ከጠየቃቸው ከእነዚያ ጥያቄዎች አንዱ በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 12 ቁጥር 56 ላይ ይገኛል። ይህ ጥያቄ ከዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት በፊት ለነበሩትና ክርስቶስን ይሰሙ ለነበሩ ሰዎች እንዳስፈለገው ሁሉ በዚህ ዘመን ለምንኖር ለእኛም ያስፈልጋል። ይህ የእኛ ዘመንስ ምን ዓይነት ነው? ወዴት እያመራ ነው? ፍጻሜውስ ምን ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች ልንጠይቅና በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ለነዚህ ጥያቄዎች በቅድሚያ በነቢያት፣ በጌታ በራሱና በሐዋርያት በትንቢት የተሰጡትን መልሶች ልናጤን ይገባል። ዛሬ የወጣችው የመለከት ድምጽ 12 ቁጥር ይህን ጥያቄ በአጭሩ በማንሳት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት እጅግ እየተቃረበ መሆኑን ለማስረዳት ትሞክራለች። መልካም ምንባብ።
ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ