የመጽሄቷን PDF ኮፒ ዳውንሎድ በማድረግ ማንበብ ይቻላል፤ ይህ መልእክት ለማይደርሳቸውም እንድታደርሱ በትህትና እጠይቃለሁ።
በዚህች እትም ውስጥ የሚከተሉት ትምህርቶችና ሃሳቦች እንዲሁም
ደግሞ ካለፈው የቀጠለው የዶ/ር ዘመድኩን ተሻለ የህይወት ምስክርነት ክፍል አራት ቀርበዋል።
1) 1) በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተገለጠችው ታላቂቱ ጋለሞታ፣ የምስጢር ባቢሎን ማን ትሆን?
2 2) መጽሐፍ
ቅዱስ “ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ”፣“የዓመጽ ሰው”፣ “የጥፋት ልጅ” የሚለው ማንን ነው?
3) የሃሰተኛው ክርስቶስ ምልክት ወይም 666 የሚባለው ምን ሊሆን ይችላል?
4 4) በየእለቱ በታላቅ ፍጥነት እየበዛና እየተራቀቀ የሚሄደው ቴክኖሎጂ እና የመጨረሻው ዘመን የሚገናኙበት ምስጢር ይኖር ይሆን?
ለነዚህና ሌሎችም ተያያዥ ጥያቄዎች በአጭሩ መልስ ለመስጠት ተሞክሯል። ባለፉት ሁለት ሺ ዓመታት በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት
ተመራማሪዎችና ጸሐፊዎች የሰጧቸውን ግምገማዎች እና ትንተናዎች በመመርኮዝና በዘመናችን የተደረጉና እየተደረጉ ካሉ ጥናቶች ሰፋ ያለ
ተቀባይነት ያላቸው ሃሳቦችና መረጃዎችም ቀርበዋል።
ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል። አይዘገይምም፤ ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፥
ወደኋላም ቢያፈገፍግ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እብራውያን 10፡37
ማራናታ !! አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!!
ወንድማችሁ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ