህዋ ምርምር ማእከላቸው ባለስልጣኖች ከእኛ ከሰው የተሻሉ፣ የበለጡ፣ ምናልባትም ኃጢዓት
የሌለባቸውና የሰውን ዘር ከችግሩ እንዲወጣ ሊረዱ የሚችሉ ይሆናሉ ብለዋቸዋል። ስለማይታወቁ በራሪ ዲስኮችና ስለነዚህ ፍጡራን የሚያወሩ
ሰዎች አእምሮአቸው ትክክል ያልሆነ፣ የቃዡ፣ ወይም በ “CONSPIRACY
THEORY” የሚያምኑ
ብቻ ናቸው ሲባል ከርሞአል። ታላላቆቹ የዓለም መንግስታት ብዙ መረጃ ቢኖራቸውም ጸጥታንና መረጋጋትን ያሰጋል በማለት በከፍተኛ ምስጢር
የያዙት ጉዳይ ነው። ባለፈው ዓመት ለምርጫ የተወዳደሩት ሂላሪ ክሊንተን እኔ ብመረጥ ይህ ጉዳይ ወደ አደባባይ እንዲወጣ ለማድረግ
እሞክራለሁ ብለው ነበር። በተያያዘው ዜና ላይ የቀረበው ከአሜሪካ ዋና ዋና የህዋ ምርምር ባለሙያዎች አንዱና እጅግ ባለጸጋ የሆኑት
ሮበርት ቢገሎ እነዚህ ፍጡራን መኖርና ምድርን መጎብኘት ብቻ ሳይሆን ዛሬ በምድር ላይ አሉ ብለው ሲናገሩ ይሰማሉ። እነሱ ምንም
ሆነ ምን ስም ይስጡአቸው እንጂ እነዚህ ነገሮች አዲስ ወይም ከሌላ ዓለማት የመጡና ከሰው በላይ የሰለጠኑ ፍጥረታት አይደሉም። መጽሐፍ
ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በምድር ላይ የተከሰቱት በኖህ ዘመን እንደነበር ይገልጻል። ስማቸው ኔፊሊም፣ ራፋይም፣ አናቃውያን ወዘተ በማለት
ይጠቅሳቸዋል። የወደቁ መላእክት ከሰው ሴቶች ልጆች ጋር ዘራቸውን በማደባለቅ የፈጠሩአቸው እኩይ ፍጥረታት ናቸው። ሲሞቱ አጋንንት
የሆኑት እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው የመጨረሻው ዘመን ላይ ስለደረስን ዛሬ ደግሞ እንደገና መምጣት ጀምረዋል ማለት ነው።
እኒህ ባለሙያና ሌሎች ብዙ ጉዳዩን በጥልቅ የሚመራመሩና ከነዚህ ፍጥረታት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያደረጉ አዋቂዎች
እንደሚናገሩት ፍጥረታቱ በድብቅ ለአንዳንድ ታላላቅ መንግስታት ጋር ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎችን (በተለይም ደግሞ የጦርነት ቴክኖሎጂዎችን)
ሲያቀብሉ ኖረዋል የሚሉም ብዙ መረጃዎች አሉ። ይህ መረጃ ጥቂት በጥቂት ወደ አደባባይ እየወጣ ነው። ለምሳሌ የእንግሊዝ መንግስት
በሚቀጥሉት ጥቂት ወሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አንዳንድ መረጃ ወደ አደባባይ ያወጣል። ባለፈው ዓመት CIA የሚባለው የአሜሪካ ስለላ ድርጅትም ትንሽ መረጃ ለቅቆ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ የመጨረሻው ጨዋታ
መንፈሳዊ ነው። ከእኛ ይሻላሉ፣ እንዲያውም የፈጠሩን እነሱ ናቸው የሚሉና የሚያመልኳቸውም አሉ። የሮም፣ የግሪክ፣ የግብጽ ጀግኖች፣
ግዙፍ ሰዎች፣ አማልክትና ነገስታት የነበሩትም ከነዚሁ ወገን መሆናቸው ተዘግቦአል። በተለያየ ቀውስ ውስጥ የምትታገለው ዓለማችን
ከኛ የተሻሉ መሪዎች ያስፈልጓታልና እነሱ ሊረዱን መጡ ቢባል ብዙ ሰው ሊቀበለው ይችላል ተብሎ ስለተገመተ ነው ኔፊሊም ዘመናዊ ስም
ተሰጥቶአቸው እየተገለጹ ያሉት። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ምድርን ሁሉ የሚያስተው ሃሰተኛው ክርስቶስ የሚገለጽበት ዘመን ምናልባት
ተቃርቦ ይሆን? ከነዚህ መካከል ወይም የነዚህ ALIENS
ወይም EXTRA TERRESTRIALS መሪ ይሆን እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ የሚገለጸው? ጊዜ ይገልጸዋል።
ክርስቲያን ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሱን ገልጾ የማጥኛውና የሚሰሙትን ዜናዎች በእግዚአብሔር ቃል መሰረት መመዘኛው ጊዜም ዛሬ ነው። አለበለዚያ
የምንሰማው ሁሉ እውነት እየመሰለን ልንስት እንችላለን። በጌታ ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ