በዚህ ባለፈው ሳምንት አምስተኛው የዓለም መንግስት ጉባኤ በዱባይ መካሄዱን ሰምታችሁ ይሆን? ከ1800 ዓመታት በፊት በፓልማይራ
ሶሪያ ተሰርቶ የነበረውና በISIS የፈረሰው የበዓል ቤተ ጣዖት ቅጂ በ3D ማተሚያ ተሰርቶ በለንደን፣ በኒውዮርክ እና አሁን ደግሞ
በዱባይ እንደተተከለስ አንብባችኋል ወይ?
“የዓለም መንግስት” ጉባኤ ማለት የምታውቁት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ
አይደለም። ይህ ጉባኤ እንደሚካሄድ በዜና በሰፊው የሚዘገብ አይደለም። ከFEBRUARY 12 እስከ 14 የተካሄደው ይህ “የዓለም
መንግስስት” ጉባኤ ግን ትንሽ ስብሰባ አይደለም። አራት ሺ (4000) የሚሆኑ የአገር መሪዎችና ከፍተኛ የመንግስታት ባለስልጣኖች
እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዋና ዲሬክተርም የተሳተፉበት ነው። ይህ ከ2013
ጀምሮ በዱባይ እየተካሄደ ያለ ታላቅ ስብሰባ ከመጀመሪያው ዓመት ስብሰባው ተካፋዮች አንዱ የጊዜው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም
ነበሩ። ታዲያ እንዲህ ያለ ታላቅ ጉባኤ እየተካሄደ ሳለ የተበላ የተተፋው ሁሉ ዜና ተብሎ በሚቀርብበት በምእራቡ ዓለም እንኳን እንደ
ታላቅ ዜና አይቀርብም። ለዚህም ነው ብዙ የታሪክና የመጽሐፍ ቅዱስ
ትንቢት ፍጻሜን የሚከታተሉ ምሁራን ይህ “የዓለም መንግስት” ወይም “WORLD GOVERNMENT” የተባለው የቱ ነው? መቼ ነው
የተመሰረተው? ማን መሰረተው? የተባበሩት መንግስታት እያለ ይህ ለምን አስፈለገ? ወይም ደግሞ ምናልባት በመጨረሻው ዘመን ይገለጣል
የተባለው በሃሰተኛው ክርስቶስ ስር የሚመራው አንድ የዓለም መንግስት ጥንስስ ይሆን ወይ እያሉ ጥያቄዎችንና መላምቶችን እየሰነዘሩ
ያሉት? በዚህ ዓመቱ አምስተኛ ስብሰባው ላይ ከ130 የዓለም አገሮች የተውጣጡ መሪዎች የተገኙበት ይህ ጉባኤ በምድራችን ላይ ያሉ
ዋና ዋና የሚባሉ እንደ “የዓለም የኢኮኖሚ መድረክ WORLD ECONOMIC FORUM” ያሉ እና ሌሎችም ትልልቅ ድርጅቶች የተሳተፉበት
ነው? ብዙ የትንቢት ፍጻሜን የሚከታተሉ ምሁራንን ከሚከነክነው ነገሮች አንዱ ደግሞ የሚከተለው ነው። ቁመቱ 20 ጫማ የሚሆን ከ1800
ዓመታት በፊት በፓልማይራ ሶሪያ ተሰርቶ የነበረውና ISIS ያፈረሱት የበዓል ቤተ ጣዖት መግቢያ ታላቅ በር (ARCH) በ3D ማተሚያ
የተሰራ ምስል በ2016 ዓም ተሰርቶ በለንደንና በኒውዮርክ በአደባባይ ቆሞ ነበር። አሁን ደግሞ ይህ በር የዓለም መንግስት ጉባኤ
በሚካሄድበት በዱባይ ተተክሎ ሰንብቷል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዓል የሚባለው ጣዖት በብዙ ስሞች በየአገሩ ይጠራ እንጂ ከጥፋት
ውሃ በኋላ በባቢሎን ተመስርቶ የነበረው አንድ የዓለም መንግስት ገዢና አምላክ ተብሎ የሚመለክ ነበር። ይህ አምላክ በሮም አፖሎ፣
በግሪክ ዙስ፣ በግብጽ አይሲስና በሌሎችም አገሮች የተለያዩ ስሞችን ይዞ እስከዛሬም ድረስ በስውር የሚመለክ ነው። በተለምዶ እንደሚነገረን
ጣዖት ድንጋይና ብረት ሳይሆን ከበስተጀርባው እጅግ ኃይለኛ የሆኑ የወደቁ መላእክትና የአጋንንት መናፍስትን የሚወክል ነው። በዓል
የሚባለው መንፈስ ደግሞ በመጨረሻው ዘመን ከጥልቁ እንደሚወጣ በዮሃንስ ራእይ የተነገረለት የሃሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ እንደሆነ
ብዙ የመጽሃፍ ቅዱስ ትንቢት አስተማሪዎች ይስማሙበታል። ታዲያ ይህ የፈረሰው የፓልማይራው የበዓል ቤተ ጣዖት መግቢያ በር ቅጂ ለምንድ
ነው እንደገና በ2016 ዓም የተሰራውና በዓለም ዋና ዋና ከተማዎች ሁሉ በአደባባይ ሊተከልና ሊታይ የተፈለገው። ከሁሉም በላይ ደግሞ
ለምንድ ነው ይህ አምስተኛው የዓለም መንግስት ጉባኤ በሚካሄድበት በዱባይ ከተማ የተተከለው። እነዚህ ሁኔታዎች ናቸው ታዲያ ይህ
የዓለም መንግስት ጉባኤ የተባለው ምናልባት በመጨረሻው ዘመን ይመጣል የተባለው በሃሰተኛው ክርስቶስ የሚመራው አንድ የዓለም መንግስት
ጥንስስ ይሆን ወይ እያሉ ብዙዎች እንዲጠይቁ ያነሳሳው። የተያያዙትን ዜናዎች የኢንተርኔት ማገናኛዎች (LINKS) ከዚህ ቀጥሎ ልኬያቸዋለሁና
አንብቡአቸው። መጽሃፍ ቅዱሳችንን፣ በተለይም የዚህን ዘመን መልክ የሚያስረዱንን ትንቢቶች ቀረብ ብለን እናጥና። በዓለም ላይ እየተካሄዱ
ያሉትን ትንቢት ነክ ዜናዎች ከልብ እናስተውል።የጌታ መምጣት እየተቃረበ ሲሄድ ዓለም ሁሉ በትልቅ ስህተት ውስጥ እንደሚገባ ተጽፎአል።
በክርስቶስ የምናምን ሁሉ ግን መጽሐፍ ቅዱስን በእጃችን ይዘን እና፣ የእግዚአብሔር መንፈስም ወደእውነት ሁሉ ሊመራን ዝግጁ ሆኖ
ሳለ ዓለም በሚሳሳትበት ስህተት መሳሳት የለብንም። ጌታ እግዚአብሔር ክርስቶስን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ ይስጠን። ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ማገናኛዎች በመከተል አንብቡ። ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ አንድ የዓለም መንግስት ጉባኤ በዱባይ ተካሄደ፣ የበዓል ቤተ ጣዖት መግቢያ በር በዱባይ ተተከለ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ