ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ዓለም ሁሉ የሚቀበለው ስህተር እየመጣ ነው። የሚመጣውን ስህተት መለየት እንችል ይሆን።
ባለፈው ወር
(JANUARY) በተከታታይ በጻፍኳቸው መልእክቶች ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓቱ ሲቃረብ የሚኖረው ሁኔታ የሆህን ዘመን እንደሚመስል መናገሩን፣ የኖህ ዘመን ምን ይመስል እንደነበረና የእኛ ዘመን ደግሞ ከሱ ጋር እንዴት
እንደሚያያዝ መፅሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ለመግለጽ በጥቂቱ ሞክሬያለሁ። ለበለጠ መረጃ የመለከት ድምጽ መጽሄትን አራተኛ እትም
እንድታነቡት እጋብዛችኋላሁ። እነዚያን መልእክቶች ካስታወሳችሁ፣ ከጥፋት ውኃ ቀደም ብሎ፣ ከዲያብሎስ ጋር አብረው ካመጹት የሰማይ
መላእክት አንዳንዶቹ የእግዚአብሔርን የፍጥረት ስርዓት በመጣስ ወደ ምድር ወርደው የሰውን ሴቶች ልጆች እንደወሰዱና ከነሱም ጋር
የተከለከለ ፍትወተ ስጋን በመፈጸም ኔፊሊም የተባሉ እጅግ ግዙፍ (ረዓይት) የሆኑ በባህርያቸውና በአካላቸው ከፊል የወደቁ መላእክትና
ከፊል ሰው የሆኑ ልጆችን እንደወለዱ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 6 እና ሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተገለጠውን ተመልክተናል።
እነዚያ የወደቁ መላእክት፣ ልጆቻቸው ኔፊሊም እና ዘሮቻቸው እንዲሁም ከነሱ ጋር የተባበሩት የኖህ ዘመን ሰዎችም ዓመጻቸው እጅግ
ስለበዛ ጌታ አምላክ ኖህን፣ ቤተሰቡን እና የተመረጡ እንስሳትን በኖህ መርከብ ካስገባ በኋላ የዘመኑን ዓለም በውኃ አጠፋ። የኔፊሊም
ታሪክ ግን በኖህ ዘመን አላበቃም። ዘፍጥረት 6 ቁጥር 4 ላይ እንደምናነበው ከወደቁት የሰማይ መላእክት አንዳንዶቹ ዘራቸውን ከሰው
ዘር ጋር በማደባለቅ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምጽ ያደረጉት በኖህ ዘመን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ ነበር። ጌታ አምላክ
በባቢሎን የሰዎችን ቋንቋ የደባለቀው እንደዚያው እንደኖህ ዘመን ሌሎች የወደቁ መላእክት እንደገና የሰውን ዘር በመበከላቸውና ከዚያም
ጋር ተያይዞ የሰው ዘር እግዚአብሔርን በማምለክና በስርዓቱም ከመሄድ ይልቅ የነዚያን የወደቁ መላእክትና የልጆቻቸውን የኔፊሊምን
ክፉ መንገድ ስለተከተለ ነበር። እግዚአብሔር ለእስራኤል ህዝብ የከነዓንን ምድር ሲያወርስም ዋናው ጦርነት በዚያ ከነበሩ የኔፊሊም፣
የራፋይም፣ የኤሚማውያን፣ ዘምዙማውያን እና ሌሎችም የረዓይት ዘሮች ጋር እንደነበር በብሉይ ኪዳን ተጽፎአል። የሰዶምና የገሞራ መጥፋትም
ከዚሁ ከኔፊሊምና ዘሮቻቸው ዓመጽ ጋር ግንኙነት አለው። ይህ ሁሉ ታሪክ ይመስላል። ነገር ግን ታሪኩ ዛሬም በእኛ ዘመን ያላቆመ
ነገር ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ መጥቶ የዘለዓለም መንግስቱን እስኪመሰርት ድረስም አያበቃም።
ልብ ብላችሁ ዜናዎችን እና
ታሪክን ካስተዋላችሁ በተለይ ከ1960ዎቹ ጀምሮ በሌላ ዓለማት የሚኖሩ ከእኛ ከሰው ልጆች የላቁ ሰው መስል ፍጥረታት ሳይኖሩ አይቀሩም
ተብሎ ብዙ ይናፈሳል። እነዚህ ALIENS፣ Extra-Terrestrial Intelligence፣ ET ወዘተ በሚባሉ ስሞች ስለሚጠሩት ነገሮች እና ስለ
UFO (የማይታወቁ በራሪ ነገሮች) እጅግ ብዙ ፊልሞች ተሰርተዋል፣ መጻህፍትም ተጽፈዋል ዛሬም እየተጻፉ ነው። STAR WARS የሚባለውን
ፊልም ማየት ብቻ ብዙ መረጃን ይሰጣል። ባለፉት ስድሳ የሚሆኑ ዓመታት የሰው ልጅ ወደጨረቃ ሄድን፣ ወደ ማርስ መንኮራኩር ላክን
እና ወዘተ የሚሉ የህዋ ምርምር ልእቀት ዜናዎችን ሲሰማ ቆይቷል። የአሜሪካው NASA እና የሩሲያው የህዋ ምርምር ማእከል ህዋን በተመለከት በመሪነት ቦታ ላይያሉ ናቸው። የሚገርመው ግን
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም የራሷ የህዋ ምርምር ማእከል አላት። ታዲያ እስከ ዛሬ ድረስ NASAም ሆነ ሌሎቹ መንግስታዊ የህዋ ምርምር
አካላት የማይታወቁ በራሪ ዲስኮችም ሆነ EXTRA TERRESTRIAL ALIENS አሉ ወይ፣ የሉም ወይ የሚለው ጥያቄ በአደባባይ ሲነሳ አናውቅም፣ መረጃ የለንም ከማለት በቀር አሉም የሉምም ብለው አያውቁም።
ሰማያት እስከ ሁለት መቶ ቢሊዮን በሚቆጠሩ ጋላክሲዎች የተሞሉ ናቸው ብለው የህዋ ምርምር ሊቃውንት ያስተምራሉ። ምድራችን የምትዞራት
ጸሃይ ደግሞ MILKYWAY በሚባለው ጋላክሲ ውስጥ የምትገኝ አንድ ኮከብ ነች። እነዚያ ወደ ሁለት መቶ ቢሊዮን የሚቆጠሩ ጋላክሲዎች
ደግሞ እያንዳንዳቸው እንደ ጸሃይ ያሉ ከመቶ ቢሊዮን በላይ ከዋክብትም እንዳሉአቸው ይገመታል።
ባለፉት ጥቂት አሰርት ዓመታት
ታዲያ NASA እና ሌሎችም የምርምር ድርጅቶች እንደምድራችን ያሉ ሌሎች ፕላኔቶች በሌሎች ከዋክብት ዙሪያም ሊኖሩ ይችላሉ ሲሉ ሰንብተዋል።
በየጊዜውም ይህን ወይም ያንን አገኘን ሲሉ ከርመዋል። ይህን የሚያደርጉትም በዚህ ፍጥረተ ዓለም ውስጥ ከሰው ሌላ እውቀት ያላቸው
ፍጥረታት ይኖሩ ይሆን ወይ? የሰው ልጅ ከዚህች ምድር ወጥቶ ሌላ ዓለም ላይ ሊኖር ይችላል ወይ የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎችን ለመመለስ
ነው። ታዲያ ልባችን ትልቅ ይሁን እንጂ ተራው ሰው እስካሁን ድረስ በዚህ በቅርቡ ወዳለችው ጨረቃም መሄድ አልቻለም። ከምድር ቀጥሎ
ወዳለችው ማርስም መሄድ ይቅርና ውሃ አላት ወይስ የላትም የሚለው ጥያቄ እንኳን መልስ አላገኘም። ይህ በዚህ እንዳለ ታዲያ ባያያዝኩት
ዜና ላይ እንደምታዩት NASA በFEBRUARY 22 2017 ባወጣው መግለጫ ላይ ከምድር 40 (አርባ) የብርሃን ዓመት ወይም
235 ትሪሊዮን (235,000,000,000,000) ማይል ወይም 380 ትሪሊዮን (380,000,000,000,000) ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኝ አንድ ጸሃይ ዙሪያ የሚሽከረከሩ TRAPPIST 1 የሚባሉ ሰባት ፕላኔቶችን አገኘን ብለዋል። ብዙ
አድማጮችን እና ተመራማሪዎችን ያስገረመው ግን NASA እነዚህን ፕላኔቶች አገኘን ብሎ መናገሩ ወይም ፕላኔቶቹ ያሉበት ርቀት አይደለም።
ከዚህ በፊት NASA አድርጎት በማያውቀው መንገድ እነዚህ ፕላኔቶች ውሃ ሊኖራቸው ይችላል፣ እንዲያውም ደግሞ ALIENS ወይም Extra-Terrestrial
Intelligence ወይም ET የተባሉ ፍጥረታት ሊኖሩባቸው ይችላሉ ማለቱ ነው። ይህ ዜና በወጣ በማግስቱም የዓለም ህዝብ ሁሉ
ይህን ዜና በስእልም ሳይቀር እንዲደርሰው የፕላኔቶቹን ፎቶ በፖስተር አድርጎ አውጥቶአል። እዚህ ጎረቤታችን ማርስ ላይ ውሃ አለ
ወይስ የለም ለማለት እስካሁን የፈጀባቸው የNASA ሰዎች እንዴት ነው ዛሬ እንዲህ ፈጥነው እጅግ ሩቅ ባሉና ሰው በተራ ቴሌስኮፕ
እንኳን ሊያያቸው በማይችሉ ፕላኔቶች ላይ ውያ ሊኖር ይችላል ብለው ለማመን የቻሉት?
ታዲያ ይህ ከመጽሃፍ ቅዱስ፣
ከኖህ ዘመን፣ ከጌታ ዳግም ምጽዓት ጋር ምን ግንኙነት ሊኖረው ይችላል??
በኖህ ዘመን እንደሆነው ሁሉ ከወደቁት መላእክት አንዳንዱ ባለፉት 150 ዓመታትም እንደገና ወደምድር በመምጣት ከሰው
ዘር ጋር መደባለቃቸውን የሚያስረዱ ብዙ መረጃዎች አሉ። ከነዚህም ዋነኛው የሁለተኛውን የዓለም ጦርነትን ያካሄዱት የናዚዎች ምስጢር
ነው። ከናዚ ፖለቲካና የጦር ኃይል በስተጀርባ እጅግ ስውር የነበረው የጨለማ ሃይማኖትና እንቅስቃሴ ይመራ የነበረው ደግሞ በኔፊሊም
መሰል ፍጥረቶችና በከፍተኛ የናዚ ባለስልጣኖች ነበር። እነዚያ ኔፊሊም መሰል ፍጥረታትም ጀርመን በዘመኑ ሌሎች መንግስታት የሌሏቸውን
የጦር መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎችን እንደሰጧቸው የሚያሳዩ መረጃዎች ከሩሲያና ከአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች እጅ ዛሬ ወጥተው በአደባባይ
ይገኛሉ። ለዚህ ነው ሂትለር የነዚያን የወደቁ መላእክት ለማስደሰት ሲል ስድስት ሚሊዮን አይሁድን የፈጀው። ለዚህም ነው ከጦርነቱ
ፍጻሜ በኋላ አሚሪካና ሶቪየት ህብረት የጀርመንን ናዚ ከፍተኛ ሳይንቲስቶች በመውሰድ ዛሬ ያሉበት ደረጃ ላይ የደረሷቸውን የጦርነት
ቴክኖሎጂዎች ያገኙት። በታሪክ እንደተነገረን ሂትለር እንዳልሞተ፣ ይልቁንም ጦርነቱ ከማብቃቱ ከብዙ ዓመት በፊት ጀምሮ በነዚያው
በኔፊሊም መሰል ፍጥረታት በመታገዝና በመመራት በደቡብ ዋልታ በሚገኘው የአንታርክቲክ ክፍለ ዓለም ከበረዶው በታች በምድርና ባህር
ስር ከፍተኛ የጦር ሰፈሮችን ሰርቶ ብዙ የቅርብ ደጋፊዎቹን ወደዚያ አሽሽቶ ነበር የሚሉ ብዙ መረጃዎች ዛሬ ወጥተዋል። እሱ ራሱ
ደግሞ ሸሽቶ ወደደቡብ አሜሪካ በመሄድ እድሜ ጠግቦ እንደሞተ ያስረዳሉ። ሶቪየቶች አገኘን ብለው አስቀምጠውት የነበረው የሂትለር
አስከሬንም የሌላ ሴት እንደሆነ ታሪኩ ከሾለከ ውሎ አድሮአል።
እነዚያ ኔፊሊም መሰል ፍጥረታትና
የሚተባበሩአቸው ሰዎች ታዲያ በዚያ በአንታርክቲካ ሆነው እጅግ የላቀ ቴክኖጂዎችን እንደፈጠሩ የቅርብ መረጃ ያላቸው አዋቂዎች ይናገራሉ።
ከነሱ የተረፉአቸውን ትንንሽ ቴክኖሎጂዎች ለቀረው ዓለም ስላካፈሉ ነው ባልታሰበ ፍጥነት የሰው ልጅ ሰማንያ በማይሞሉ ዓመታት ዛሬ
ያለበት ቴክኖሎጂ ላይ የደረሰው የሚሉ መረጃዎችም ብዙ ናቸው። ሂትለር ዓለምን እገዛለሁ ብሎ በጉልበት እንዲነሳ ያደረጉት እነዚያ
ኔፊሊም መሰል ኃይላት ታዲያ ዛሬ ወደ ዓለም ለመምጣትና የሰው ልጅ በሙሉ እነሱን እንዲቀበልና መሪያቸውን፣ እኛ ሃሰተኛው ክርስቶስ
የምንለውን፣ እንዲከተል ለማድረግ ከጦርነት ይልቅ የውሸት ሰላምና የማታለል ስራን ሊሰሩ የተዘጋጁ ይመስላል። ይህንን ጉዳይ በቅርቡ
የሚያጠኑ ክርስቲያን ተመራማሪዎችና የታሪክ ምሁራን እነዚያ ከናዚ ጀርባ የነበሩ ኔፊሊም መሰሎችና ተባባሪዎቻቸው ባለፉት ሰባ ወይም
ሰማንያ ዓመታት ያዘጋጁአቸውን ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ምድርን ለመግዛት ሲመጡ የዓለም ህዝብ በቀላሉ ሊቀበላቸው ይችላል ብለው
ያቀዱት የሰው ልጅ ሌሎች ፕላኔቶችን አገኘ፣ በምርምርም ደግሞ ከእኛ የተሻሉ ሌሎች ፍጥረታት እንዳሉ ደረስንበት በሚል ሽንገላ ሊሆን
እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። በዚሁ በዓለማችን እና በጨለማው መንፈሳዊ ዓለም ያሉ ኃይላት ከሌላ ዓለም መጣን በማለት፣ በብዙ በማናውቀው
ቴክኖሎጂ በማደናበርና የምድርን ህዝብ በማሳሳት ዓለም ዛሬ ካለችበት ውጥንቅጥ ውስጥ አወጣችኋለው የሚለውን መሪያቸውን ሃሰተኛውን
ክርስቶስን ለዓለም ለማስተዋወቅ እየተዘጋጁ እንዳሉ ብዙ አዋቂዎች ይጠረጥራሉ። ባለፈው ዓመት እንኳን ታላላቅ የዓለም መሪዎች፣ የአሜሪካውን
ፕሬዝደንት ኦባማን፣ የሩሲያውን ሊቀጳጳስና የአሜሪካውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጨምሮ ሰው የሌለበትን የአንታርክቲካን ክፍለ ዓለም
መጎብነታቸው ለዚህ ከላይ ለተገለጸው የስውር ዝግጅት መረጃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቁሞአል። ሃሰተኛው ክርስቶስ ሲመጣ ዓለምን ሁሉ
እንደሚያስት ተጽፎዓል። ሳይንስንና ህዋን ተመርኩዞ የሚመጣ ስህተትን ሊቃወም ወይም ሊጠይቅ የሚችል ብዙ አይደለም። በሚባለውና በሚነገረው
ሁሉ አንሸበር፣ አንደናገር። ነገር ግን ከሚመጣው ዓለም አቀፍ ስህተትና ቅዥት ብሎም ከሚከተለው ጥፋት እንድንድን እንጸልይ። ቃሉን
እናንብብ። በዚህ ርዕስ ላይ በመለከት ድምጽ ቁጥር አምስት ላይ የበለጠ መረጃና ትንተናን ለመስጠት እሞክራለሁ። ጌታ ይባርካችሁ።
ዶ/ር በፈቃዱ ብርሃኑ አድማሱ።