የኢሉሚናቲን ምስጢር የሚያሳዩ ዘግናኝ የባእድ አምልኮ ልብሶችና ጌጦች እንደ ፋሽን በለንደን ከተማ ቀረቡ ተባለ።
በመጨረሻው ዘመን መጨረሻ ላይ መሆናችንን ገና ለሚጠራጠሩ ብዙ ማስረጃዎች በግልጽ ወደ አደባባይ እየወጡ ነው። ከዛሬ ጥቂት ዓመታት በፊት እንኳን "ኢሉሚናቲ" የሚባል የምስጢር ድርጅት አለ ብሎ የሚያወራ ምንም እንደማያውቅ ወይም መሰረት የሌለውን የሴራ ወሬ የሚያምን ሰው ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ኢሉሚናቲ ማለት በላቲን ቋንቋ "የበራላቸው" "የተገለጸላቸው" "ሰው የማይውቀውን ትልቅ ምስጢር የሚያውቁ" ወዘተ ማለት ነው። በዚህ ስም ስር የታቀፉ እጅግ ብዙ የምስጢር ድርጅቶች አሉ። የነዚያ ድርጅት አባላት በምድር ላይ ታላላቅ፣ ሃብታም፣ ዝነኛ፣ ባለስልጣን፣ ዘፋኞች፣ ተዋናዮች ናቸው። በዚህ ልንደነቅ አይገባም። ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሰይጣንን "የዚህ ዓለም ገዥ" ብሎ በተደጋጋሚ በወንጌል ላይ ጠርቶታል። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክነት (ወልድነት) እና ፍጹም ሰው ሆኖ መምጣቱን፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ በመስቀል ላይ መሞቱን፣ በሶስተኛው ቀን መነሳቱ፣ በክብር ማረጉንና ዳግም ተመልሶ መምጣቱን ከሚያምኑ ክርስቲያኖች በስተቀር ዓለም በሙሉ ዛሬ የሚገዛው በዚህ ዓለም ገዥ በዲያብሎስ ነው። ይህን ዲያብሎስ ነው በተለያየ ስም እያሽሞነሞኑ ትልቅ ምስጢር አድርገው ሊያቀርቡልን የሚሹት። የኢሉሚናቲ አባላትና አጃቢዎቻቸው ያውቁታል የሚባለው ትልቅ ምስጢር ደግሞ "ሉሲፈር" ወይም "ዲያብሎስ" አምላክ ነው ብለው መቀበላቸውን ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈው ውጭ አንድም አዲስ ነገር ወይም ምስጢር የለም። በኤደን ገነት ሄዋንን እና አዳምን ያሳተው ያ የቀደመው እባብ በየዘመናቱ በተለያየ ስም የሰውን ዘር ሲያታልል ቆይቶ አሁን ደግሞ ታዋቂ፣ ሃብታም፣ ዝነኛና ባለ ስልጣን በሚባሉ ሰዎች በመጠቀም የሰውን ዘር እንደ ኖህ ዘመን፣ እንደ ሰዶምና ገሞራ ለሳትና ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቷል። መጽሐፍ ቅዱሱን የሚያነብ ክርስቲያን ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ከመገለጡና የዘላለም መንግስቱን ከመመስረቱ በፊት ሃሰተኛው ክርስቶስ (ሃሳዊው መሲህ) እንደሚገለጽና ብዙዎችን እንደሚያስት ሊረዳ ይችላል። ይህ ያለንበት ዘመን ሃሳዊው መሲህ ሊገለጽ እጅግ የተቃረበበት ጊዜ ነው። ለዚህ ነው ብዙ አስፈሪና ዘግናኝ ነገሮችን እየሰማንና እያየን ያለነው። በተያያዘው ዜና ላይ እንደምናየው፣ ድሮ ልጆች ሆነን ወላጆቻችን ጭራቅ እያሉ ሲነግሩን የነበሩት አስደንጋጭና አስፈሪ ነገሮች ሁሉ ዛሬ ፋሽን ተብለው በአደባባይ፣ ለዚያውም በለንደን ከተማ በሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ ሲቀርቡ ማየት የማይጠበቅ ቢሆንም፣ ዓለማችን ወደ ምን ዓይነት መንፈሳዊ ዝቅጠትና ጨለማና ውስጥ እየገባች እንዳለ ያስረዳል። አባቶቻችን ነቢያትና ሐዋርያት ወዮ እያሉ የተነበዩት ዘመን ውስጥ መሆናችንን የሚያመለክተው ከዚህ መልእክት ጋር የተያያዘው ዜና ብቻ አይደለም። ጦርነትና የጦርነት ወሬ፣ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ ማእበል፣ የምድር መናወጥ፣ ህዝብ በህዝብ ላይ፣ መንግስትም በመንግስት ላይ መነሳታቸው የየዕለት ዜና ከሆነ ውሎ አድሮአል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል እንደተናገረው ይህ ጊዜ የንስሐ ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ከክፉ መንገዳችን ሁሉ ልንመለስና የወንጌሉን መልእክት ተቀብለን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መዳናችንን የምናረጋግጥበት ጊዜ ነው። እግዚአብሔር ወልድ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ "እኔ መንገድና እውነት ሕይትም ነኝ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።" ዮሐንስ 14፡7 ብሎ ተናግሮአል። ሐዋርያቱም "መዳንም በሌላ በማንም የለም፣ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና" የሐዋርያት ሥራ 4፡12 ብለው ነግረውናል። ሁሉ ነገር እንዳለ ይቀጥላል በማለት ተዘናግተን እንደ ኖህ ዘመን ሰዎች ስንበላና ስንጠጣ ከዘለዓለማዊው የነፍሳችን ነገር ተዘናግተን የጌታ ቀን በድንገት እንዳይደርስብን እንንቃ። እንደዚህ ዜና፣ በዓለም ላይ የሚሆነው ክፉ ነገር ሁሉ ሊያነቃን እንጂ ሊያስደነግጠን አይገባም። በእርግጥ የሚያስፈራውና የሚያስደነግጠው ግን ንስሃ ገብተን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ታርቀን ሳንዘጋጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊፈርድ ተመልሶ የመጣብን እንደ ሆነ ነው። እግዚአብሔር ዘመኑን የምንለይበትና እርሱን በንስሃ በመፈለግ ወደ እርሱ የምንመለስበትን ልብ ይስጠን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
የመለከት ድምጽ ብሎግ የአማርኛን ቋንቋ በተቀዳሚነት ለሚጠቀሙ ሰዎች በሙሉ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የወንጌል የምስራች ለማድረስ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ክርስቲያኖች ደግሞ መሰረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ለማስተማር ያገለግላል።
ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 3 እውነት መሆኑን የሚያሳይ የቴክኖሎጂ ግኝት
ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 3 እውነት መሆኑን የሚያሳይ የቴክኖሎጂ ግኝት
http://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-4898576/Scientists-transfer-light-sound-waves-world-first.html
http://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-4898576/Scientists-transfer-light-sound-waves-world-first.html
የእግዚአብሔርን ታላቅነት፣ ኃይል፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ ክብርና ግርማ ከሚያሳዩን ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው እርሱ ሁሉን
ነገር መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉን ነገር የፈጠረው በአፉ ቃል መሆኑ ነው። ቃልን በመናገር ብቻ ያልነበረውን ነገር ወደ መኖር የሚያመጣ
ከእርሱ ሌላ ማንም የለም። በዘፍጥረት 1፡2 ላይ እንደምናየው ጌታ አምላክ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ ምድር ባዶ እንደነበረችና፣
ጨለማም በጥልቁ ላይ እንደነበረ ተጽፎአል። ቁጥር 3 ላይ ስንደርስ ደግሞ ጌታ አምላክ ቃልን ብቻ በመናገር ብርሃንን እንደፈጠረ
እናያለን። ይህ ብርሃን እኛ የሰው ልጆችና ፍጡራን ሁሉ ልናየውና ልንጠቀምበት የምንችለው ብርሃን ነው። ይህ ብርሃን የተፈጠረው
በመጀመሪያው ቀን ሲሆን፣ የተፈጠረውም ከጌታ አምላክ አፍ በወጣው ቃል ኃይል ብቻ ነው። ጸሃይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ደግሞ የተፈጠሩት
በአራተኛው ቀን ነው። ስለዚህ የጌታ የአምላካችን ቃል ነው ብርሃንን የፈጠረው።
ብርሃን እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም፣ እስከ ዛሬ ድረስ የሰው ልጅ የሰራው ቴክኖሎጂ ግን ብርሃንን ገርቶ በሚገባ ሥራ ላይ ማዋል
ያልቻለበት ዋነኛ ምክንያት ብርሃን እጅግ ፈጣን መሆኑ ነው። ብርሃን በአንድ ሰከንድ ውስጥ ከ 299,792 ኪሎሜትር በላይ ይሄዳል። ማለትም
በአንድ ሰከንድ ውስጥ ብርሃን ምድርን ከሰባት ጊዜ በላይ ይዞራታል ማለት ነው። ታዲያ የሰው ልጅ ዛሬ የሚጠቀምባቸው እጅግ ፈጣን
የሚባሉ ኮምፒውተሮች እንኳን ይህን ፍጥነት መድረስ ስለማይችሉ ብርሃንን ለመረጃ መሰብሰቢያ፣ ማጠራቀሚያ፣ ለስሌትና ለማሰራጫ ሊጠቀሙበት
አልቻሉም። የዛሬዎቹ ኮምፒውተሮች የተሰሩባቸው ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች እጅግ ብዙ ኃይል የሚፈጁ፣ ከፍተኛ ሙቀት የሚያወጡና በማግኔታዊና
የኤሌክትሮን ሞገድም በቀላሉ ሊታወኩ የሚችሉ በመሆናቸው አስተማማኝነታቸው ብዙ ጥያቄ አለበት።
ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ዜና ላይ እንደምናነበው፣ በአውስትራሊያ የሚገኘው የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ
ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ብርሃንን ወደ ድምጽ ለመለወጥ የሚያስችል መሳሪያ ሰርተዋል። ይህ መሳሪያ ብርሃንን ወደ ድምጽ ለአጭር
ጊዜ ለውጦ ለማዘግየት መቻሉ ተዘግቦአል። የድምጽ ፍጥነት በሰከንድ 331 ሜትር ነው። ይህ ደግሞ የብርሃንን ፍጥነት 1/1000
ኛ ያህል ስለሆነ፣ አዲሱ ግኝት በሚገባ በስራ ላይ ሲውል የሰው ልጅ የብርሃንን ፍጥነት በመጠቀም አስተማማኝ ያልሆኑትን የዛሬዎቹን
የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች ፎቶን በሚባሉት ትንንሽ አካላት በሚሰሩ መሳሪያዎች ሊለውጣቸው ይችላል የሚል ትልቅ ተስፋን ፈጥሮአል።
የዛሬው መልእክቴ ትኩረት ኤሌክትሮኒክስ፣ ፎቶንስ ወይም አዲሱ
የቴክኖሎጂ እርምጃ አይደለም። የሰው ልጅ በምርምሩ ብርሃንን ዝግ አድርጎ ወደ ድምጽ በመቀየር ብርሃን መረጃን እንዲሸከምና ስራን
እንዲሰራ ማድረጉ ለሁለት ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ይመሰክራል። 1ኛ) እግዚአብሔር ቃልን በመናገር ብቻ ብርሃንንና ዓለምን
በሙሉ መፍጠሩ (ድምጽን ወደ ብርሃን፣ ቁስ አካላትና ሌሎችም የኃይል መልኮች መለወጡ) እውን መሆኑን፣ 2ኛ) መጽሐፍ ቅዱስ የማይሳሳትና እንከን የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን።
የእግዚአብሔር ቃል፣ ድምጽ፣ ብርሃንን ስለ ፈጠረው ነው የሰው ልጅ ብርሃንን ወደ ድምጽ በመለወጥ ዝግ ሊያደርገው የቻለው። ስለዚህ
በአንድ መልኩ የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያደረጉት የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ኋላ ገልብጠው መቅዳት ነው ማለት ይቻላል። በኃጢዓት
መታለልና በዲያብሎስ ሽንገላ መንፈሱ የታወረው የሰው ዘር እንደሚገባ አላስተዋለውም እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል
በመሆኑ ገና የሰው ዘር መርምሮ ያልደረሰባቸውንና ሊደርስባቸው የማይችሉ ታላላቅ ምስጢሮችን ያዘለ ነው።
በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ላይ “እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ” ተብሎ የተጻፈው ቃል እውነት ከሆነ ሌላውም የመጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ እውነት ነው ማለት ነው። እነዚያ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደግሞ
እኛ የሰው ልጆች በበደላችንና በኃጢዓታችን ፈጽመን እንደ ጠፋንና በራሳችንም ጥረት ከዘለዓለም ሞት ልንድን እንደማንችል በግልጽ
ይነግረናል። (ገላትያ 2፡16) ነገር ግን እግዚአብሔር ለእኛ ካለው
ታላቅ ፍቅሩ የተነሳ፣ አንድ ልጁን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመላክ፣ እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቃይቶ በመሞቱና በመነሳቱ በደሙ የገዛልንን
ጽድቅ አምነን እና ተቀብለን የዘለዓለምን ሕይወት እንድናገኝ የምስራቹ ወንጌል ይነግረናል። ይህ ያለንበት በዓመጽ የተሞላ ዓለም
ደግሞ ከክፋት ወደ ክፋት እየባሰ በመሄዱና በዚህም መንገድ ለዘላለም መቀጠል ስለማይችል ጌታ አምላክ በዘመኑ መጨረሻ ልጁ ኢየሱስ
ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ እንደሚመጣ፣ በሕያዋንና በሙታን ላይ እንደሚፈርድና የዘለዓለም መንግስቱን እንደሚመሰርት ብሉይም ሆኑ አዲስ
ኪዳን ያስተምሩናል። በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 22 ቁጥር 12 እና 13 ላይ እንዲህ ተጽፎአል፡ “እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፣ ለእያንዳንዱም
እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ፣ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ኦሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።” ልንሰራው የሚገባ ዋነኛው ስራ ሊያድነን የመጣውን የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ
ክርስቶስን በመቀበል ማመን ነው። “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሰራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስም መልሶ፣ ይህ የእግዚአብሔር
ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው። “ ዮሐንስ 6፡28-29 ስለዚህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውና
እኛንም ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚወስደን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማመን ነውና፣ ይህን ታላቅ ሥራ ዛሬ ነገ ሳንል እንፈጽም።
በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፣ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ዮሐንስ 3፡18
ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
ምድራችን በብዙ ጥፋት እየተመታች ነው፣ የታላቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ፍራንክሊን ግራሃም ዓለም ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መዘጋጀት አለበት አሉ።
የታላቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ዓለም ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት መዘጋጀት አለበት አሉ።
እንኳን እግዚአብሔር ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። አዲስ ዓመት ሲመጣ ሁላችንም አዲስ ነገርን ተስፋ እናደርጋለን።
በምእራቡ ዓለም ያሉ ሰዎች አዲስ ዓመታቸው ሲገባ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን በማለት ከራሳቸው ቃል ኪዳን ይገባሉ። ክርስቲያኖች
የሆንን ሁሉ በአዲሱ ዓመት በበለጠ ወደ እግዚአብሔር ለመጠጋት፣ እርሱን በበለጠ ለማወቅና ለመታዘዝ ብንሻ ያንን መሻት እግዚአብሔር
ይሰጠናል ብዬ አምናለሁ። “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት፣ ጽድቁንም ፈልጉ፣ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” ማቴዎስ
6፡33 ተብሎ ተጽፎአልና። በዚህ በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር ይህንን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር እንድንፈልግ እግዚአብሔር ይርዳን።
በግል ሕይወታችንም ሆነ በአካባቢያችን፣ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ሁሉ በአዲሱ ዓመት የምንሰማው ዜና በሙሉ መልካም ቢሆን
ምንኛ ደስ ይል ነበር? ለጊዜው ግን እውነታው እንዲህ አይደለም። ዳግም በመምጣቱ ሁሉን ነገር አዲስ የሚያደርገው ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በክብር እስኪገለጽ ድረስ መልካምና ክፉ ዜና እየተደባለቀ መስማታችን የግድ ነው። በተለይም ደግሞ የጌታችን ዳግም ምጽዓት
ቀን እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ዘመን ምድራችን በብዙ ትግልና ጣር ውስጥ መሆኗን ለማየት ሩቅ መሄድ አያስፈልገንም። በደቡብ ሱዳን
ሲነጉድ የከረመው ጦርነት፣ በሶማሊያ ላለፉት 26 ዓመታት ሶማሊያን ያፈራረሳት የእርስ በርስ ጦርነት፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ብዙ
ህዝብ የፈጀውና አገሪቱን ያወደመው የየመን ጦርነት፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአገራቸው ያፈናቀለው የሶሪያ ጦርነት፣ እኤአ
ከ2003 የጀመረውና እስከ ዛሬ ድረስ አገሪቱን እያፈራረሰ ያለው የኢራቅ ጦርነት፣ ላለፉት 16 ዓመታት ሳያቆም በአፍጋኒስታን የሚካሄደው
ጦርነት ወዘተ ጦርነትን በተመለከተ ልንጠቅሳቸው ከምንችላቸው ጥቂቶቹ ናቸው።
ይህ የሚያውከን ከሆነ ደግሞ ከዚህ የበለጠና ዓለም እስከ ዛሬ ድረስ ያላየችውን ጥፋት ሊያመጡ የሚችሉ መፋጠጦች በኤኮኖሚና
በወታደራዊ ኃይላቸው ታላላቅ በሚባሉት አገሮች መካከልም በየጊዜው እየተካረሩ እየሄዱ ናቸው በማለት ብዙ ታዛቢዎች ያስጠነቅቃሉ።
ታላቂቷ አገር አሜሪካ ከሩሲያ፣ ከቻይና፣ ከሰሜን ኮሪያና ከኢራን ጋር የገባችባቸው እሰጥ አገባዎች ወደ ሰላም የሚያመሩ አይመስሉም።
ምድር ፍጹም ሰላም ያገኘችበት ጊዜ አልነበረም የሚሉ የታሪክ ባለሙያዎች እንኳን፣ ዛሬ ዓለማችን ያለችበት ውጥረት ግን ከመቼውም
ጊዜ ይልቅ እጅግ ውስብስብና ከባድ መሆኑን አይክዱም።
ዘማሪው ወንድማችን ደረጃ ከበደ “ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ፣ የሚሆነው በምድር ዙሪያ፣ እየከፋ ሲሄድ ጊዜው መሸሸጊያ ኢየሱስ
ነው” የሚለውን መዝሙር ከዘመረ ከአርባ ዓመት በላይ ሆኗል። የዚያ መዝሙር እውነተኛ መልእክት ግን ከዚያን ጊዜ ይልቅ ዛሬ እውን
እየሆነ ነው ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም። ሆን ብለን አናይም፣ አንሰማም ካላልን፣ ወይም ደግሞ ብዙ ክፉ ዜናዎችን ከመስማታችን
የተነሳ ልባችን ካልደነደነ በስተቀር በዓለም ሁሉ ዙሪያ ጎልቶ የሚታየውና የሚሰማው ዜና መልካም አይደለም። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘው
ድረ ገጽ ላይ እንደምታነቡት ባለፉት ሁለት ሳምንታት እንኳን የተከሰቱትና ከባድ የህዝብ እልቂትና የንብረት ውድመት ያስከተሉትን
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ብቻ እንኳን ስንመለከት ምድራችን ወደሚያስፈራ ሁኔታ ውስጥ እንደገባች እንረዳለን። የሚቀርበው የጥፋት
ዜና ሁሉ ሆን ብሎ ከትንቢተ ኤርምያስ ምእራፍ 50 እና 51፣ ከትንቢተ ዳንኤል፣ ከትንቢተ ኢዩኤል ምእራፍ 2፣ ከማቴዎስ ምእራፍ
24፣ ማርቆስ 13፣ ሉቃስ 21 እና ከዮሐንስ ራዕይ መልእክቶች ላይ ተወስዶ የተጻፈ ይመስላል። በእርግጥ ዛሬ የምናያቸው ነገሮች
ከጌታ ዳግም ምጽዓት በፊት በሚከሰተው የታላቁ የመከራ ዘመን ውስጥ ከሚፈጸሙት እጅግ አስፈሪ ነገሮች ጋር ሊወዳደር ባይችልም፣ በብዙ
ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ግን በከፍተኛ አደጋና ችግር ውስጥ በየእለቱ እየገቡ ናቸው። ምናልባት እኛ ባለንባቸው ስፍራዎች ሰላም
ከሆነ እግዚአብሔር ያን እድል የሰጠን ለሌሎቹ እንድንጸልይ መሆኑን አንዘንጋ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ
እንዲሁም ሌሎች የምድር አካባቢዎች ከተከሰቱት ከፍተኛ ጥፋቶች መካከል የሚከተሉትን ብቻ መጥቀስ ይበቃል፡




















((

((

((

((

ባለፉት 12 ዓመታት ያልሆነና ከፍተኛ የሆነ ከጸሃይ
የተወረወረ ጨረር ምድርን በመምታቱ በብዙ የዓለም ስፍራዎች የሬድዮ ሞገድን አቋርጧል፣ አቃውሷል።ከፍተኛነቱ X10 C.M.E ነው የሚባለው ይህ ሞገድ በምድር መንቀጥቀጥና በአየር ንብረት ላይም ከፍተኛ ተጽእኖ
ማድረጉ ተዘግቧል።
እነዚህ ዜናዎች መልካም ወይም የሚያበረታቱ አይደሉም። ነገር
ግን ሕይወቱን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰጠ ክርትሲያን እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአጋጣሚ የሚሆኑና ተስፋ የሚያስቆርጡ አይደሉም።
ጌታ ከመመለሱ በፊት በምድር ላይ የግድ ሊሆኑ አላቸው። እነዚህን ሁሉና ሌሎችንም በዚህ መልእክት ያልተጠቀሱ ሁኔታዎችን በማገናዘብ
ነው የታላቁ ወንጌላዊ የዶ/ር ቢሊ ግራሃም ልጅ የሆኑት ፍራንክሊን ግራሃም ዓለም ሁሉ ለክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ሊዘጋጅ
ይገባዋል ያሉት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲገለጽና በጽድቅ ሲነግስ ምድር ሁሉ በሰላም ታድራለች። ክርስቲያን የሆነ
ሁሉ ያንን ቀን በናፍቆት ይጠብቃል። ተግተን በመጸለይና የምስራቹን ወንጌል ላልሰሙት በማድረስ መቅረዛችንን በዘይት ሞልተን ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠብቀው። በሁለንተናችን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጽ ዝግጁ እንድንሆን ጌታ አምላክ ጸጋውን ሁሉ ያብዛልን።
ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
የሰው ልጅ በተወሰነች እውቀቱ የእግዚአብሔርን ስራ እያመሳቀለ ብዙዎችን እያጠፋ ነው።
ከሶስት ቀናት በፊት ሃብታሞቹና ታላላቆቹ የምድር መንግስታት የምድርን አየር በሰው
ሰራሽ ቴክኖሎጂ በመቀየር ድርቅን፣ ጎርፍን፣ ማእበልንና ሌሎችም ምድርን የሚያጠፉ የአየር ንብረት ቀውሶችን ማምጣታቸው ወደ አደባባይ
ከወጣ ውሎ ማደሩን የሚያሳዩ መረጃዎችን አካፍዬ ነበር። ከዚህ መልእክት ጋር አያይዤ የላክሁት የ ዩ-ቲዩብ ማገናኛ፣ በ70ዎቹ አሜሪካ በቬትናም ባደረገችው ጦርነት የጦር ኃይሏ የአካባቢውን የአየር
ንብረት በመቀየስ ከፍተኛ ዝናብ፣ ጎርፍና ጥፋትን ታመጣ እንደነበር የሚያስረዱ ዘገባዎችን ይዟል። ተጨማሪ መረጃን የሚፈልግ ሰው
ደግሞ “Operation popeye” ብሎ በመፈለግ የአሜሪካ የጦር ኃይልና
የጦር መሳሪያ አምራቾች እንዲሁም ተኮናታሪዎች የአየር ንብረትን ምህንድስናን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀማቸው የአደባባይ ምስጢር መሆኑን
ማየት ይችላል። ይህን ማገናኛ በመጠቀም ቪዲዮውን ተመልከቱት፡ https://www.youtube.com/watch?v=Cpr5JVWjIW4
በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በመካከለኛው አሜሪካ በሚገኙ ደሴቶችና በደቡባዊና
ደቡባዊ ምስራቅ አሜሪካ ከፍተኛ ጥፋትን እያመጣች ያለችው ሃሪኬን ኢርማ ከ 600 ሺህ በላይ ሰዎች ከፍሎሪዳ ግዛት እንዲሰደዱ ባደረገችበት
በዚህ ወቅት፣ ይህች ታላቅ ሞገድም ሆነ ከእርስዋ በፊት ብዙ የቴክሳስን ግዛቶች ያጠፋው ሃሪኬን ሃርቪ፣ የአየር ንብረት ጦርነትን
በሚያካሂዱ ክፍሎች የተቀነባበሩ እንደሆኑ ብዙዎች እየዘገቡ ነው። ዋሽንግተን ፖስት የሚባለው ጋዜጣ እንኳን ሳይቀር፣ ይህች ሞገድ፣
ሃሪኬን ኢርማ፣ “በGPS ትመራ ይመስል በካሪቢያኑ ባህር ብዙ ደሴቶችን ካጠፋች በኋላ አሁን ደግሞ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትል
ቀጭን በሆነውን የፍሎሪዳ የመጥበሻ መያዣ መሰል መሬት ላይ ወደ አሜሪካ እየገባች መሆኗን ታዝቦ ዘግቦአል።
ሃሪኬን ኢርማ ከምታመጣው ጥፋት ሁሉ እጅግ እየተፈራ ያለው ደግሞ በዚያው በፍሎሪዳ
ግዛት የሚገኙ ሁለት የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎችን በመምታት የኑክሊየር ጥፋት ትፈጥር ይሆን የሚለው ሥጋት ነው። ሌሎች ደግሞ ከዚህም
አልፈው ይህች ሞገድ ከነዚህም አልፋ በአካባቢው ያሉ እስከ አስራ ሁለት የሚደርሱ የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎችንም ትጎዳ ይሆናል
ይላሉ። ሃሪኬን ኢርማ እያጣች ካለችው ጥፋት ሰው ገና ሸሽቶ ሳይጨርስ
ሌሎች ሁለት ሞገዶችም ከበስተኋላዋ እያደጉ እንደሆነ ተዘግቧል። ሁኔታውን ቀረብ ብለው የሚያጠኑ ባለሙያዎች ደግሞ የሁለቱ ትልልቅ
ሞገዶች ስም ራሱ የሚያስገርምና ምናልባት፣ በአጋጣሚ የተሰጠ ላይሆን ይችላል ይላሉ። ከሁለት ሳምንት በፊት ቴክሳስን ያጠፋው HARVEY
የሚለው ስም መሰረቱ ከፈረንሳይ ሲሆኑ ትርጉሙ “ተዋጊ” ወይም “ለጦርነት ዝግጁ፣ ብቁ የሆነ” ማለት ነው። አሁን ጥፋት እየሰራች
ያለችው ሞገድ IRMA ስም ደግሞ መሰረቱ ጀርመንኛ፣ ትርጉሙም “በሙሉ፣ ጠቅላላ፣ ዓለም አቀፍ” ማለት ነው። ከሃርቪም ይልቅ ከፍተኛ
ጥፋት ልታስከትል ስለምትችል ይህችን ሞገድ ብዙ አዋቂዎችና የመንግስት ባለስልጣናትም ሳይቀር “የኑክሊየር ሞገድ” በማለት ሰይመዋታል።
የሰው ያገኘውን እውቀትና ቴክኖሎጂ በመጠቀም በሌሎች ላይ ጥፋትን ለማምጣት፣ ደካሞችን
በማስፈራራትና በጉልበት ለመግዛት ሲሞክር ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ጌታ አምላክ በኖህ ዘመን የነበረውን ዘመንም በውሃ ያጠፋው
እንዲህ እንደ ዛሬው በምድር ላይ ዓመጽ ስለ በዛ ነበር። በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 17 እና 18 የተጠቀሰችው፣ በተለይም ደግሞ በምዕራፍ
18 ላይ የተገለጸችው፣ ምድርን ሁሉ እንደፈለጋት እየረጋገጠች ትገዛ የነበረችውና በኋላም ከጥልቁ የሚወጣው አውሬና ተከታዮቹ የሚያጠፉአት
ታላቂቲ ባቢሎን የዛሬዋ አሜሪካ ትሆን?!
በዚህ ሁሉ መካከል የሰው ነፍስ ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ግን በዙፋኑ አለ።
በእርሱ የሚታመኑ ሁሉ በማይናወጠው ዓለት በክርስቶስ ላይ የተመሰረቱ ስለሆኑ በምድር ላይ እየነፈሰ ያለው የዓመጽና የጥፋት ማእበል
አያጠፋቸውም። ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ጌታ አምላክ ግን በጎቹን ለመጠበቅ አይተኛም፣ አያንቀላፋም፣ አይደክምም አይታክትም። ሁሉንም
በጊዜው በክርስቶስ ውብ አድርጎ እንደገና ይሰራዋል። የጌታ ሰላምና ጸጋ ይብዛላችሁ። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
አሜሪካን እያጠፉ ያሉት ታላላቅ ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው ተባለ "ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ" ራዕይ 11፡18
አሜሪካን እያጠፉ ያሉት ታላላቅ ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው ተባለ
የሰሞኑ ታላላቅ የባህር ሞገዶች ሰው ሰራሽ ናቸው እየተባለ ነው
“ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ”። ይህ ቃል የሚገኘው በዮሐንስ ራዕይ ምእራፍ 11 ቁጥር 18 ላይ ነው።
ከቁጥር 15-19 ያለውን ማንበብ ሙሉ ሃሳቡን ይሰጣል። በዚህ መጽሃፍ ውስጥ
ሰባት ማህተሞች ይፈታሉ፣ ሰባት መለከቶች ይነፋሉ፣ ሰባት ጽዋዎችም በምድርና በሰማይ ላይ ይፈስሳሉ። ሰባተኛው ማህተም ሲፈታ እግዚአብሔር
ለዚህ ዓለም ፍጻሜ ያዘጋጀው ምስጢር ይፈጸማል፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ይነግሳል። ያ ሲሆን ደግሞ የእግዚአብሔር
ቅዱሳን ወደ መንግስቱ ዓመጸኞችም ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘለዓለም ጨለማ ይሄዳሉ። ዛሬ ይህን መልእክት እንድጽፍ
ያስገደደኝ ነገር፣ “ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” የሚለውን ቃል ዛሬ በምድር ላይ እየተካሄደ ካለው ነገር ጋር
በጥሞና ሳስተውለው የሰው ልጆች ምን ያህል ጉልበትና እውቀት ቢኖራቸው ነው ምድርን እስከ ማጥፋት ድረስ የደረሱት የሚል ጥያቄ መሙላቱ
ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ ምድርን እያወከ ስለሆነ ሃብታሞቹም ሆኑ ድሆቹ አገሮች ብዙ ስምምነቶችን ሲያደርጉ ከርመዋል። የኪዮቶ
ፕሮቶኮል፣ በቅርቡ ደግሞ የፓሪስ ስምምነት። በመገናኛ ብዙኃን፣ በትምህርት ቤት፣ በየዩኒቨርሲቲዎቹና በመዋእለ ህጻናትም እንኳን
ሳይቀር እኛ የሰው ልጆች የምናደርገው ግድ የለሽ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ምድርን እያጠፋ ስለሆነ እንድንጠነቀቅ ነው። ስለዚህም
ሁላችንም የምንችለውን በማድረግ ይችን እግዚአብሔር የሰጠንን ምድር ለመንከባከብ ጥረት እናደርጋለን ይህንንም መቀጠል ያስፈልገናል።
ነገር ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የአደባባይ ምስጢር እየሆነ የመጣ ነገር አለ። ባለፉት ከአንድ መቶ በሚበልጡ ዓመታት የሰው
ልጅ፣ በተለይም ደግሞ ሃብታምና ኃያል የሆኑት እንደ አሜሪካና ሩሲያ ያሉ አገሮች የአየር ንብረት ምህንድስና ሳይንስን በከፍተኛ
ፍጥነት በማሳደግ የምድርን አየር ንብረት በሚፈልጓቸው ቦታዎች ላይ ለመቀየር የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደ ገነቡና ይህንንም ሲፈትሹ
እንደኖሩ እጅብ ብዙ ማስረጃዎች ወደ አደባባይ ወጥተዋል። እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ደመና እንዲፈጠር፣ የተፈጠረ ትንሽ ደመና
እንዲሰባሰብ፣ እንዲበዛና ወደሚፈለገው አቅጣጫ እንዲሄድ ለመግራት፣ ትልልቅ ሞገዶች (storms and hurricanes) እንዲፈጠሩ፣ የተፈጠሩት እንዲዳከሙ ወይም እንዲጠናከሩና
ወደተፈለገበት አካባቢ እንዲሄዱ፣ በአንድ ስፍራ ድርቅ በሌላው ቦታ ደግሞ ከፍተኛ ጎርፍ እንዲፈጠር በማድረግ ብዙ ህዝቦችን የሚጨርሱ
እኩይ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ በግልጽ እየተዘገበ ነው። ይህን ስራ የሚሰሩት ደግሞ የአሜሪካ መንግስት ወታደራዊና ሲቪል መስሪያ
ቤቶች፣ የጦር መሳሪያ አምራቾች፣ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ባለቤቶችና ተኮናታሪዎች እንደሆኑ ብዙ መረጃዎች ያመለክታሉ። እነዚህ ሰው
ሰራሽ በአካባቢና በዓለም የአየር ንብረት ላይ ቀውስ የሚፈጥሩ ምርምሮች፣ ሙከራዎችና ስራዎች እንደሚፈጸሙ ደግሞ ሁለቱም የአሜሪካ
ምክር ቤቶች በግልጽ ያውቃሉ፣ ሪፖርቶችም ይቀርቡላቸዋል። እንዲያውም ምክር ቤቶቹና ብዙ የመንግስት ቢሮዎችም ለዚሁ ስራ የሚያስፈልገውን
በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር በጀት ይመድባሉ። የአየር ንብረትን ለመቀየር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች አሉ ወይ ብሎ የሚጠራጠር ካለ ደግሞ የአሜሪካን መንግስት የአእምሮ ውጤት
ባለቤትነት (patent) መመዝገቢያ ቢሮ እጅግ ብዙ
ለሆኑ ለእነዚህ ቴክኖሎጂዎች በየጊዜው ያደረገውን ምዝገባ ማየት ይበቃል። ይህንን መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ድረ ገጽ እንድትጎበኙ
በትህትና እጋብዛችኋለሁ። http://www.geoengineeringwatch.org/
ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ዜናና ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱት፣ ባለፈው በኦገስት ወር መጨረሻ ላይ በደቡባዊ አሜሪካ
የቴክሳስ ግዛት ላይ፣ በተለይም በሂዩስተን ከተማ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰው ከፍተኛ ሞገድ (hurricane Harvey) ከላይ በተጠቀሱት ቴክኖሎጂዎች ተቀነባብሮአል ተብሎ በከፍተኛ
ደረጃ ይጠረጠራል። በዚያ ሞገድ የተጎዱ ህዝቦች ገና በቂ እርዳታ እንኳን አግኝተው ሳያበቁ አሁን ደግሞ ሌላ hurricane Irma የሚባልና ከሁለት ሳምንት በፊት ከተከሰተው እጅግ የሚከፋ ሞገድ በመምጣቱ
በደቡባዊውና በምስራቃዊው አሜሪካ የሚገኙ ብዙ ክፍለ ሃገሮች በተጠንቀቅ ላይ ሲቆሙ፣ ብዙ ሰዎችም የሚመጣውን ጥፋት ፍራቻ ከቤታቸው
እየተሰደዱ ይገኛሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴት የአሜሪካ የራሷ መንግስት ወታደራዊና ሲቢል ድርጅቶች፣ የጦር መሳሪያ አምራቾችና
ተኮናታሪዎች እንዴት በራሷ በአሜሪካ ግዛት ላይ ጥፋት የሚፈጥር ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለው ጥያቄ ለእኔም ሆነ ለብዙዎች ለማመን
የሚያዳግት ነው። ቀረብ ብለው በአሜሪካ ውስጥ ዛሬ ያለውን ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ለሚያጠኑ፣ ይች ታላቅ አገር በዓለም ዙሪያ
የሚቃወሟትን መንግስታት በመገለባበጥና አገሮችን በማፈራረስ የምታደርገውን ለሚከታተሉ ታዛቢዎችና በአየር ንብረት ምህንድስና ላይ
ከፍተኛ እውቀት ላላቸው ለራሷ ለአሜሪካ ባለሙያዎች ግን ይህ እንግዳ ነገር ወይም የማይታመን አይደለም። አሜሪካ ያላትን ከፍተኛ የሳይንስና ወታደራዊና እውቀትና ቲክኖሎጂ በመጠቀም
አየሩን እደሚፈልጉት በመለዋወጥ የራሷን የአገሪቱን ህዝብ በሚጎዳ መንገድ ይሰራሉ ተብለው በሰፊው የሚታሙት “ጥልቅ መንግስት” (deep state) የሚባለው ከተመረጡ የመንግስት ባለሥልጣናት በስተጀርባ የሚሰራው መዋቅር
መሆኑንም ብዙዎች ይዘግባሉ።
በአሜሪካ ብቻ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የአየር ንብረትን ሊቀይሩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች የአእምሮ ባለቤትነት ሰርቲፊኬት ቁጥሮች
በአሜሪካ መንግስት የpatent ቢሮ ድረ ገጽ ላይ ማየት ይቻላል። በየጊዜው አየር ንብረትን ለመቀየር በሰማይ ላይ ስለሚረጩት ኪሚካሎችም (chemtrail) እጅብ ብዙ ማስረጃዎች በአደባባይ ይገኛሉ። የአሜሪካ ምክር ቤቶች
ባለፉት ሰባ (70) ዓመታት የአየር ንብረትን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ እንደተፈለገው ስለመለወጥ ስለሚያስችሉ ስራዎች፣ ቴክኖሎጂዎች፣
ፕሮጀክቶች ብዙ ውይይቶችን አካሂደዋል፣ ሪፖርቶች ቀርበውላቸዋል፣ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፣ ህጎችንም አውጥተዋል። ይህን ሁሉ አስመልክተው
ነው ብዙ አዋቂዎች ምድራችን ወደ ከፋ ጥፋት ውስጥ ከመግባቷ በፊት እያስጠነቀቁ ያሉት። ታዲያ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለሚያውቅ ይሆን በመጨረሻው ቀን እሱ ውብና
ድንቅ አድርጎ የሰራትን ምድርንና በላይዋ ላይ ያለውን ህይወት በግድየለሽነት፣ በስግብግብነትና በክፋት የሚያጠፉትን ሁሉ የሚፈርድባቸው?
ለዚህ ይሆን ሃዋርያው ዮሐንስም “ምድርን የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” የሚለውን የሃያ አራቱን ሽማግሌዎች ቃል የሰማው? ሲነገረን እንደኖረው የአየር ንብረት ቀውስ
ሁሉ የእግዚአብሔር ስራ እንዳልሆነ በዚህ የተጠቀሱትን መረጃዎችና የተያያዘውን ዜና በማንበብ የተሻለ መረዳትን ማግኘት ይቻላል። ዘመኑ እጅግ አስፈሪ ነው። እግዚአብሔር ግን የሚታመኑበትንና ተስፋ የሚያደርጉትን
በዚህ ሁሉ ውስጥ ይጠብቃል። ለምድር ሁሉ፣ በተለይም በአየር ንብረት ቀውስ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ ሁሉ እንጸልይ። ወንድማችሁ ዶ/ር
በፈቃዱ አድማሱ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፣ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡16
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፣ አስቀድሞም በእኛ
የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡16
በምእራቡ ዓለም የሚገኙ ብዙዎች ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ከሚያውቁት ይልቅ፣ ስለ
ፊልሞች፣ ዘፋኞች፣ ተዋናዮችና ታዋቂ የሚባሉ ሰዎች የሚያውቁት ይበልጣል። የብዙዎች የክርስትና እምነትም የሚወሰነው በሳምንት አንድ
ወይም ቢበዛ ሁለት ጊዜ በጸሎት ቤት ወይም በቴሌቪዝንና በሬድዮ በሚሰሙት ላይ ነው። የቴሌቪዥን፣ ሬድዮ፣ ሲኒማ ቤት፣ ኢንተርኔትና
ኮምፒውተር መምጣት ብዙ መልካም አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም፣ ብዙ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ቁጭ ብሎ ከማንበብና የወንጌልን እውነት
በቀጥታ ከመረዳት ይልቅ በነዚህ መገናኛ ብዙኃን የሚቀርቡትን ብቻ ቁጭ ብሎ በመመልከት መንፈሳዊ ህይወታቸውን የሚገነቡ ይመስላቸዋል።
በትክክለኛ መንገድ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስተምሩ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ገንቢ አገልግሎት አላቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ
ማንበብ የሚችል ክርስቲያን የሰማውን ሁሉ ከመቀበሉ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ እውነቱን መፈተንና መመርመር ያስፈልገዋል። አስተማሪና
የቤተክርስቲያን መሪ የሆነውን ጢሞቲዎስን እንኳን ሐዋርያው ጳውሎስ “እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ” ይለዋል። 1ኛ ጢሞቲ 4፡13 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የዘመኑን አዋቂ ነን ባዮች ሰዱቃውያንን
“መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል ስለማታውቁ ትስታላችሁ” አላቸው። ማቴዎስ 22፡29-33
ከዚህ መልእክት ጋር ከተያያዘው ሪፖርት እንደምትመለከቱት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት
መሪዎች ነን የሚሉ ብዙ የአሜሪካ የውሸት አስተማሪዎችና የውሸት መጋቢዎች በግልጽ የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃወም ትምህርትን እንደ
እውነት ለማስተማርና ተከታዮቻቸውም እንዲቀበሉት ለማድረግ ተስማምተው ውል ፈርመዋል። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ወንድና ሴት አድርጎ
ፈጠራቸው ተብሎ በግልጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሳለ፣ ሰው ወንድና ሴት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብዙ ጾታዎችም ሊኖሩት ይችላሉ፣ ሰው ሲፈልግ ወንድ ሲፈልግ ሴት፣ ሳይፈልግ ደግሞ ከሁለቱም የተለየ፣
ወይም ሁለቱንም ወይም ምንም ጾታ የለኝም ማለት ይችላል፣ ጋብቻ ደግሞ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ ሳይሆን ሰዎች
እንደ ፈለጉት ሊያደርጉት የሚችሉ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም መቀበል አለባት የሚል ትምህርትን የሚያጸድቅ ቃል ኪዳንን ተፈራርመዋል።
በዚሁ በፈረንጆቹ አመት የካናዳ መንግስትም አንድ ህጻን ሲወለድ ወንድ
ወይም ሴት ብቻ ሳይሆን ጾታው ያልተወሰነም ሊሆን ይችላል ብሎ፣ በትውልድ መረጃ እና በፓስፖርት ላይ እንኳን ወንድም ሴትም ያልሆነ
የሚባል ሶስተኛ ጾታን ፈጥሮአል። ከላይ የተጠቀሱት ሃሰተኛ አስተማሪዎች ደግሞ ከዚህም አልፈው ተርፈው የነርሱን የመርገም ፍልስፍናና
ትምህርት እንደ አዲስ የመንፈስ ቅዱስ መገለጽ በማቅረብ፣ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሩትን ክርስቲያን መሪዎችና
አስተማሪዎች ራእይ የሌላቸውና ኋላ ቀሮች ናቸው በማለት በግልጽ እያሳጡ ይገኛሉ።
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍቅር የቀመሱና የእግዚአብሔርን
ቃል ተረድተው ለጌታ በመታዘዝ ሕይወት የሚመላለሱ ክርስያኖች ሁሉ በዚህ ዜና ሊደነግጡ አይችሉም። ምክንያቱም ይህ የትንቢት ፍጻሜና
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓቱ ስለተቃረበ የግድ ሊሆን የሚገባው ነገር ነው። ነገር ግን ማንም የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ
ይጠንቀቅ። ዛሬ የሐሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ እንደ ድሮው በስውር ሳይሆን በግልጽ በምድር ላይ እየሰራ ነው። በ2ኛ ተሰሎንቄ ምዕራፍ
2 ላይ እንደ ተጻፈው መቼ ለይቶለት እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚቀመጥ ቀኑን ባናውቅም፣ የቤተ
ክርስቲያን መሪዎች ነን፣ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተን ነው እያሉ የእግዚአብሔርን ቃልና መሰረታዊ የተፈጥሮ ህግጋትን የሚጻረሩ ነገሮችን ክርስቲያኖች እንዲቀበሉ የሚያስተምሩ እነዚህ የሃሰተኛው
ክርስቶስ መንገድ ጠራጊዎች መሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም። ምክንያቱም ያ ዐመጸኛ የመገለጹ አንዱ ምልክት የእግዚአብሔርን ህግጋት
ለመለወጥ መሞከሩ ነው። ትንቢተ ዳንኤል 7፡25።
እንንቃ ! መጽሐፍ ቅዱሳችንን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስር ሆነን እናንብብ እና እናጥና።
ከእውነተኛ ክርስቲያኖችና የቤተ ክርስቲያን መሪዎቻችን ጋር ያለንን ህብረት እናጠንክር። የምንሰማውና የምናምነው ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ
እውነት ጋር የሚስማማ መሆኑን እናረጋግጥ። እምነትና በክርስቶስ ደም የታጠበ በጎ ህሊና ካለን ከቃሉ ቃር የሚጻረረውን የሃሰትና
የአጋንንት ትምህርት መለየት እንችላለን። ይህ ወቅት ግን የትእግስትና የጽናት ጊዜ ነው። በእውነተኛ ክርስቲያን ላይ ያለው ሰልፍና
ጦርነት ዛሬ የሚመጣው ከሩቅ ሳይሆን በተያያዘው ሪፖርት ላ እንደምታነቡት
ክርስቲያንና መሪዎች ነን ከሚሉ ነው። እግዚአብሔር ግን ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል። ከእግዚአብሔር በክርስቶስ ዳግም የተወለደም ሁሉ
መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ሆኖ ስለሚመሰክርለት የእግዚአብሔር መሆኑን ያውቃል። ከሁለት ሺህ ዓመታት ያህል በፊት ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ
ከተናገረ፣ እኛ ደግሞ የሚታየውን ሁሉ እያየንና እየሰማን በእርግጥም ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ መድረሱን
እናውቃለን።
ልባችን አይታወክ። ሌሊቱ ሊነጋ ሲል ጨለማው ይከብዳል እንዲሉ፣ በምድር ላይ ዓመጻው
ይክበድ እንጂ፣ የነገስታት ንጉስና የጌቶች ጌታ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድንገት ከተፍ ይላል። የዓለም መንግሥት ሥልጣንም
ሁሉ የእርሱ ሊሆን ቀኑ ቅርብ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በቅንነት
በሚወዱና በሚያመልኩት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ሰላም ይሁን። ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የምድርን አየር እያናጋ ነው፣ የምድር መንቀጥቀጥና እሳተ ገሞራም የማፈንዳት ጥፋቶች ይሰራሉ
በኖኅ ዘመን እንደነበረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ክዶ ራሱ አምላክ ለመሆን ሲቃጣው በራሱ እና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ትልቅ ጥፋትን እየፈጠረ ነው። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ ጌታ አምላክ የሰው ልጅ ሊ...
-
የኖኀ ዘመን ፥ ኔፊሊም እነማን ናቸው? ከየት መጡ? ምን አደረጉ? ፍጻሜያቸውስ? ትምሕርት 5 ዘፍጥረት ምዕራፍ 6 “በዚያን ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ...
-
የኖህ ዘመን እንደነበር የጌታ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፡ ኔፊሊም ከየት መጡ? ከሰው ሴቶች ልጆች የወለዷቸው እነዚያ “የእግዚአብሔር ልጆች” የተባሉት እነማን ናቸው? ትምሕርት 6 ባለፉት 5 ትምህርቶች ጌታ ኢየሱስ...
-
በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግም መወለድ ማለት ምን ማለት ነው? ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ፣ May 6, 2018 አንድ ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግም ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊ...