(ከጽሁፉ መጨረሻ ላይ የተሰጠውን የድረ ገጽ ማገናኛ በመጫን የተያያዘውን ዜና አንብቡ)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዳግም ምጽዓቱ መዳረስ ደቀመዛሙርቱ በጠየቁት ጊዜ ከሰጣቸው ምልክቶች አንዱ “ጦርንም እና የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፣ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው” ማቴዎስ 24:6 የሚል ነበር። ቃየል ወንድሙን አቤልን ከገደለው በኋላ የሰው ልጅ ከጦርነት ያረፈበት ረጅም ዘመን ባይኖርም የጌታ መመለስ ሲቃረብ በምድር ላይ የሚታዩት ጦርነቶች ግን እጅግ ታላላቅና ብዙ ህዝብን የሚፈጁ መሆናቸው በመጽሀፍ ቅዱስ ተገልጦአል። ያለፈው 20ኛው ክፍለ ዘመን ዓለማችን በሰው ልጅ ታሪክ ታይተው የማይታወቁ ሁለት ታላላቅ ጦርነቶችን፣ ማለትም አንደኛውንና ሁለተኛውን የዓለም ጦርነቶች ያየችበት ጊዜ ነበር። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ከአስራ ሰባት ሚሊዮን በላይ ህዝብ ሲያልቅ የቆሰለው ደግሞ ከሃያ ሚሊዮን በላይ ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሞተው ህዝብ ደግሞ ወደ ስድሳ (60) ሚሊዮን የሚገመት ሲሆን በጦርነቱ ሳቢያ በመጣ ረሃብና በሽታ ያለቁት ደግሞ ወደ ሃያ (20) ሚሊዮን ናቸው። ይህም በጠቅላላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያለቀውን ህዝብ ቁጥር ወደ ሰማኒያ (80) ሚሊዮን ያደርሰዋል። እነዚህ ከ1914 እስከ 1918 እና ከ1939 እስከ 1945 የተካሄዱ ሁለት የዓለም ጦርነቶች የፈጁት ህዝብ ከመቶ (100) ሚሊዮን በላይ ነው ማለት ነው። በአገር ደረጃ ብናየው ደግሞ ያለቀው ህዝብ ቁጥር ዛሬ በምድር ላይ ከሚገኙት 196 አገሮችና ግዛቶች ውስጥ አናሳ የህዝብ ቁጥር ያላቸውን 71 (ሰባ አንድ) አገሮች በሙሉ የሚደመስስ ነበር ማለት ነው። እነዚህ ሁለት የዓለም ጦርነቶች ምንም ያህል ትልልቅ ቢሆኑም ታዲያ፣ ገና ሊመጡ ካላቸው ጦርነቶች ጋር ሲወዳደሩ እጅግ ትንሽ እንደሚሆኑ ብዙ መረጃዎች ያሳያሉ። ዛሬ በዓለማችን ላይ ካሉት የጦር መሳሪያዎች ዓይነትና ብዛት ጋር ሲመዛዘኑ የሰው ልጅ በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተዋጋባቸው መሳሪያዎች እጅግ ኋላ ቀርና ደካማ ነበሩ። በሂሮሺማ ጃፓን ላይ የተጣለው የአቶሚክ ቦምብ ጉልበቱ አስራ አምስት ሺ ኪሎ ቲኤንቲ (15KILO TON TNT) ሲሆን በናጋሳኪ ላይ የተጣለው ደግሞ ጉልበቱ ሃያ ሺ ኪሎ ቲኤንቲ (20 KILO TON) ነበር። እነዚያ ሁለት ቦምቦች በድምሩ ከ129ሺ እስከ 246 ሺ ወታደሮችና ሲቪል ህዝቦችን አሰቃቂ በሆነ መንገድ ፈጅተዋል። በሂሮሺማ ላይ የተጣለው ቦምብ ክብደቱ አራት ሺ አራት መቶ ኪሎግራም ሲሆን የናጋሳኪው ደግሞ 4670 ኪሎግራም ነበር። በዘመኑ እጅግ ታላቅ የተባሉት እነዚያ አቶሚክ ቦምቦች ጉልበት ከዛሬዎቹ ጋር ሲወዳደር ታዲያ እነዚያ የ1945ቶቹ የሚመደቡት በጣም ትንንሽ ወይም በሰው የጀርባ ቦርሳ ሊያዙ ይችላሉ ከሚባሉት ጋር ነው። ሩሲያ በቅርቡ እንደሰራችው የተዘገበው RS28 SARMAT የሚባለው የኑክሊየር ቦምብ(ሚሳኤል) ሶቪየት ህብረት ሰርታው የነበረውን RS36 SATAN የተባለውን የሚተካ ሲሆን፣ ይህ ቦምብ እንግሊዝን ወይም ፈረንሳይን የሚያህል አንድን አገር በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ የሚያጠፋ እንደሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህንን እና ከዚህ አነስ የሚሉ ከ13800 (አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ) የኑክሌየር ቦምቦች ዛሬ በአገሮች እጅ ውስጥ አሉ። ከነዚህም ውስጥ 3530 የሚሆኑት በማንኛውም ሰዓት ለመተኮስ ተዘጋጅተው በተጠንቀቅ ይጠብቃሉ። ሩሲያ 7000 የኑክሌየር ቦምቦች እንዳሏት ሲገመት አሜሪካ ደግሞ 6800 እንዳሏት ይዘገባል። ከዘጠና ከመቶ በላይ የሚሆኑት እነዚህ ምድርን አጥፊ መሳሪያዎች የሚገኙት በአሜሪካና በሩሲያ እጅ ነው። ሁለቱ አገሮች ብቻ በድምር 13800 ቦምቦች ሲኖሩአቸው ታናናሽ የኑክሌየር ሃይሎች የሚባሉት ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ ህንድና እስራኤል ደግሞ በድምሩ 1105 ቦምቦች አሉአቸው። ሰሜን ኮሪያም ይህ መሳሪያ እንዳላት በሰፊው ይዘገባል። “እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋን የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር ብሎ ጌታ በማቴዎስ 24:22 ላይ የተናገረው እነዚህና ሌሎችም ብዙ የዘመናችን አስፈሪ የጦር መሳሪያዎች የሚያመጡትን እልቂትም ሊመለከት እንደሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢትና የሳይንሱ እውቀት ያላቸው ሰዎች ያስረዳሉ። ዓለማችን በዚህ ዓይነት የፍጅት ፍጥጫ ውስጥ ሆና እያለች ነው ከ2012 ጀምሮ ብዙዎች፣ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት በቅርቡ ሊነሳ ይችላል የሚሉት። የካቶሊኩን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እንዲያውም ይህ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት አሁንም ትንሽ በትንሽ ጀምሮአል በማለት ደጋግመው ተናግረዋል። ልብ እንበል፣ ይህ የአፍ ወለምታ አይደለምና። አሜሪካና አጋሮቿ በአንድ በኩል፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያና ሌሎችም አገሮች ከባድ በሆነ የጦርነት ዝግጅት ውስጥ ከገቡ ዓመቶች እየተቆጠሩ ነው። ካለፈው ዓመት የክረምት ወራት (SUMMER) ጀምሮ አሜሪካ ብቻ ከ2500 በላይ ታንኮችን እና በቅርቡ ደግሞ ከ100 በላይ የጦር ሄሊኮፕተሮችን ወደ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ፖላንድ እና ሶስቱ የቦልቲክ ሪፐብሊክ ወደሚባሉት አገሮች አስገብታለች። ሩሲያ በበኩሏ ሰራዊቷን በሙሉ በተጠንቀቅ ላይ በማቆም ከፍተኛ የጦርነት ልምምዶችን እያደረገች ነው። በደቡብ የቻይና ባህር አካባቢም አሜሪካና ቻይና በፍጥጫ ላይ ናቸው። ሰሜን ኮሪያም በበኩሏ የኑክሌየር ቦምቦች እና የሚሳኤል ተኩስ ልምምዶችን እያደረገች መሆኑ በየእለቱ የሚዘገብ ነው። ጦርነት በድንገት አይፈነዳም። ኃይለኞቹ የዓለም አገሮች ሁሉ ከፍተኛ የጦርነት ዝግጅት እያደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። የሶቪየት ህብረት የመጨረሻ ፕሬዝደንት የነበሩት ሚካኤል ጎርባቾቭ በቅርቡ ይህን በማስመልከት ሲናገሩ ዓለም ለሶስተኛው የዓለም ጦርነት በከፍተኛ ፍጥነት እየተዘጋጀች ነው በማለት አስጠንቅቀዋል። የዓለም ከፍተኛ የኑክሊየር ባለሙያዎች ማህበርም ዓለም በኑክሊየር ጦርነት ልትጠፋ የቀራት ሁለት ደቂቃ ነው በማለት አስጠንቅቀዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል። ዳሩ ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ያመነ ክርስቲያን ሊፈራ አይገባውም። ማወቅ፣ መጸለይ፣ በልብ መዘጋጀትና ለሚጠፉት ወንጌልን መስበክ ግን ግዴታችን ነውና እንትጋ። በሚቀጥሉት መልእክቶቼ ላይ የበለጠ ዝርዝርን ለመስጠት እሞክራለሁ። ከ100 በላይ የአሜሪካ የጦር ሄሊኮፕተሮች አውሮፓ ገቡ

እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ ልባችሁንም በሰላሙ ይጠብቅ። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ