የኖህ ዘመን እንደነበረ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት
እንዲሁ ይሆናል፥ ትምህርት ቁጥር 3
በትምህርት 1 እና 2 ላይ
እንደተመለከትነው እጅግ አስደናቂ የሆኑና እንደ ብርቅ የሚታዩ ብዙ ጥንታዊ ስፍራዎች አሉ፣ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ቱሪስቶች ይጎበኛሉ፣
በተለያየ የእውቀት መስክ በተሰማሩ ተማራማሪዎችና ምሁራንም እየተጠኑ ናቸው። ለምሳሌም ያህል የጠቀስኳቸው የግብጽ ፒራሚዶች፣ በሊባኖስ
ባዓልኤክ የሚገኘው የጁፒተር ቤተ መቅደስ፣ በካምቦዲያ የሚገኘው የአንግ ኮር ዋት ቤተ መቅደስ እንዲሁም በሜክሲኮ፣ በፔሩ እና በሌሎችም
የደቡብ አሜሪካ አገሮች፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በእስያ የሚገኙ እጅግ ብዙ ፒራሚዶች፣ ቤተ መቅደሶች፣ ታላላቅ የጥንት
የአምልኮና የስፖርት ማእከሎች፣ አገርን ከአገር እና ከተማን ከከተማ የሚያገናኙ የመሬት ውስጥ ዋሻዎችና መንገዶች እንዲሁም ባህር
የከደናቸው ከተሞች አሉ። ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የተማርናቸው የታሪክ፣ የአርኮዎሎጂ እና ሌሎችም የህብረተሰብ ሳይንሶች
እንደ ነገሩን ከሆነ ታዲያ እነዚህ ግዙፍ፣ አስደናቂና ውስብስብ ነገሮች የተሰሩት የሰው ልጅ የድንጋይ መሳሪያዎችን ከመጠቀም አልፎ
የነሃስ መሳሪያዎችን መስራት በጀመረባቸው ዘመናት ነበር። ታዲያ የሰው ልጅ ብረትንና የብረትን መሳሪያዎች እንኳን ገና ባልሰራበት
በዚያ ዘመን እንዴት አድርጎ ነው እነዚህን እጅግ ታላላቅ ነገሮች የሰራው የሚለውን ጥያቄ ተመራማሪዎች እስከ ዛሬ ሊመልሱት አልቻሉም።
እነዚህ ግዙፍ ስራዎች እንኳን በነሃሱ ዘመን ይቅርና ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመንም እንኳን የሰው ልጅ በደረሰበት የእውቀትና የቴክኖሎጂ
አቅም ለመሰራት እጅግ አዳጋች፣ ብዙ ጊዜና ወጭ የሚጠይቁ ናቸው። ለምሳሌና የነዚያን የጥንት ስራዎች ከባድነት ለማነጻጸር ያህል
ባለፈው በ2016 ዓም በዘመናዊቷ በስዊትዘርላንድ ውስጥ ተጠናቆ የተመረቀው የጎታርድ የምድር ውስጥ መንገድ (TUNNEL) ለምሳሌ
ቁመቱ 15 ኪሎ ሜትር ሲሆን በመጀመሪያ ስራው የተጀመረው በ1871 ዓም ነበር። በጊዜው በብዙ ችግሮች ምክንያት ሊጠናቀቅ ስላልቻለ
እንደገና በ1990ዎቹ መጨረሻ ላይ ተጀምሮ ከ18 ዓመታትና ከ23 ቢሊዮን ዶላር ወጭ በኋላ ነበር በ2016 ስራው የተጠናቀቀው።
እስቲ ለምሳሌ ያህል ከነዚህ
ትልልቅ የጥንት ዘመን ስራዎች መካከል አንዱን ብቻ ባጭሩ እንመልከት። ከአባይ ወንዝ በስተምዕራብ ድሮ ሜምፊስ ተብላ ትጠራ ከነበረችው
ከተማ ሳይርቅና በዛሬዋ የካይሮ ከተማ ፊት ለፊት የሚገኘው እጅግ ታላቅ የሆነው የጊዛ ፒራሚድ በጣም ከሚታወቁት ታላላቅ የጥንት
ስራዎች አንዱ ነው። የዚህ ፒራሚድ አሰራር ፣ ግዙፍነቱ፣ የተሰራባቸው ድንጋዮች ትልልቅነት፣ ከባድነት፣ ጠንካራነት፣ እንከን የሌለው
አቆራረጥና ልሙጥ መሆን፣ ፒራሚዱ የተሰራበት ስፍራ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ እና ከታዋቂ የሰማይ ከዋክብትና የከዋክብት ክምችት ጋር
ያለው ቅኝት በሙሉ ሲታሰብ ሰሪዎቹ እጅግ የላቀ የሂሳብ፣ የምህንድስና፣
የጂኦግራፊ፣ የጂኦሎጂ እና የከዋክብት ጥናት እውቀት ብቻ ሳይሆን ዛሬም እንኳን የሰው ልጅ የሌሉት የምህንድስና ቴክኖሎጂ፣ የኃይል
ምንጭና የመጓጓዣ መሳሪያዎችም እንደነበሯቸው ያሳያሉ። ብዙ ምሁራንንና ተመራማሪዎችን እዚህ ድምዳሚ ላይ ካደረሱአቸው መረጃዎች አንዳንዶቹ
የሚከተሉት ናቸው። የጊዛው ፒራሚድ የተሰራው እጅግ ጠንካራ ከሆነው ግራናይት ከሚባለው ድንጋይና ከኖራ ድንጋይ ነው። በተሰራበት
ዘመን የውጭ አካሉ ፍጹም ልሙጥና ለስላሳ ሆኖ ከሰማይ ሲታይ የሚያንጸባርቅ እንደነበር ይታመናል። አንዳንድ አፈ ታሪኮች ደግሞ ፒራሚዱ
ቁመቱ ከዘጠኝ ሜትር በላይ (30 ጫማ) ከሆነ ከወርቅ የተሰራ ጫፍ ወይም ቆብ ነበረው ይላሉ።
ፒራሚዱ ለማያውቀው ተራ የድንጋይ ክምር ይምሰል እንጂ በውስጡ ለመተላለፊያና
አየርን ለማንሸራሸር የሚሆኑ ታላላቅ መንገዶች ወይም ኮሪደሮች አሉት። ለማምለኪያ ወይም መስዋእት ማቅረቢያ የተሰሩ የሚመስሉ ክፍሎችም
በውስጡ አሉ። ፒራሚዱ የተቀመጠው 57200 ካሬ ሜትር በሚሆን ቦታ ላይ ሲሆን የተሰራው ደግሞ በግምት 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ከሚሆኑ
ድንጋዮች ነው። የተሰራባቸውም እያንዳንዱ የግራናይት ድንጋዮች ክብደታቸው እስከ 50 ቶን (50 ሺ ኪሎ) የሚመዝኑ ሲሆን፣ ብዙዎቹ
ድንጋዮችም እስከ 100 ቶን (100ሺ ኪሎ) ይደርሳሉ። ፒራሚዱ መሬት ላይ ያረፈበት ቅርጹ አራት ማእዘን (SQUARE) ሲሆን አራቱ
ገጾቹ ደግሞ እኩል ቁመት ያላቸው ሶስት ማእዘኖች ናቸው። እነዚህም አራት ገጾች ፊታቸው ወደ ምስራቅ፣ ምእራብ፣ ሰሜንና ደቡብ ያመለክታል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ክንድ (CUBIT) ሲለካ የእያንዳንዱ የአራቱ ማእዘን ቁመት 365.2422 ክንድ ነው። ይህ ቁጥር ደግሞ በአንድ የጸሃይ ዓመት ውስጥ ያሉትን የፍጹም ቀኖች ቁጥር ያመለክታል።
አራቱ ባለ ሶስት ማእዘን ገጾቹ ዘንበል ያሉበት ማእዘን (ANGLE) አራቱ ገጾቹ በ232.52 ክንድ ከፍታ ላይ እንዲገናኙ ያደርጋቸዋል። የፒራሚዱ እግር ያረፈባቸው ሁለት ወገኖች ቁመት ተደምሮ
በዚህ ቁጥር (በ 232.52 ሜትር) ቢካፈል በሂሳቡ ዓለም በጣም
የሚታወቀውን ቁጥር 3.14159ን ወይም ፓይ (PI) የሚባለውን ይሰጠናል። በመሬት ላይ ያረፈበት
የአራቱ ማዕዘኖች ቁመት ሲደመር ደግሞ (365.2422 X 4)=14609.68 ነው። ይህ ደግሞ የፒራሚዱ ቁመት ሁለት እጥፍ የሆነ የወገብ ስፋት ካለው (232.52) ክብ ቅርጽ የዙሪያ ቁመት (CIRCUMFERENCE) ጋር እኩል ነው። ማለትም (232.52 X 2 X 3 3.14159)። ይህ ማለት ደግሞ ፒራሚዱን የሰሩት
አራት ማዕዘንን ወደ ክብ መቀየር የሚለውንና ከላይ የተገለጹትንም ውስብስብ የሂሳብ ህጎችና ስሌቶች ማወቅ ብቻ ሳይሆን ሃሳቡንም
ይህን በሚያህል ግዙፍ ስራ ላይ ማዋል የሚችሉ ነበሩ ማለት ነው።
ከላይ የተሰጠውን መረጃ
እንኳን ረጋ ብለን ብናጠናው እጅግ ብዙ ጥያቄዎችን እናነሳለን። ለመሆኑ እንዴት ነበር ሰሪዎቹ 100 ሺ ኪሎ የሚከብዱ የግራናይት
ድንጋዮችን ስህተትና እንከን በሌለው ቅርጽና ፍጹምነት የቆረጡት። ድንጋዩ ከተቆረጠበት ቦታ ፒራሚዱ ወደተሰራበት ቦታ ያጓጓዙት እንዴትና
በምን ነበር? ከዚያስ ደግሞ በምንና እንዴት ነበር ድንጋዮቹን እያነሱ ይህንን ተራራ የሚያህል ነገር የገነቡት? እነዚህ እጅግ ግዙፍ
የሆኑ ድንጋዮች የተቆረጡበት መሳሪያ ምን እንደነበር እንኳን ሊታወቅ እስከማይችል ድረስ ማእዘናቸው ያለ እንከን የሆነና ድንጋዮቹም ሲቆረጡ በላያቸው የቀረ የየመጋዝ ወይም የመሮ ምልክት እንኳን የሌለባቸው
ለስላሳ ናቸው። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ፒራሚዱ ሌሎች እጅግ ብዙ
አስገራሚ ምስጢሮችንም ይዟል። ለምሳሌ ወደላይ የቆሙት የአራቱ ማእዘኖቹ ዝንባሌ (ANGLE) ከቁመቱ ጋር ሲነጻጸር 10 በ 9 ነው። ማለትም ፒራሚዱን እንደመሰላል አድርገን ወደ ላይ አስር ጫማ ብንወጣ
ከምድር ከፍ የምንለው ግን 9 ጫማ ብቻ ነው። ይህ ስሌት ምስጢርን ይዟል። የፒራሚዱ ጠቅላላ ከፍታ (232 52 ክንድ) ሲባዛ በ10 ሲባዛ በ9 ኃይል (ማለትም 232 52 X 10^9) የሚሰጠን ቁጥር 91,840,000 ማይል ወይም ከምድር እስከ ጸሃይ ድረስ ያለውን ርቀት ነው። የሰው ልጅ በእጅ የሚገፋ ጋሪ እንኳን ባልነበረው በዚያ ዘመን
እነዚያ ገንቢዎች ከምድር እስከ ጸሃይ ድረስ ያለውን ርቀት ማወቅ ብቻ ሳይሆን ማወቃቸውንም ደግም በፒራሚዱ ልኪት ላይ በምስጢር
ስሌት ማስቀመጣቸው የዘመናችንን ትልልቅ መሃንዲሶች፣ የሂሳብ፣ የህዋ ምርምርና ሌሎች ሊቃውንትንም ግራ ያጋባ ነገር ነው።
ፒራሚዱ በምድር ላይ የተቀመጠበት
ቦታ በካርታ ላይ አሉ ብለን በምንጠቀምባቸው ሃሳባዊ የአግድም እና የቁልቁል መስመሮች (LONGITUDE AND LATTITUDE)
ላይ ሲታይ በ30ኛው ዲግሪ ላቲቲውድ እና በ30ኛው ዲግሪ ሎንግቲውድ መገናኛ ላይ ነው የተተከለው። ይህ ቦታ ደግሞ በዓለማችን ላይ
ያለውን የብስ አራት እኩል ቦታ የሚከፍል ቦታ ነው። የፒራሚዱ ሰሜናዊ ገጽም ከውነተኛው የምድር ሰሜን ዋልታ ጋር በትክክል የተቀመጠ
ነው። ኮምፓስና ማግኔት ባልነበረበት ዘመን ይህን ማድረግ ለሰው ልጅ በፍጹም የማይቻል ነገር ነው ቢባል መረዳቱ ያላቸው ብዙ ሰዎች
ይስማማሉ። የምድርን ካርታ በሎንግቲውድ እና በላቲቲውድ ከፍሎ የማስቀመጥ ሃሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ የተሞከረው ከክርስቶስ
ልደት በፊት በ2ኛው ዓመተ ዓለም (ከ200 እስከ 101 ዓመተ ዓለም) በግሪካዊው ሂፓርከስ ነበር። ይህ የጊዛ ፒራሚድ ደግሞ ተሰርቶ
የተጠናቀቀው በ2560 ዓመተ ዓለም ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ማለትም ሎንግቲውድ እና ላቲቲውድ የሚባሉት መስመሮች ከመታሰባቸው ከ2360
ዓመት በፊት ነበር ማለት ነው።
የፒራሚዱ ሰሪዎች ፒራሚዱ
በምድር ላይ የተቀመጠበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን ፒራሚዱ ከሰማይ ከዋክብትና፣ ከዋክብቱም የምድር አራቱ ወቅቶች በተለዋወጡ ቁጥር ሊታዩ
የሚችሉበትን አቅጣጫ እና ከፒራሚዱ መስኮቶች ወደ ከዋክብቱ ሊኖር የሚገባውን ዝንባሌም (ANGLE) በትክክል በማስላት በማነጻጸር ነው
የሰሩት። በፒራሚዱ ሰሜናዊና ደቡባዊ ገጾች (ግድግዳ) ላይ ከውጭ ወደ ፒራሚዱ መሰረት የሚወርዱ ሁለት ሁለት የመተላለፊያ
ዋሻ መሰል ቀዳዳዎችን ሰርተዋል። በሰሜን በኩል ካሉት ሁለት ቀዳዳዎች አንዱ ቤታ ኡርሳ ሌላው ደግሞ አልፋ ድራኮኒስ ወደሚባሉ በድራኮ የከዋክብት ክምችት ውስጥ
ወዳሉ የታወቁ ከዋክብት በቀጥታ ያመለክታሉ። በደቡባዊው ገጹ ላይ ያሉት ሁለት ቀዳዳዎች ደግሞ ሲሪየስ እና ዜታ ኦሪዮኒስ ወደሚባሉት
ግብጻውያን ያመልኳቸው ወደነበሩ ከዋክብት ያመለክታሉ። ይህ ፒራሚዱ ከሰማይ ከዋክብት ጋር በመገናዘብ የተሰራበት እውቀት በዓለም
ላይ ባሉት በሌሎቹም ብዙዎች ጥንታዊ ቦታዎች ስራ ላይ መዋሉ ተረጋግጦአል። ከላይ ባጭሩ የተገለጹትንና ሌሎችንም ብዙ መረጃዎች ያጠኑ
ምሁራን፣ ይህ ፒራሚድና ሌሎችም ብዙዎች በምድር ሁሉ ያሉና አስደናቂ የተባሉ የጥንት ስራዎች እንዴት እንደተሰሩና ማን እንደሰራቸው
ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እስከዛሬም ድረስ ሊያረጋግጡ አልቻሉም። ነገር
ግን ታሪካቸው በየትምህርት ቤቱና በየዩኒቨርሲቲው ከሚሰጡት ትምህርቶች ጋር እንዳይጋጭ በማለት ብቻ፣ እነዚህ የጥንት ስራዎች ያሉባቸው
አገሮች “የጥንት ህዝቦች ስራዎች” ናቸው በሚል መሸፈኛ ብቻ ያልፉታል።
እግዚአብሔር ግን ራሱንና
ቃሉን ያለ ምስክር አይተውምና ባለፉት 200 በሚሆኑ አመታት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸውን ነገሮች በጥሞናና በብዙ ሳይንሳዊ መንገዶች
የሚያጠኑና ቃሉን የሚያምኑ ምሁራን ስለ ግብጹ ፒራሚድም ሆነ ስለ ሌሎቹ አስገራሚ የጥንት ስራዎች አመጣጥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጣቸው
ብዙ መረጃዎች እንዳሉ ደርሰውበታል። ምድር በጥፋት ውኃ ከመጥፋቷ በፊት ቀደም ብሎና ከዚያም በኋላ በአንድ የተሳሳተ ኪሩብ (ሰይጣን
በምንለው) መሪነት ከክብራቸው ከወደቁት እጅግ ብዙ የሰማይ ሰራዊት መካከል አንዳንዶቹ ወደ ምድር በመውረድና የእግዚአብሔርን የፍጥረት
ህግ በመጣስ ከሰው ሴቶች ልጆች ጋር በመደባለቅ ኔፊሊም የሚባሉትን እንደወለዱ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 6 ላይ እናነባለን። እነዚህ
ኔፊሊም ደግሞ በምድር ላይ ኃያላን እንደነበሩ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ እናነባለን። ይህንን መረጃ በሚገባ ተረድተን እንኳን ሳናበቃ ነው በዚሁ በዘፍጥረት ምእራፍ 6 ላይ ጌታ አምላክ በሰው
ልጅ ላይ መቆጣቱንና ምድርን በውኃ ለማጥፋት መወሰኑን ለኖኅ የገለጸው። ከላይ ያነበብነውን የግብጹን ፒራሚድና የሌሎችንም የጥንት
ስራዎች በተመለከተ ዘፍጥረት 6 ብቻውን መልሱን በሙሉ አይነግረንም። መነሻው ግን የዚሁ የወደቁት መላእክት ዘራቸውን ከሰው ዘር
ጋር የማደባለቁና እጅግ ግዙፍ፣ ኃያላንና ብዙ እውቀትና ቴክኖሎጂ የነበራቸው የኔፊሊም በምድር ላይ መብዛት ነበር።
አማልክት ነን በማለትና
የሰውን ልጆች በማስጨነቅ በጥንት ዘመን በምድር ሁሉ ይገዙ የበሩት እነዚህ ኔፊሊምና ከነሱ የወጡ ዘሮች ናቸው። በጥንት ዘመን የታወቁ
ኃያላንነበሩ ብሎ ዘፍጥረት 6 የሚጠቅሳቸው እነዚህ እኩይ ፍጥረቶች በኖኅ ዘመን ምድርን በዓመጻና፣ በደም መፋሰስ ምልተዋት ነበር።
እነዚህ ናቸው የከነዓንን ምድር ሞልተው ምድሪቱን ያረከሱትና ጌታ አምላክም ሙሴንና እስራኤልን ፈጽማችሁ አጥፉአቸው ብሎ ያዘዛቸው።
እነዚህ ናቸው ለሰው ልጅ መፋጀትን፣ ልጆቻቸውን እንደ መስዋእት ለአጋንንት ማቅረብንና ሌሎችንም እጅግ ዘግናኝ ኃጢአቶችን ያስተማሩት።
ይህ እውነት ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ራዕይ ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጧል። ኔፊሊም እጅግ ግዙፍ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስም
እነዚህን ህቦች ኔፊሊም፣ ራፋይም፣ አናቃውያን፣ ሖራውያን ኤሚማውያን፣
ዘምዙማውያን፣ ወዘተ በማለት ይጠራቸዋል። እነዚህ ኔፊሊምና ዘሮቻው ናቸው አማልክት ነን በማለት በብዙ ስሞች እስከ ዛሬ ድረስ የሚመለኩት።
እነዚህን ህዝቦች ነው ከኢያሱ ጋር ሄደው የነበሩት ሰላዮች “እኛ በፊታቸው እንደ አንበጣ ነን” ብለው የፈሩት።
እነዚያ የኔፊሊም ህገ ወጥ
አባቶች የሆኑት የወደቁ መላእክት መበከልና ማጥፋት የጀመሩት የሰውን ዘር ብቻ ሳይሆን እንስሳትንም ነበር። ስለዚህም ዘራቸውን ከእንስሳት፣
የሰውንም ዘር ከእንስሳት ጋር በማደባለቅ ካይሜራ (CHIMERA) የሚባሉ ከፊል እንስሳ ከፊል ሰው የሆኑ አስፈሪ ፍጥረታትን መፍጠር
ብቻ ሳይሆን እነዚያ ፍጥረታት እንደ አማልክት እንዲመለኩም ያደርጉ ነበር። ለዚህ ነው የግብጽ አማልክት የሰውና የአንበሳ ድብልቅ
(SPHINX)፣ የሰውና የአሞራ ድብልቅ (ለምሳሌ የግብጽ አምላክ ሶካር) እና ሌሎችንም ፍጥረታት በመከላለስ የፈጠሩት። እነዚህ
ፍጥረታት በየትምህርት ቤቱ እንደተነገረን ተረት ተረት የፈጠራቸው የሰው ሃሳቦች (MYTH) ሳይሆኑ በእርግጥ የነበሩ ለመሆናቸው
ለዘመናት ተደብቀው የነበሩ ብዙ መረጃዎች ወጥተዋል ዛሬም እየወጡ ነው። ዛሬ በኛ ዘመን ደግሞ እነዚሁኑ እኩያን ፍጥረታት ነው በፊልም፣
በልብ ወለድ መጻህፍት፣ በልጆች መጫወቻዎችና በዜና መልክም ሳይቀር ALIENS፣ EXTRA TERRESTRIALS፣ SKY
TRAVELLERS ወዘተ በማለት ሊያቀርቡልን የሚሞክሩት። ሰይጣን መላእክቱን በዚህ መንገድ ያሰማራበት ምክንያት ደግሞ የሰውንና
የእንስሳትን ዘር በክሎ ለማጥፋት ነበር። ለዚህ ነው ጌታ አምላክ ኖህንና ቤተሰቡንና፣ የተመረጡ እንስሳትን ብቻ በማስቀረት በዚያ
ዘመን የነበረውን ዓለም በውኃ ያጠፋው።
የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣንና
በሰማያዊ ስፍራ ያሉ የክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት መኖራቸውን ብዙዎቻችን ክርስቲያኖች በጨረፍታም ቢሆን ብናውቅም፣ ከዚህ በላይ ባጭሩ
ለማቅረብ የሞከርኩትን መረጃ ለማመን ለብዙዎቻችን ከባድ መሆኑን እረዳለሁ። ይህንን መረጃ ያቀረብኩበት ዋነኛ ምክንያ አንድ ነው።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን፣ በዚህ በኛ ዘመንና የሱ ዳግም ምጽዓት በሚቃረብበት ጊዜ እንደ ኖህ ዘመን ሁሉ የሰይጣን አሰራር በረቀቀ መንገድ እየተገለጠ ስለሚሄድ ነው። ልብ ብላችሁ ከሰማችሁና
ካያችሁ ብዙ ፊልሞች፣ መጻህፍት፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ የህጻናት
ፊልሞችንም ጨምሮ የሚያወሩትና የሚያሳዩት ስለ ALIENS፣ EXRA TERRESTRIALS፣ ሰውን ስለሚተኩ ሮቦቶች፣ ሰውና እንስሳ
ስለሚመስሉ ፍጡሮችና እነዚያም ደግሞ ከኛ ከሰው ልጆች የተሻሉ መሆናቸውን ነው። StarWars እና Independence Day የሚባሉት ፊልሞች ብቻ እንኳን ለዚህ በቂ ምሳሌዎች ናቸው። በ2016 ብቻ የሚከተሉት
13 ፊልሞች የተሰሩትና የቀረቡት በዚህ ርዕስ ላይ ነው፤ Moonwalkers, The Fifth Wave, Lazer Team, The Last Man on
the Moon, The Little Prince, Batman v Superman: Dawn of Justice, Independence
Day: Resurgence,
Star Trek Beyond, The Space Between Us, Rogue One, Passengers። እነዚህና ከነሱም በፊት የወጡ ፊልሞች፣
የሚናፈሰው ዜናና ለልጆቻችንም በየትምህርት ቤቱ የሚሰጠው ቀልድ መሰል ትምህርት ዓላማቸው አንድ ነው። ይህም ዓላማ ጌታ አምላካቸውን
በሚገባ የማያውቁ ክርስቲያኖችን ጨምሮ የዓለም ህዝብ ሃሰተኛውን ክርስቶስን እንዲቀበሉ ልባቸውን ለማዘጋጀት ነው። በሚቀጥሉት ትምህርቶች
ይህንን በተመለከተ የበለጠ ዝርዝርና ክርስቲያኖች እንዴት ከዚህ ስህተት መጠበቅ እንደምንችል መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን መሰረት
አድርገን እንማራለን። እስከዚያ ግን መደንገጥ ወይም መታወክ የለብንም። እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ሁሉ በቁጥጥሩ ስር ያደረገውን፣
ድል የነሳውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለተቀበልን በሚመጣው ነገር ሁሉ ድል አድራጊዎች ነን። የእግዚአብሔር ቃል የገለጸልንን እውነት
ሁሉ ለማወቅ መትጋት ግን ያስፈልጋል። ጌታ ይባርካችሁ። አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር በፈ ቃዱ ብርሃኑ አድማሱ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ